Friday, 31 January 2014

ቤተ ክርስቲያን የማናት?

ወላይታ ሶዶ ደብረ መንክራት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያንTewodros Belete Mengistu's photo.
 
                                                                        

እርግጠኛ ነኝ ሁላቸሁም አንባቢዎች ይህንን ጽሁፍ ስትመለከቱ የሁላችንም ናታ! እንደምትሉ ይገባኛል ፡፡ ነገር ግን ይህንን ጥያቄ ለማንሳት የተገደድኩት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቤተ ክርስቲያን የጥቂት ግለሰቦች መሆኗ በግልጥ ይታያል ፡፡ እኔ እንደማምነው ቤተ ክርስቲያን ከስያሜው እንደምንረዳው የክርስቲያን ሁሉ እንጂ ጥቂት የፖለቲካ ሰዎች ወይም መነኮሳት ወይም ደግሞ ያለ ምልአተ ጉባዔ ውሳኔ የጥቂት ጳጳሳት ብቻ ሆና እየታየች ነው ከዚህ የተነሳ ሊቃውንቱ ፤ ቀሳውስቱ ፤ምእመናኑ  በተለይ የነገዋ የቤተክርስቲያኒቱ ሆነ የሀገሪቱ ተረካቢ  የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ቤተ ክርስቲያኒቱ በምንም መልኩ የማትመለከታቸው እስኪመስል ድረስ ከላይ የጠቀስኳቸው ጥቂት አካላት  ቤተክርስቲያኒቱን ወደከፋ የኑፋቄ ማዕበል ሞገድ ውስጥ ለማስገባት ጥረት እያደረጉ መሆኑ ግልጥ ነው ለዚህ እንደ ጥሩ ማሳያ መመልከት የምንችለው በቅርቡ ታረቀ ተብሎ በቀጥታ  እንዲያስተምር የተፈቀደለት በጋሻውን መጥቀስ በቂ ነው፡፡ እኔ በጣም የደነቀኝ  በጋሻው ወደ አውደ ምህረት እንዲመለስ ቀን ከሌሊት የሚወጡ የሚወርዱ ጥቂት ጳጳሳትም ሆኑ ሌሎች ሰዎች  ቤተ ክርስቲያን ስትቃጠል፤ ስትዘጋ እንዲሁም በጂንካና በጉምዝ በአጠቃላይ በጠረፋማው አካባቢ ያሉት የሰው ልጆች የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች መሆን እንፈልጋለን የሚያስተምረን ፤የሚያጠምቀን  አጣን ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ በአህዛብ ተከበው  ቤተ ክርስቲያናቸው ሲቃጠልባቸው ደም ሲያለቅሱ አንድ ቀን እንኳን እንባቸውን የሚያብስ ጠፍቶ እያየን ነው ነገር ግን የለየለትን መናፍቅ ወደ አውደ ምህረት ለመመለስ የ24 ሰዓት ትጋት ሚስጥሩ ምን ይሆን ? የቤት ሥራውን የሰጠው ማነው? ያን ጊዜ ማለትም በ1999 ዓ.ም በጅማ ዞን በበሻሻ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ህዝበ ክርስቲያኑ በገዛ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ በገጀራ አንገቱ ሲሰየፍ በእሳት ሲቃጠል ማነው ከጳጳሳትም ሆነ ሌሎች የቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ ሐላፊዎች ህዝቡን ያጽናናው? ጆሮ ዳባ ልበስ ተብሎ አይደለም የቀረው? ዛሬ በጋሻው ወደ አውደ ምህረት ካልተመለሰ ሞቼ እገኛለሁ የሚሉ ግለሰቦች ያን ጊዜ የት ነበሩ? አሁንም ቢሆን ቤተ ክርስቲያን ስትቃጠል እሳት የሚሞቁ መሆናቸው የታወቀ ነው ፡፡ቅዱስ ሲኖዶሱ መናፍቁ በጋሻው በአካል ቀርቦ ይጠየቅ ባለው መሠረት ቢጠራ መቅረብ ያልፈለገው በጋሻውን በአቋራጭ ታርቆአል ብለዋል  ለመሆኑ የኑፋቄ ጉዳይ በእርቅ ተፈቶአል ማለት እኮ ሊቃውንቱን ፤ካህናቱን፤ ምእመናኑን መናቅ አይደለም? ወይስ ቤተ ክርስቲያን የእኛ ብቻ ናት ማለትስ አይደለም? እንግዲህ ሁሉም ገደብ አለውና ከዚህ በኋላ መታገስ በጉዳዩ መስማማት ስለሚሆን  የሚከተሉትን ማድረግ ግድ ይላል

