በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራስኪጅ ፊርማ የወጣው የዋና ጸሐፊዎች ዝውውር የተነሳ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ደብር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ሊቀ ስዩማን ፍቅሩ
መስፍን በማንሳት ወደ ጽርሐ ጽዮን ጎላ ቅዱስ ሚካኤል መዛወራቸውን ተከትሎ የቀጨኔ አካባቢ ምእመናን በሰላም ከካህናቱና ከምእመናኑ
ጋር ተግባብቶ ለልማት በመፋጠን ላይ ያለውን የደብራችንን ዋና ጸሐፊ ያለምንም ምክንያት አዛውረው በሙስናና ሙዳዬ ምጽዋት በመገልበጥ
የሚታወቀውን የደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤ ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሐፊ የነበረውን መጋቤ ጥበብ ሠናይን ወደ ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ደብር በዋና ጸሐፊነት በመዛወራቸው ከፍተኛ ቅሬታ
ፈጥሯል፡፡ በተለይ የደብሩ ካህናትና የአካባቢ ወጣቶች ሀገረ ስብከቱ ያወጣውን አዲሱን መዋቅር /ለውጥ በጉጉት ለተግባራዊነቱ በመጠባባቅ
ላይ እያለን ሰላማዊውን እና በሁለንተናዊ ብቃት ያለውን ማለትም በዘመናዊው
እና በመንፈሳዊ ትምህርት ዝግጅት ያለውን ሊቀ ስዩማን ፍቅሩን አንስቶ
በሙስና ዓለም ያወቀውና በምንም ቢቀመር በሙስና ካልሆነ በስተቀር ብቃት የሌለውን ሰው ዋና ጸሐፊ ብሎ መመደብ ሀገረ ስብከቱ አሁን የጀመረውን የለውጥ ጎዳና የሚያሰናክል በመሆኑ ያለ ጥናት
የሚተገበሩ ዝውውሮች ሆነ ቅጥሮች በጥንቃቄ መሆን አለበት ብለዋል ፡፡በተለይ እንደ ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ያሉ አድባራትን
ለቦታው የማይመጥኑን መጋቤ ጥበብ ሠናይን በዋና ጸሐፊነት መመደብ
ከታሰበው ለውጥ ጋር የሚቃረን በመሆኑ ሊስተካከል ይገባል ብለዋል፡፡ ወጣቶቹ ባለፈው ቅዱስ ፓትርያርኩ‹‹ ሙስናን ለማጥፋት ተፋጠኑ,, በማለት እንዳሳሰቡት ሁሉ አሁንም በሙስና ገንዘብ የሰከሩትን
መጋቤ ጥበብ
ሠናይ የተባሉት የደብሩ ዋና ጸሐፊ ሆነውተመድበው ማገልገል አይችሉም በማለት
ተቃውሞአቸውን ለመግለፅ ወደ ሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ለመሄድ ዝግጅት ማድረጋቸው ተገልጦአል፡፡
No comments:
Post a Comment