እንደሚታወቀው አቡነ ሳዊሮስ በተለያዩ ሚዲያዎች እንደተዘገበው ከተሸሙ እስከ አሁን በሄዱበት ሀገረ ስብከት ህዝቡን ከመበጥበጥ ወደኋላ ብለው እንደማያውቁ ይታወቃል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከትንም የተሃድሶ
መናፍቃን መፈንጫ ለማድረግ ሙከራ ቢያደርጉም በቀድሞው ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ስብከት የታነጸ ታላላቅ ምእመናንና ወጣቶች ያሉበት በመሆኑ በእንጭጩ ሊቀጭ ተችሎአል ነገር
ግን ጳጳሱ ሀገረ ስብከቱን የሚመሩበት አቅም ስለሌላቸውና በሰላማዊ
መንገድ ተስማምተው መምራት ስላልቻሉ ሥራስኪያጃቸውን ጨምሮ በአስቸኳይ እንዲነሱ ጠይቀዋል ጳጳሱ በአገኙት በድረክ ሁሉ እኔን የበጠበጠኝ
ማኅበረ ቅዱሳን ነው እያሉ በማሳበብ የኛን ጥያቄ ወደጎን መተዋቸው ንቀት ነው ; በማለት ህዝቡን የበለጠ እንዳስቆጣ ምእመናን ገልጸዋል
ትናንት በ27/4/2006 ዓ.ም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሁለት ልዑካን የላከና ከተወሰኑት የሀገር ሽማግላች ጋር ለማደራደር
ቢሞከርም ጉዳዩ የህዝብ ነው መወሰን ያለበት
ህዝቡ ነው በማለት ለሐሙስ ጥር 1/5/2006 ዓ.ም ቀጠሮ ተይዞአል በተለይ በወሊሶ ከተማ እና ወረዳዎች ያሉ ምእመናን በቅርቡ
ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ፓትርያርኩ ጽ/ቤት እንደሚመጡም ታውቆአል ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የተላኩት ልዑካንም ወደ ጳጳሱ
እንደሚያደሉም አንዳንድ ምእመናን ስጋታቸውን ቢገልጡም ምንም የሚመጣ ለውጥ እንደ ሌለ ይናገራሉ በቅርቡ ምእመናን ጳጳሱን ማየትም ሆነ ድምጻቸውን መስማት አንፈልግም በማልት ከየ ደብሩም ሆነ
የቅዱስ ገብርኤል በዓል ዕለት/ታኅሳስ 19 ቀን ከጨፎ ቅ/ ገብርኤል
ቤ/ክ እንዳሰናበታቸው ይታወቃል የዞኑ አስተዳደርም በቅርብ ርቀት እየተከታተለ የሚገኝ ሲሆን ቤተ ክርስቲያኗ የራሷን ችግር በራሷ
ትፍታው ጣልቃ መግባት አልችልም ችግሩ የማይፈታ ከሆነ ግን ህዝቡ መታወክ ስለሌለብ የራሱን ድርሻ ሊወጣ እንደሚችል ተገልጦአል በአስቸኳይ ጳጳሱንና ሥራስኪያጁን ማንሳት ካልተቻለ ግን ወደ ሌላ ብጥብጥ
/ግጭት እንዳያመራ አንዳንድ ምዕመናን ስጋታቸውን ገልጠዋል ፡፡ ቀጣይ
ሂደቶችን አናደርሳለን
egnih sew ye tehadison alama lemasakat new pipisinan yetekeblut........min endemil alakim gin Geta Egziabher ye ejachun yistachu ye cinodosun gubae eregtew eskemewtat yederesu ahunim beyehedubet mibetebetu memenun ke betekristian lemaswetat tatkew ketensut mehal nachew
ReplyDelete