Wednesday, 26 March 2014

ቤተ ክርስቲያንን የማፈራረስ የቀደመ ሴራ ሲያገረሽ “የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ላንተ ይብስብሀል” ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? (click here)


(አንድ አድርገን መጋቢት 15 2006 ዓ.ም )፡- አሁን መንግሥት በቤተክህነት ጥቂት ደጋፊዎችና በቆየ የውስጥ አላማው አማካኝነት ሊሰራ አስቧል የተባለው ማኅበረ ቅዱሳንን አመራሮች እና ቀጥሎም ማኅበሩን የሚከስ ዘጋቢ ፊልም ነገሩን ከአንድ ማኅበር ጋር ብቻ የሚያያይዙት አልጠፉም ፤ ነገር ግን ማኅበረ ቅዱሳን እና ቤተክርስቲያን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ መሆናቸው እስከ አሁን የገባቸው አይመስልም ፡፡ ባሳለፍናቸው 20 ዓመታት በርካታ ሥራዎችን በቤተክርስቲያኒቱ የእዝ ሰንሰለት ስር በመሆን ማኅበረ ቅዱሳን መስራቱ በአይን የሚታይ በእጅ የሚዳሰስ እውነት ነው፡፡ ጠላት ግን የሚታየው የባለፈው መልካም ሥራ ሳይሆን የወደፊቱ የእንቅፋት መንገድ ስለሆነ ዛሬ ላይ ይህን እግዚአብሔር የሚገኝበትን ረዥም ጉዞ ለማደናቀፍ በይፋ ሃይማኖተኞችም ፖለቲከኞችም ሳይሆኑ አንድን አላማ ለማሳካት በአንድ ጉባኤ ተሰብስበዋል ፡፡ ይህ ፊልም እንደተባለው ተሰርቶ ለእይታ የሚቀርብ ከሆነ ቀጥሎ ምን ሊከሰት እንደሚችል ለመገመት ነብይነትን አይጠይቅም ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ እንዲህ ባለበት አንድም ሰው ባጣችበት ጊዜ ላይ ፤ ሲኖዶሷ ለሁለት በተከፈለበት ፤ ሙሰኝነትና ዘረኝነቱ ጣራ የደረሰበት ፤ ሁሉም ሰሚ እንጂ ተናጋሪ አንደበት የሌለው ይመስል ዝም ባለበት ጊዜ የቤተክርስያኒቱ እምነት ፤ ሥርዓትና ትውፊት ትውልድ እንዲያውቅ ፤ አብነት ትምህርት ቤቶቿ ከመዘጋትና ከተማሪ ድርቅ ከመመታታቸው በፊት የቻለውን ያህል እያደረገ ዘለቄታዊ ካህናትና ዲያቆናት መሰል አገልጋዮች እንዲወጡ የበኩሉን ትንሽ የማይባል ሥራ እየሰራ የሚገኝውን ማኅበር በቤተክህነቱ ውስጥ የቀድሞ ስርዓት ርዝራዥ በሆኑ ሰዎች አማካኝነት ይሰራበታል የተባለው ዘጋቢ ፊልም የሚዘጋጅ ከሆነ ውድቀቱ ከአንድ ማኅበር ይልቅ የቤተክርስቲያኒቱ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባናል፡፡

ከዓመት በፊት የአቡነ ጳውሎስ  ዜና እረፍተ ከተሰማ በኋላ ሃዘን ለመድረስ የመጡት የህወሀት የቀድሞ ከፍተኛ አመራር  ቤተ ክርስቲያኒቱ ሃገራዊ ግዴታዋን ስትወጣ የነበረች፣ ለወደፊቱ ታላቅ ሚና ሊኖራት የሚችል ስለኾነች አሁን የት አለች ብለን እናስብ በማለት በቤተክህነት አዳራሽ በተቀመጠው ደብተር ላይ ማስፈራቸው ይታወቃል፡፡ አዎን በቤተክርስቲያን ላይ የሚደረጉ ሴራዎችን የሚመሩት የሚያሳልጡትና መነሻ እና መድረሻቸውን አስልተው የሚጓዙት ፖለቲከኞች በአደባባይ እንዲ ይሉናል ፤ ዘወር ብለው ደግሞ ቤተክርስቲያኒቱ ሀገራዊ ያላትን ተሰሚነት ለመቀነስ በፖለቲከኞች የእዝ ሰንሰለት እንድትወድቅ እና አድራጊ እና ፈጣሪዋን እንድትለይ የኮሜዲ ድራማ ስክሪፕት ሃሳብ ያመነጫሉ ፡፡ አንዳንዴ የሚያገኙት ጥቅም አይናቸውን ያሳወራቸው የውስጥ እና የውጭ ጠላቶች ደግሞ በትህምክት ባህር ውስጥ የሰመጡ ትህምክተኛ ሆነው ሳለ የ“ትምክተኞች” መሰብሰቢያ ብለው ሲናገሩ ይስተዋላል፡፡