2.    ከዚህ በፊት ወጣቱ ስለነ በጋሻው ጉዳይ መረጃ አጠናክሮ ለቅዱስ ሲኖዶስ  በማቅረቡ ሲኖዶሱም ወደ ሊቃወንት ጉባዔ መመራቱ ይታወቃል  ነገር ግን ሊቃውንት ጉባዔው በሁለት በመከፈሉ ማለትም የተወሰኑት ሊቃውንት በመረጃው መሠረት ይወሰን ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ ምንም ችግር የለበትም በማለት ግንኙነት ያላቸው ይከራከራሉ እና መረጃዎቹ ሁሉ ተዳፍነዋል
3.     ከዓለማቀፉ የተሀድሶ ጉሩፕ የተለቀቀው ገንዘብ ምክንያት ጥቂት ተሀድሶን የሚያስፋፉ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር መመሳጠራቸው  በግልጥ ይታወቃል ይህንን መረጃ በቅርቡ ይፋ የሚደረግ ቢሆንም ምእመናን ቤተ ክርስቲናችንን ከቀድሞው ይልቅ ጠንክረን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ መገንዘብ ማስገንዘብ ያስፈልጋል
4.     ከዚህ በኋላ በቸልተኝነት ብዛት ቤተ ክርስቲያናችን በተሃድሶ ወራሪ ልተወረር ስለምትችል እስከ ሞት ድረስ መስዋእትነትን በመክፈል መተበቅና የመሳሰሉትን ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ፡፡
           ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን

2 comments:

  1. Werena hamet astelegn...lemin memenanun tebetebitalachu merja kale sinodos lay akirbe endiwegez madereg newu .
    kalebeleza sibket teresto siele kidusan sile emebetachin ,..........tetachu yesewu hamet lay yetesemarchu sewoch Egizeabheren feru. Ene eterateralehu enate rasachu tadiso protestant satihono atkerum ...Betekiristiyan higia siriat eyalat higina siriat endelelat yemitadergu tada enate yetewahido lijoch nachu .
    betu balabet alewuna zim belu !

    ReplyDelete
  2. ለህዝቡ ስርዐተአልበኝነት-anarchism እያሰተማራችሁ መሆኑ ነው!!!ይሄ ማህበር በዚህ አካሄዳችሁ የተነሳ እንዳይፈርስ እሰጋለሁ.በጣም ፊጥ…ፊጥ ብላችሁዋል. ህዝቡ ዳር አይደለም. ሰበካጉባኤ ማለት የምዕመን፣የሰ/ተማሪ፣የካህናት ውህደት ነው. ስለዚህ ህዝቡ ከአመራሩ ጀምሮ የቤተክርስቲያን ባለቤት መሆኑ ግልጽ ነው.
    ወይ ፊትለፊት ኑ.ያለዚያ የታዳጊ ሰ/ተማሪዎችን አእምሮ በመበረዝና ጥቂት የዋህ ምእመናን አሳስቶ ከለላ በማድረግ በምእመንና ሰ/ተማሪ ስም አመራሩን ለመውሰድ የምታደርጉት ጥረት ማንንም አይጠቅምም-ራሱን ማህበረቅዱሳንን ጨምሮ.ያለፉት የአቡነጳውሎስ ዘመን ፕሮፖጋንዳዎቻችሁ ይበቁናል. ወደዛ ዘመን አትጎትቱን. ምእመኑንም ከካህናት ለመለየት አትጣደፉ.
    ተሀድሶዎች ወትሮም የሚለዩት በሊቃውንት እንጅ በምዕመናን አይደለም.እንዲያ አልተጻፈልንም.አባቶችም እንዲህ ያለ የምዕመን ውግዘት አብነት ብለው አላኖሩልንም.
    የበጋሻው ኑፋቄው ምን እንደሆነና ከየትኛው የቤተክርስቲያናችን መጽሀፍ እንደሚጣረስ ብትነግሩን መልካም ነው.ከዚህ ውጭ ከእናንተ ነጠላ አደግድጎ መመጻደቅ የሚያውቃትን የሚያካፍለው በጋሻው እንደሚሻል ስገልጽ ያለምንም መሳቀቅ ነው.

    ReplyDelete