Saturday, 22 March 2014

የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ተቃዋሚ አማሳኞች ማኅበረ ቅዱሳን በአክራሪነትአ እና ሕገ ወጥነት የሚወነጀልበትን መሠረተ ቢስ ክሥ የሚያዳብር የአቋም መግለጫ የሚያወጡበትን ስብሰባ ቅዳሜ ለማካሔድ እየቀሰቀሱ ነው



ማኅበረ ቅዱሳን
ማኅበረ ቅዱሳን
  • አማሳኞቹ ‹‹በግንቦቱ ሲኖዶስ ለውሳኔ ይቀርባል›› ያሉት የአቋም መግለጫ ከፖሊቲከኞችና ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኞች ጋራ ግንባር የፈጠሩበትና የማኅበሩን መዋቅር እና አገልግሎት አዳክሞ ለመቆጣጠር አልያም አካቶ ለማፍረስ ለተያዘው የአስተዳደራዊ ርምጃ ውጥን ግብዓት የሚኾን ነው፡፡
  • የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር እና ሥራ አስፈጻሚ አባላት በደጅ ጥናትም ቢኾን ከፓትርያርኩ ጋራ በግንባር የመነጋገር ዕድል ካገኙና ፓትርያርኩም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ይዘው ሌላ ዙር ሰፊ ምክክር እንደሚያካሒዱ በገለጹሳምንት ጊዜ ውስጥ÷ ‹‹በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ለግንቦት ሲኖዶስ ውሳኔ ግብዓት የሚኾን የአቋም መግለጫ እናውጣ›› ለሚሉ አማሳኞች የስብሰባ ፈቃድ መሰጠቱና ፓትርያርኩም በስብሰባው ላይ ለመገኘት መስማማታቸው፣ ሰሞኑን የሚታየው የማኅበሩን እንቅሰቃሴ በአስተዳደራዊ ርምጃዎች የማሰናከልና አገልግሎቱን የማዳከም ርብርብ ውጫዊ ፖሊቲካዊ ግፊትም እንዳለበት አመላካች ኾኗል፡፡
  • ፓትርያርኩን በግንባር ያነጋገረው የማኅበሩ አመራር በአጠፌታው፣ የሚሰነዘርበትን ማንኛውንም ውንጀላ በፍትሕ አካል በሕግ አግባብ ከመፋረድ ጀምሮ በጥቅመኝነት፣ በፖሊቲከኝነትና በኑፋቄ ዓላማዎች የሚገፋውን የቀንደኛ አማሳኞች ክሥ በዐደባባይ ለመፈተንና ለማጋለጥ እንደሚሠራ ይጠበቃል፡፡
*                               *                              *
NebureEd Elias Abreha
ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከሰጠው አቅጣጫ በተፃራሪ ‹‹የአደረጃጀትና አሠራር ጥናቱን ዳግመኛ መገምገም›› በሚል በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ስም ተሠይመው የጥናት ሰነዱን በተጽዕኗቸው ሥር ካስገቡት ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ እና አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ጋራ ጥብቅ ቁርኝት ፈጥረው የሚንቀሳቀሱት አማሳኞቹ እነ ኃይሌ ኣብርሃ እና ዘካርያስ ሐዲስ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ሀብትና ንብረቱን ያስረክብ›› በሚል በጠሩት ስብሰባ ላይ የማይሳተፉ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችን በመፈረጅና የሓላፊነት ቦታቸውን በማስነጠቅ ጭምር ለማስመታት እየዛቱ ናቸው፡፡
  • ‹‹ድምፃችን አልተሰማም›› የሚሉ የተቋማዊ ለውጥ ደጋፊዎች በበኩላቸው፣ በአማሳኞቹ የተጠራውን ስብሰባ÷ የአደረጃጀትና አሠራር ጥናቱ የደረሰበትን ለማወቅ እና በማኅበሩ ላይ አላግባብ የሚደረገው ተጽዕኖ እንዲቆም ወደሚጠይቅ ትዕይንት ለመለወጥ እየተዘጋጁ ናቸው፡፡
  • ፓትርያርኩ የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ተቃዋሚ አማሳኞችን ለአማካሪነትና ለረድእነት ባቀረቧቸው ግለሰቦች አሳላፊነት በየዕለቱ ለማለት በሚቻል ኹኔታ እየተቀበሉ ከመማከር ባሻገር በስብሰባቸው ላይ ለመገኘት ፈቅደዋል መባሉ ለመልካም አስተዳደር፣ ፍትሕና ርትዕ ከሚናገሩበት ሞራላዊ ሥልጣን እንደሚያሰናብታቸው እየተነገረ ነውውጤቱም ቤተ ክርስቲያናችንን የርስ በርስ ትርምስ ውስጥ በመጨመር ተቋማዊ ህልውናዋን ለከፋ አደጋ እንዳያጋልጠው አስግቷል፡፡

No comments:

Post a Comment