ቀድሞ በቤተክርስትያናችን አባቶች ላይ የተከፈተው የስም ማጥፋት ዘመቻ የምናስታውሰው ነገር ነው ፤ አባቶች ሲሰደቡ ቤተክርስቲያን መሰደቧን ጭምር የምናውቅ ሰዎች ጥቂት ብንሆንም ፤ አሁን ደግሞ አንድ ላይ መስደቡ የማያዋጣ ስለመሰላቸው በተናጥል የመምታት ዘመቻ ውስጥ ሊገቡ እንደሆነ የሚሰሙትና የሚታዩት ነገሮች እያመላከቱ ይገኛሉ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ፍቃድ ሰጥቶት በተሰጠው ፍቃድ የሚንቀሳቀስን መንፈሳዊ ማኅበር አንደበት አውጥተው ሲሳደቡ ለሰማቸውና ጽሁፋቸውንም ላነበበ ሰው ቢዘገይም የሚደገስ ታላቅ የተንኮል ድግስ መኖሩ የማይቀር መሆኑ ይገባዋል፡፡ ጠላት የቤተክርስቲያኒቱን መሰረት ለመናድ ጥልቅ ጉድጓድ ቢቆፍርም መሰረቷን ሊያገኝው በሰውኛ ሃሳቢ ሊበታትናት ግን አይቻለውም፡፡ ቅዱስ መጽሀፉ ጠባቂዋ አያንቀላፋም ብሎላታልና፡፡
  
እስኪ ህወሀት(ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ) በቤተክርስትያን ላይ ያለውን አቋም ቀድሞ ምን እንደሚመስልና አሁን ሀገሪቱን እያስተዳደራት የሚገኝው የብሔር ተኮር ፓርቲዎች ስብስብ(ኢህአዴግ) እዚች አንዲት ቤተክርስቲያን ላይ እቅዱ ምን ነበር? የሚለውን የሚታወቅ ታሪክ ዘወር ብለን ለመመልከት እንሞክር፡፡
የህወሀት( ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ) መስራችና ኮማንደር የነበሩት ያያኔው ታጋይ ያሁኑ ዶክተር አረጋዊ በርሄ A Political History of the Tigray People’s Liberation Front ( 1975-1991) የተሰኘ መጽሐፍ ማሳተማቸው ይታወቃል። መጽሐፉ አስራ ሁለት ምእራፎችና 355 ገጽ ያሉት ሲሆን በይዘቱም በርካታ ጉዳዮችን ይዳስሳል።
የመጽሐፉ ደራሲ ደግሞ የህወሀት የፖሊት ቢሮ አባልና ከህወሀት ጥንሥስ ጀምሮ ፖሊሲ አውጪ አመራር ስጭና አዋጊ ስለነበሩ በተራ አባላቶቸ የማይታወቁ በርካታ ሚስጥሮችን በመጽሐፋቸው ይፋ አድርገዋል። መጽሀፉ ስለ ብሔር ፓለቲካ አደገኛነት ስለ ማሌሊት ማኒፌስቶ 1976 አና ትግራይን ስለመገንጠል የነበረውን ውዝግብ ስለ ስብሀት ነጋና መለስ ሚስጥራዊ ሰንስለቶች ስለ ጦርነቱ ከኤርትራው ኢሳያስ ጋር ስለነበረው ፍቅርና ጠብና አሁን ድረስ እያዋጉ ስላሉት መሰረታዊ ምክንያቶችና ሌሎች ብዙ አስገራሚ ሚስጥሮችን ይተነትናል።
እኔን ግን የሳበኝ ህወሀት ወይም ወያኔ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስቤተ ክርስቲያንላይ ከበረሀ ጀምሮ የሰራውን ደባ የሚያትተው ክፍል ነው።ዶክተር አረጋዊ በዚሁ መጽሀፋቸው ምእራፍ አስር ላይ “Neutralizing the Church and Mobilizing Muslims “ በሚለው ንኡስ ርእስ ስር ህወሀት የኢትዮጵያ ተዋሕዶቤተ ክርስትያንን እንዴት እንደተዋጋትና አሁን ቤተ ክርስትያና ውስጥ የሚታዩት አበይት ችግሮች በሙሉ ህወሀት ከበረሀ ጀምሮ ያቀዳቸው መሆኑን በዝርዝር አስቀምጠውታል።


ወያኔ ቤተ ክርስቲያንን መታገል ለምን ፈለገ?
