Friday, 31 January 2014

ቤተ ክርስቲያን የማናት?

ወላይታ ሶዶ ደብረ መንክራት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያንTewodros Belete Mengistu's photo.
 
                                                                        

እርግጠኛ ነኝ ሁላቸሁም አንባቢዎች ይህንን ጽሁፍ ስትመለከቱ የሁላችንም ናታ! እንደምትሉ ይገባኛል ፡፡ ነገር ግን ይህንን ጥያቄ ለማንሳት የተገደድኩት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቤተ ክርስቲያን የጥቂት ግለሰቦች መሆኗ በግልጥ ይታያል ፡፡ እኔ እንደማምነው ቤተ ክርስቲያን ከስያሜው እንደምንረዳው የክርስቲያን ሁሉ እንጂ ጥቂት የፖለቲካ ሰዎች ወይም መነኮሳት ወይም ደግሞ ያለ ምልአተ ጉባዔ ውሳኔ የጥቂት ጳጳሳት ብቻ ሆና እየታየች ነው ከዚህ የተነሳ ሊቃውንቱ ፤ ቀሳውስቱ ፤ምእመናኑ  በተለይ የነገዋ የቤተክርስቲያኒቱ ሆነ የሀገሪቱ ተረካቢ  የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ቤተ ክርስቲያኒቱ በምንም መልኩ የማትመለከታቸው እስኪመስል ድረስ ከላይ የጠቀስኳቸው ጥቂት አካላት  ቤተክርስቲያኒቱን ወደከፋ የኑፋቄ ማዕበል ሞገድ ውስጥ ለማስገባት ጥረት እያደረጉ መሆኑ ግልጥ ነው ለዚህ እንደ ጥሩ ማሳያ መመልከት የምንችለው በቅርቡ ታረቀ ተብሎ በቀጥታ  እንዲያስተምር የተፈቀደለት በጋሻውን መጥቀስ በቂ ነው፡፡ እኔ በጣም የደነቀኝ  በጋሻው ወደ አውደ ምህረት እንዲመለስ ቀን ከሌሊት የሚወጡ የሚወርዱ ጥቂት ጳጳሳትም ሆኑ ሌሎች ሰዎች  ቤተ ክርስቲያን ስትቃጠል፤ ስትዘጋ እንዲሁም በጂንካና በጉምዝ በአጠቃላይ በጠረፋማው አካባቢ ያሉት የሰው ልጆች የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች መሆን እንፈልጋለን የሚያስተምረን ፤የሚያጠምቀን  አጣን ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ በአህዛብ ተከበው  ቤተ ክርስቲያናቸው ሲቃጠልባቸው ደም ሲያለቅሱ አንድ ቀን እንኳን እንባቸውን የሚያብስ ጠፍቶ እያየን ነው ነገር ግን የለየለትን መናፍቅ ወደ አውደ ምህረት ለመመለስ የ24 ሰዓት ትጋት ሚስጥሩ ምን ይሆን ? የቤት ሥራውን የሰጠው ማነው? ያን ጊዜ ማለትም በ1999 ዓ.ም በጅማ ዞን በበሻሻ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ህዝበ ክርስቲያኑ በገዛ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ በገጀራ አንገቱ ሲሰየፍ በእሳት ሲቃጠል ማነው ከጳጳሳትም ሆነ ሌሎች የቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ ሐላፊዎች ህዝቡን ያጽናናው? ጆሮ ዳባ ልበስ ተብሎ አይደለም የቀረው? ዛሬ በጋሻው ወደ አውደ ምህረት ካልተመለሰ ሞቼ እገኛለሁ የሚሉ ግለሰቦች ያን ጊዜ የት ነበሩ? አሁንም ቢሆን ቤተ ክርስቲያን ስትቃጠል እሳት የሚሞቁ መሆናቸው የታወቀ ነው ፡፡ቅዱስ ሲኖዶሱ መናፍቁ በጋሻው በአካል ቀርቦ ይጠየቅ ባለው መሠረት ቢጠራ መቅረብ ያልፈለገው በጋሻውን በአቋራጭ ታርቆአል ብለዋል  ለመሆኑ የኑፋቄ ጉዳይ በእርቅ ተፈቶአል ማለት እኮ ሊቃውንቱን ፤ካህናቱን፤ ምእመናኑን መናቅ አይደለም? ወይስ ቤተ ክርስቲያን የእኛ ብቻ ናት ማለትስ አይደለም? እንግዲህ ሁሉም ገደብ አለውና ከዚህ በኋላ መታገስ በጉዳዩ መስማማት ስለሚሆን  የሚከተሉትን ማድረግ ግድ ይላል

