Wednesday, 22 January 2014

የሆሳዕና ቡሻና በዐታ ለማርያም ገዳም ተቃጠለ

     ጥር 13 ቀን 2006 ዓም.   

                        
በእንዳለ ደምስስ
በሐድያና ስልጢ ሀገረ ስብከት ጎረጎራ ወረዳ ውቅሮ ፋለታ ቀበሌ የደብረ ምጥማቅ ቡሻና በዓታ ለማርያም ገዳም ጥር 10 ቀን 2006 ዓ.ም. የከተራ ዕለት መነሻው ባልተወቀ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ መቃጠሉን የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ቢኒያም መንቻሮ ገለጹ፡፡bushana

ሥራ አስኪያጁ በሰጡን መረጃም የከተራ ዕለት የበዐታ ለማርያም ታቦት ወደ ጥምቀተ ባሕር ከወረደ በኋላ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ መቃጠሉን ገልጸው ቤተ ክርስቲያኑ ንዋያተ ቅዱሳቱን ጨምሮ ሙሉ ለሙሉ ወድሟል ብለዋል፡፡

በካዝና ውሰጥ የነበረው የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጽላት ካዝናው በእሳቱ በከፍተኛ ሁኔታ በመለብለቡ ምክንያት መክፈት እንዳልተቻለና መቃጠልና አለመቃጠሉን እንዳልተረጋገጠ ያስታወቁት ሥራ አስኪያጁ፤ ጉዳዩን ለፖሊስ በማሳወቅ የቃጠሎውን መንስኤ ለማጥራት ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

የቡሻና በዐታ ለማርያም ገዳም ከዚህ በፊት ሥዕለ አድኅኖ በዛፎች ላይ ታይቶበት በነበረ ቦታ መቃኞ ተሰርቶለት ሐምሌ 2001 ዓ.ም. ቅዳሴ ቤቱ እንደተከበረ ይታወቃል፡፡

1 comment:

  1. በሆሳእና ቡሻና ስለሆነው ነገር ስለምን እንጨነቃለን? በሁሉም አቅጣጫ ኦርቶዶክሳውያን ተቆጥተን ሀገራችንን የሁከት ሜዳ እንድናረጋት የተሸረበውን ሴራ ስለምን በትእግስት እና በጸሎት አናልፈውም? እኛ እኮ ያለነው በመስታወት ውስጥ ነው። ጌጣችን እንዳይሰበር ሀላፊነት አለብን። ይህች ሀገር በሰላም ውላ ሰላም እንድታድር ከማንም በላይ ኦርቶዶክሳውያን ሀላፊነት አለብን። አባቶቻችን ብዙ ከፍለው ኢትዮጵያን እንደሀገር አቆይተዋል። ያልገባቸው ብዙ ይላሉ። ብዙ ይሰራሉ። በዚህ እልህ ገብቶን ይህችን ቅድስት ሀገር ወደ አልሆነ ነገር እንድንከት ስለሚፈታተኑን ስለምን ይጨንቀናል? ሆሳእና ቡሻና ያሉ ስልጣኔ እና ዲሞክራሲ ምን እንደሆነ ባልገባቸው ገና ምግብ ጠግበው ባልበሉ ስለሆነው ጉዳይ እናዝናለንን? ይልቁንስ እግዚአብሄር በአለም ላይ እያገነነን መሆኑን የአሜሪካን ሲያትል የጥምቀት በአል አከባበርን አላያችሁምን? ከጫካ ያልወጡ ቢያቃጥጥሉን የሰለጠነው ህዝብ ደግሞ ታቦታችንን በሞተር ሳይክል አጅቦ አከበረን። እባካችሁ ተስፋ አትቁረጡ የትኛው ነቢይ ነው በሀገሩ የተከበረው? ተዋህዶስ መቼ ነው ከመስቀል ወርዳ የምታውቀው? ህግ ለማስከበር የተሾማችሁ ዘር ቁንቁዋ ሃይማኖት ፖለቲካ ወይም ሌላ አስተሳሰብ የህግ የበላይነት በሰፈነባት ኢትዮጵያ ይህን የሽብር ተግባር የፈጸሙትን ልክ በማስገባት ስልጣኔያችሁን እንድታሳዩ እንጠብቃለን።

    ReplyDelete