ይህን መጽሀፍ ሳነብ ዋናው ጥያቄዬ የነበረው ወያኔ ቤተ ክርስቲያንን መታገል ለምን ፈለገ? “ የሚለው ነበር። ወያኔ በወቅቱ ቤተክርስትያንን አምርሮ መታገልና ማዳከም የፈለገበትን ምክንያቶች ዶክተር አረጋዊ አንድ ባንድ አስቀምጠውታል።በሚገርም ሁኔታ አንዱና ዋናው ምክንያት የቤተክርስቲያኗ ብሔራዊ አስተምህሮ መገንጠልን መቃወምና የሀገሪቱን አንድነት ደጋፊ መሆንና በባንዲራና መሰል ኢትዮጲያዊ መገለጫዎች ላይ የነበራት አስተምህሮ እንደሆነ እንዲህ ሲሉ አስቀምጠውታል።
“A combination of factors made relations between TPLF and the EOTC church difficult …the church taught its followers to respect their allegiance to the Ethiopian state and was, in effect , a school for national consciousness, using national symbols such as the flag in all religious and social events. No church ever conducted major ceremonies without hoisting the Ethiopian flag – an act also regularly observed …’ page 244
“The pragmatic TPLF understood the church’s role in village social life and its support for the unity of the country .It also understood a possible alliance between the Church with its forces that stood against socialism and nationalization of the land as well as separatism .The church was viewed as a force standing in the way of TPLF. …there was no doubt that it wanted to subordinate the church to its cause” page 245
የኢትዮጵያ ተዋሕዶቤተክርስቲያን በህዝቡ ውስጥ ያላት ተቀባይነትና ቤተ ክርስቲያና በሀገር አንድነት ላይ ያላት ጽኑ አቋም  እግዚአብሔር  የለም ብሎ የሚያስተምረውን ሶሺያሊዝምን መቃወሟና በባንዲራ ላይ ያላት ጽኑ አስተምህሮናና የመገንጠል ተቃዋሚ መሆኗ በወያኔ ጥርስ ውስጥ እንድትገባ ምክንያት እንደሆነ ዶክተር አረጋዊ እማኝነታችውን ከገለጡ በሁዋላ ወያኔ ቤተ ክርስቲያኗ ላይ ያሳረፈውን በትር እንዲህ ሲሉ ጠቅሰውታል።
የኢትዮጵያ ተዋሕዶቤተክርስቲያንን ማደንዝዝና መቆጣጠር በብሔራዊ ማንነትና በሀገር አንድነት ላይ ቤተክርስቲያኗ የያዘችው ጽኑ አቁዋም ያበሳጨው ህወሀት ቤተ ክርስቲያኗን ለማደንዘዝና ለመቆጣጠር የለኮሰውን ባለ ሶስት ዘርፍ የጥቃት ዘመቻ እንዲህ ሲሉ ይዘረዝሩታል
አንደኛ ቤተክርስቲያኗ በህዝቡ ዘንድ ያላትን ማህበራዊ ተሰሚነት ማዳከምና የቤተ ክርስቲያኗ መንፈሳዊ ጉዳዮች ሳይቀሩ በካድሬ በሚመሩ ህዝባዊ ጉባኤዎች እንዲወሰኑ ማድረግ
“the second step was to try and move the socio economic focus of life from the church to the peoples assemblies. All administrative and social activities were taken over by the associations and the baitos and even church affair such as the rights and obligations of the church and its followers fell under the jurisdiction of the assemblies. The capacity of the church to mobilize and influence waned. The church lost its status as mediator in conflicts, rights over spiritual and familiar issues because the new political authorities….”