2.    ከዚህ በፊት ወጣቱ ስለነ በጋሻው ጉዳይ መረጃ አጠናክሮ ለቅዱስ ሲኖዶስ  በማቅረቡ ሲኖዶሱም ወደ ሊቃወንት ጉባዔ መመራቱ ይታወቃል  ነገር ግን ሊቃውንት ጉባዔው በሁለት በመከፈሉ ማለትም የተወሰኑት ሊቃውንት በመረጃው መሠረት ይወሰን ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ ምንም ችግር የለበትም በማለት ግንኙነት ያላቸው ይከራከራሉ እና መረጃዎቹ ሁሉ ተዳፍነዋል
3.     ከዓለማቀፉ የተሀድሶ ጉሩፕ የተለቀቀው ገንዘብ ምክንያት ጥቂት ተሀድሶን የሚያስፋፉ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር መመሳጠራቸው  በግልጥ ይታወቃል ይህንን መረጃ በቅርቡ ይፋ የሚደረግ ቢሆንም ምእመናን ቤተ ክርስቲናችንን ከቀድሞው ይልቅ ጠንክረን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ መገንዘብ ማስገንዘብ ያስፈልጋል
4.     ከዚህ በኋላ በቸልተኝነት ብዛት ቤተ ክርስቲያናችን በተሃድሶ ወራሪ ልተወረር ስለምትችል እስከ ሞት ድረስ መስዋእትነትን በመክፈል መተበቅና የመሳሰሉትን ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ፡፡
           ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን

Sunday, 26 January 2014

የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ደብር ካህናትና አጥቢያ ምእመናን ለደብሩ አዲስ በተመደበው ዋና ጸሐፊ መጋቤ ጥበብ ሠናይ አየለን በተመለከተ ተቃውሞአቸውን ለመግለፅ ወደ ፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ አቡነ እስጢፋኖስ ዘንድ ለመምጣት መዘጋጀታቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡


 በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራስኪጅ  ፊርማ የወጣው የዋና ጸሐፊዎች ዝውውር የተነሳ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ደብር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ሊቀ ስዩማን ፍቅሩ መስፍን በማንሳት ወደ ጽርሐ ጽዮን ጎላ ቅዱስ ሚካኤል መዛወራቸውን ተከትሎ የቀጨኔ አካባቢ ምእመናን በሰላም ከካህናቱና ከምእመናኑ ጋር ተግባብቶ ለልማት በመፋጠን ላይ ያለውን የደብራችንን ዋና ጸሐፊ ያለምንም ምክንያት አዛውረው በሙስናና ሙዳዬ ምጽዋት በመገልበጥ የሚታወቀውን  የደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤ ቤተ ክርስቲያን  ዋና ጸሐፊ የነበረውን መጋቤ ጥበብ ሠናይን ወደ ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ደብር በዋና ጸሐፊነት በመዛወራቸው ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል፡፡ በተለይ የደብሩ ካህናትና የአካባቢ ወጣቶች ሀገረ ስብከቱ ያወጣውን አዲሱን መዋቅር /ለውጥ በጉጉት ለተግባራዊነቱ በመጠባባቅ ላይ እያለን ሰላማዊውን እና በሁለንተናዊ ብቃት ያለውን ማለትም  በዘመናዊው እና በመንፈሳዊ ትምህርት ዝግጅት ያለውን  ሊቀ ስዩማን ፍቅሩን አንስቶ በሙስና ዓለም ያወቀውና በምንም ቢቀመር በሙስና ካልሆነ በስተቀር ብቃት የሌለውን ሰው ዋና ጸሐፊ ብሎ መመደብ  ሀገረ ስብከቱ አሁን የጀመረውን የለውጥ ጎዳና የሚያሰናክል በመሆኑ ያለ ጥናት የሚተገበሩ ዝውውሮች ሆነ ቅጥሮች በጥንቃቄ መሆን አለበት ብለዋል ፡፡በተለይ እንደ ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ያሉ አድባራትን ለቦታው የማይመጥኑን መጋቤ ጥበብ ሠናይን በዋና ጸሐፊነት  መመደብ ከታሰበው ለውጥ ጋር የሚቃረን በመሆኑ ሊስተካከል ይገባል ብለዋል፡፡ ወጣቶቹ ባለፈው ቅዱስ ፓትርያርኩ‹‹ ሙስናን ለማጥፋት ተፋጠኑ,, በማለት እንዳሳሰቡት ሁሉ አሁንም  በሙስና ገንዘብ የሰከሩትን 

            መጋቤ ጥበብ
ሠናይ የተባሉት የደብሩ ዋና ጸሐፊ ሆነውተመድበው  ማገልገል አይችሉም በማለት ተቃውሞአቸውን ለመግለፅ ወደ ሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ለመሄድ ዝግጅት ማድረጋቸው ተገልጦአል፡፡