የሚገርመው ቤተክርስቲያኗ በራሷዋ መንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ እንኳን ለመወሰን መብቱን አሳጥቷታል። 1970ዎቹ እና ሰማነያዎቹ ህወሀት ነጻ አወጣሁዋችው በሚላቸው ቦታዎች በሙሉ የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ውሳኔዎች በካድሬና በካድሬ በሚመሩ ስብሰባዎች መወሰን ጀመሩ።
ሁለተኛው ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗን አመራር በሙሉ በህወሀት ካድሬዎች ማስያዝና የቤተክርስቲያኗን አመራረ ሙሉ በሙሉ ግእዝ በሚናገሩ ካድሬዎች መተካት እንደነበረ እንዲህ ሲሉ ይገልጹታል
“thirdly , the TPLF launched a series of conferences or seminars for selected parish priests in 1970 to win them over. The underlying motive of the seminars was to isolate the church in Tigray from the wider Ethiopian Church in order to foster Tigraian nationalism along the lines of the TPLF strategic objective. Suppressed Tigraian nationalism was invoked to challenge the dominant Ethiopian Orthodox Church. The initial wereda seminars for the priests were conducted by an eloquent TPLF fighter,Gebre Kidan Desta, a graduate of the theological College at Addis Ababa university .The themes of the seminars were to replace the Ethiopian Church authority by TPLF – minded church and the language in the church with Tigrigna and ultimately, to further Tigraian nationalism and identity ‘ page 246
የቤተ ክርስቲያኗን ኋይል ለማዳከምና ለመቆጣጠር መነኮሳት በማስመሰል ትልልቅ ገዳማት ውስጥ ካድሬዎችን በማስረግና በማስሾም በስብሐት ነጋ የሚመራ የስለላ ቡድን ለዚሁ ጉዳይ ሲባል መዋቀሩን እንዲህ ይገልጹታል
“this process involved the mobilization of parish priests and ordinary Christians to isolate them from the church national hierarchy. To weaken church authority, an intelligence group was formed under Sibhat Nega to infiltrate the wel-established monasteries in Tigrai, such as Debre Damo , by planting TPLF members’ camouflaged as monks and influencing church activities in the interests of TPLF”
ሌላውና አደገኛው ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗን አመራር ለሁለት የመክፈል ጉዳይ ነው
1987 እና 1989 (እኤአ) ትግራይ ያለውን የኢትዮጵያ ተዋሕዶቤተ ክርስቲያን ሀገረ ስብከት ከማእከላዊው የቤተክርስቲያን ሲኖዶስ መለየትና የቤተ ክርስቲያኗንም አስተዳደር ለሁለት መክፈል ከበረሀ ጀምሮ የታሰበበትና የተተገበረ ጉዳይ መሆኑን በማያወላዳ ሁኔታ እንዲህ ገልጸውታል
“ in 1987 and 1989 ,regional and national conference for priests were organized by the TPLF in liberated territories to reshape the Tigray Church in line with the TPLF program . A separate secretariat of the Orthodox Church was formed in the liberated areas of Tigray and was supposed to operate under TPLF guidelines. Practically, the Ethiopian Church was divided in to two secretariats…’
አራት ኪሎ ቤተ ክህነት
ዶክተር አረጋዊ በርሄ የጻፉት ይሄ ሁሉ ሴራ የተጎነጎነውና የተተገበረው ገና ወያኔ አዲስ አበባ ሳይገባ በረሀ ላይ እያለ ነበር። ወያኔ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ በቤተ ክህነቱ ዙርያ ምን ተፈጸመ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስና በበረሀ ታቅደው መተግበር ከጀመሩት ሴራዎች አንጻር ለመመልከት ውሳኔዎቹንና እቅዶቹን ደግመን እንያቸው
1. ቤተክርስቲያኗ ያላትን ማህበራዊ ተሰሚነት ማዳከምና የቤተ ከርስቲያኗ መንፈሳዊ ጉዳዮች ሳይቀሩ በካድሬና በካድሬ በሚመሩ ህዝባዊ ጉባአኤዎች እንዲወሰኑ ማድረግ
2. የቤተ ክርስቲያኗን ሀይል ለማዳከምና ለመቆጣጠር መነኮሳት በማስመሰል ትልልቅ ገዳማት ውስጥ ካድሬዎችን በማስረግና ማስሾም
3. የቤተ ክርስቲያኗን አመራር በሙሉ በህወሀት ካድሬዎች ማስያዝና የቤተክርስቲያኗን አመራር ሙሉ በሙሉ ግእዝ በሚናገሩ ካድሬዎች ማስያዝ
4. የኢትዮጵያ ተዋሕዶቤተ ክርስቲያን ሀገረ ስብከት ከማእከላዊው የቤተክርስቲያን ሲኖዶስ መለየትና የቤተ ክርስቲያኗንም አስተዳደር ለሁለት መክፈል ይገኙበታል፡፡ ያልተፈጸምው የቱ ይሆን? የኢትዮጵያ ተዋሕዶቤተ ክርስቲያን በሁለት ሺህ አመት ታሪኳ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሲኖዶሷ ለሁለት ተከፍሏል። የቀድሞው የሀገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔም ለአሜሪካው አምባሳደር ዶናልድ ያማሙቶ እንደገለጹት አባ መርቆሬዎስ ከሀገር የወጡት በፖለቲካ ውሳኔና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፊርማ መሆኑን ገልጸዋል። እኚህም ሰው ከዓመታት እስር በኋላ ከእስር ሲለቀቁም በዚህ  ሥራቸው መጸጸታቸውንና የፈሰሰውን ውሃ ለማቅናት ፍላጎት እንዳላቸው ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ ሥራ ጋር ተያይዞም የቤተ ክርስትያኗ ሲኖዶስ ለሁለት ተከፍሏል።
የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች በቤተ ክርስትያን ሲኖዶስ ሳይሆን በሌሎች አካላት እንደሚወሰን የአባ ጳወሎስ ሀውልት ህያው ምስክር ነው።ሲኖዶሱ ይፍረስ ብሎ ቢወስንምየማይፈርሰው ሀውልት” ብለው የወሰኑትምእመናንውሳኔ እንደጸና የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ከዋልድባ ገዳም ጋር በተያያዘ የመንግሥትን አቋም በመደገፍ ሙሉ ይሁንታውን በአባቶች የሲኖዶስ ጉባኤ ሳይሆን ከበስተኋላ ሆነው በሚሾፍሩ ሰዎች የስምነት አጀንዳውን ላይ እንዴት ለማስገባት እንደሞከሩ የምናውቀው ነገር ነው፡፡
ከክርስቶስ ወንጌል ይልቅ ፖለቲካ የሚሰብኩ ጥቁር ራስ መነኮሳትና ነጭ ለባሽ ካህናት በየቤተ ክርስቲያኑ ማየትና ማድመጥ የተለምደ ከሆነ በርካታ አመታትን ተቆጠሩ።ሌሎቸም ብዙ ጉዳዮች ሆኑ። ለጊዜው ሁሉም እቅድ የተሳካ ይመስላል።የመውጊያው ብረት ላይ መቆም ተቸሏል። ለማን እንደሚብስ ግን ወደፊት የምናየው ይሆናል።የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ላንተ ይብስብሀልየሐዋርያት ስራ 9 5 የእግዚአብሔርን ለቄሳር አሳልፈው የሰጡሐዋርያትምስለሰፈሩት ሰልሳና መቶ ከግብር አባታቸው ዋጋቸውን ይቀበላሉ።
አሁን ነገ ቤተክርስቲያን ላይ ስለሚደርሰው ነገር በመመልከት ስለ አንዲት እምነታችንና እና ስለ አንዲት ቤተ ክርስቲያናችን ብለን በጋራ የምንቆምበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡   “አመልህን በጉያ ስንቅህ በአህያ” እንዲሉ አባቻችን በአንዲት ሀገራቸው ኢትዮጵያ ፤ በአንዲት  እምነታቸው ተዋሕዶተዋሕዶ ላይ የመጣባቸውን ነገር ለመመለስ “ክተት ሰራዊት ምታ ነጋሪት” በማለት አንድነታቸውን ያሳዩ ነበር ፤ አሁንም ይሰራል የተባለውን የቅድመ ክስ ዶክመንተሪ ቀጣይ ዳፋውን ከአንድ ማኅበር በላይ በማየት አሁን ላይ ስለ አንዲት እምነታችን ዘብ ልንቆም ይገባል፡፡
የቤተ ክርስቲያን አምላክም ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን፡፡

ቤተ ክህነቱን ከሙሰኞችና ከጎሰኞች የማጥራት ዘመቻው ይሳካ ይሆን?! Posted by DejeS ZeTewahedo

March 25, 2014



(ደጀ ሰላም፣ መጋቢት 14/2006 ዓ.ም፤ ማርች 24/2014/ PDF በፍቅር ለይኩን):- ባለፈው ሳምንት ‹‹የፓትርያርኩ የለውጥ ተስፋዎች ወዴት ገቡ?›› በሚል አቶ መብራቱ መርሳ የተባሉ ግለሰብ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን ፓትርያርክ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ በቤተ ክህነቱ ተቋም የተንሰራፋውን ሙሰኝነትንና ጎጠኝነትን በተመለከተ የተማፅኖ ጦማራቸውን በሪፖርተር ጋዜጣ በኩል ለቅዱስ ፓትርያርኩ ይደርስ ዘንድ አቅርበው ነበር፡፡ እኚህ ግለሰብም ባቀረቡት የተማፅኖ ደብዳቤያቸው ዋና አሳብም፣ ቅዱስ ፓትርያርኩ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ውስጥ የነገሠውን አድር ባይነት፣ ዘረኝነት/ጎጠኝነትና ሙስና ለማጥፋት በአደባባይ ቃል የገቡበትን ዘመቻቸውን አጠንክረው እንዲቀጥሉበትና ፍሬውን በተግባር እንዲያሳዩ የሚጠይቅ ነው፡፡

በእርግጥ ይህ የአንድ ግለሰብ ብቻ ሳይሆን የበርካታዎች የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ መሪዎች፣ አባቶች፣ አገልጋዮችና ምእመናን የቀን ተሌት ብርቱ ምኞትና ተማፅኖ ነው፡፡ እኚህ ሰው ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ወደ ፕትርክና መንበር በመጡ ማግሥት የቤተ ክህነቱን ተቋም ከጎጠኞችና ከሙሰኞች ለማጥራት የገቡት ቃል ተግባራዊ ኾኖ ለማየት የነበራቸው ምኞት ከዓመት በኋላ የተጠበቀውን ያህል ዘመቻው ስኬት ባለማሳየቱና የለውጡም ሂደት በመንቀራፈፉ ሥጋት ቢጤ ገብቷቸው ይመስላል ይህን የተማፅኖ ደብዳቤ ለፓትርያርኩና ለሚመሩት የቤተ ክህነት ተቋም ለማድረስ የወደዱት፣ የተገደዱት፡፡
የእኚህ ግለሰብ ‹‹የለውጥ ያለኽ›› ተማፅኖ ጦማር በርካታዎችን የቤተ ክርስቲያኒቱን አባቶችን፣ አገልጋዮችንና ምእመናን የሚወክል እንደሆነ ነው በግሌ የማምነው፣ የምቀበለውም፡፡ የብዙዎች የአባት ያለኽ፣ የመሪ ያለኽ፣ የፍቅር ያለኽ፣ የእውነት ያለኽ፣ የፍትሕ ያለኽ፣ የበጎነት ያለኽ፣ የቅንነት ያለኽ፣ የመንፈሳዊነት ያለኽ፣ የለውጥ ንፋስ ያለኽ ጩኸትና አቤቱታ የቤተ ክህነቱን ተቋምና የአገሪቱን ሰማይ ክፉኛ ካደፈረሰው ሰንብቷል፣ ከራርሟልም፡፡
እውነተኛ የኾኑ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች፣ መንፈሳዊ መሪዎች፣ አገልጋዮችና ምእመናንም፣ አምላክ ሆይ ዝምታህ እስከ መቼ ነው?!፣ በቅዱስ መቅደስህ አደባባይ በትእቢትና በድፍረት እየተንጎማለሉ መሠውያህን በድሆች ዕንባና ደም የሞሉ ክፉዎችን የምትታገሳቸው እስከ መቼ ነው?!፣ በአፍቅሮተ ንዋይ አቅላቸውን የሳቱ፣ በክቡር ደምህ በዋጃኻቸው በጎችህ/በመንጋዎችህ ላይ በዋጋ የሚደራደሩ ይሁዳዎች- ምንደኞችና ነጋዴዎች ላይ የተግሣጽህ፣ የቁጣህ ጅራፍህ መቼ ነው የሚነሳው?!፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በዘርና በጎሳ የሚለያዩና የሚከፋፍሉ ዘረኞችና ጎጠኞችስ መቼ ነው ክፉ ዘራቸው የሚመክነው?!
የወንጌልን እውነት ቃል የሚሸቃቅጡ፣ መንፈሳዊ ሕይወትንና ስኬትን በግፍ በተከማቸ የዓመፃ ገንዘብና በዓለማዊ ሀብት የሚለኩ፣ የእግዚአብሔርን ስጦታ እንደ ስምኦን መሰሪ በገንዘብ ገዝተው በመቸርቸር ሀብትና ዝናቸውን ሰማይ ለማድረስ ዓውደ ምሕረቱን ያረከሱ አስመሳይ ነጋዴዎችና ምንደኞችስ ስለምን ቤትህን አጣበቡት?!፣ በቅድስናህ መቅደስ ላይ የሚዘባበቱ ፌዘኞችስ እስከ መቼ ሕዝብህን በሽንገላ ቃል ያባብሉታል፣ በክፉ ሥራቸውስ ያሰጨንቁታል፣ ያሰቃዩታል፣ ያስለቅሱታል?!
ስለ ሕዝብ መከራና ሰቆቃ፣ በየቀኑ እየፈራረሱ ስላሉ በክቡር ደምህ ስለዋጃኻቸው መቅደሶችህ/ሕዝበ ክርስቲያን ግድ የሚለውና በፈረሰው ቅጥር በኩል የሚቆም ነቢይ ኢሳይያስ ወዴት ይገኝ ይሆን?!፣ በመቅደስህ አጥር ስር ስለወደቁ የምድሪቱ ጎስቋሎችና መፃጉዎች፣ በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ በቤተ መቅደስ ደጃፍ ስለሚያነቡ የዋኃን ሕፃናትና እናቶቻቸውስ ማን ነው ግድ የሚለው?!፣ ሕዝብህ በየቀኑ እየፈረሰ፣ እየተናደ ባለበት፣ የአንተን ቤት በዕብነ በረድና በከበሩ ድንጋዮች አንሠራለን፣ እነገነባለን የሚሉ ግብዞችንና ሙሰኞችንስ የሚገሥጻቸው ማን ይሆን?!
ነገሥታትንና መሪዎችን በአደባባይ የሚገጥሙ፣ ስለ ክፋታቸው፣ ኃጢአታቸውና በደላቸው ፊት ለፊት የሚገሥጹ፣ ስለ እውነትና ፍትሕ የሚቆሙ መንፈሳዊ ዐርበኛ የኾኑ ባህታውያን ዮሐንሶች ወዴት አሉ?!፣ ሕዝብን ከአስጨናቂው የፈረዖን አገዛዝ ነፃ የሚያወጡ፣ በሕዝባቸውና በወገናቸው ፍቅር የነደዱ የዘመናችን ሙሴዎችስ አድራሻቸው ወዴየት ነው?!፣ እንደ ነቢዩ ኤርምያስ ዕንባቸውን እያፈሰሱ ‹‹አቤቱ የኾነብንን አስብ፣ ስለ ቅዱስ ስምህ ስትልም ዘመናችን አድስ!›› የሚሉ ኤርምያሶችን ከወዴት እናገኝ ይሆን በማለት ብዙዎች በተማፅኖ ዕንባቸውን እንደ ራሄል ወደ ጸባዖት፣ ወደ አርያም እየረጩት ነው፡፡
ምድሪቱን በከደነው በዚህ ሁሉ ዋይታ፣ ጩኸትና ሰቆቃ መካከል እጅግ ወደ ተከበረው መንፈሳዊ መንበር፣ ሥልጣንና ኃላፊነት የመጡት ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ በሹመታቸው ማግሥት ሙሰኝነትንና ጎሰኝነትን አልታገሥም፡፡ ይህ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፣ የልጆቻችን ብርቱ ጩኸትና ዋይታ ወደ ጆሮዬ ደርሷል እናም ጊዜው የለውጥ ነው፡፡ ከቅዱስ ሲኖዶስ፣ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች፣ መንፈሳዊ አገልጋዮችና ልጆቻችን ጋር በመሆን ለለውጥ እንሠራለን፣ እንደክማለን በማለት የብዙዎችን ልብና ስሜት ከፍ አደርገውት ነበር፡፡ በዚሁ መንፈሳዊ ቆራጥነትና ትጋትም የተወሰዱ የብዙዎችን ልብ በተስፋና በሐሤት የሞሉ አንዳንድ የለውጥ ዕርምጃዎችም ነበሩ ማለት ይቻል ይመስለኛል፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ ቅዱስ ፓትርያርኩ በቤተ ክርስቲያኒቱ የተንሰራፋውን የጎጠኝነትና የሙሰኝነት ችግሮች መኖራቸውን አምነው መቀበላቸው አንድ የለውጥ ዕርምጃ ነው ማለት የሚቻል ይመስለኛል፡፡ ‹‹በቅጡ ተለይቶ የታወቀ ችግር በከፊል እንደተፈታ ይቆጠራል፡፡›› እንዲሉ፡፡ ሲቀጥልም ፓትርያርኩ እነዚህ ለበርካታ ዓመታት ሲንከባለሉ የቆዩ ችግሮችን በትክክል ለይቶ ከማስቀመጥና ባለፈም ተግባራዊ ዕርምጃዎችን በመውሰድ የለውጥ ዕርምጃው በአምላካችን ረዳትነት ፍሬ እንዲያፈራ እናደርጋለን በማለት እንቅስቃሴ መጀመራቸው ለብዙዎች ብሩሕ የለውጥ ተስፋን የፈነጠቀ ነበር ማለት ይቻላል፡፡
ለአብነትም ያህል ፓትርያርኩና ቅዱስ ሲኖዶሱ በበዓለ ሲመትና በሌሎች ክብረ በዓላት ሰበብ የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪና የተንዛዛ ድግስና ውዳሴዎች እንዲቀሩ ማድረጋቸው፣ በድግስ ሰበብና በበዓላት ሽርጉድ ኪሳቸውን የሚያደልቡ ሙሰኞችን በሩ እንዲዘጋባቸው አድርጓል፡፡ በዚህም በውድ ስጦታዎችና ገጸ በረከቶች ሰበብ፣ እጅ የመጠመዘዝ ያህል ድብቅ አጀንዳቸውንና ፍላጎታቸውን ለማስፈጸም የሚተጉና የሚሯሯጡ አስመሳዮችና ሙሰኞችም ቀኑ እንዲጨልምባቸው ኾኗል፡፡
ሌላውና በተለይም በግንባር ቀደምትነት ሊጠቀስ የሚገባው የለውጥ እንቅስቃሴ ደግሞ በቤተ ክህነቱ አስተዳደር ሥራ ውስጥ ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለበት፣ መንፈሳዊ ትጋት፣ በጎነትና ቅንነት የሚንጸባረቅበት ሙያዊ/ፕሮፌሽናል አሠራር እንዲኖርና ለማድረግ ከመነጋገር አንስቶ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ልጆችና ምሁራን የተሳተፉበት ‹‹የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መዋቅር አደረጃጀትና የአሠራር መመሪያ ጥናት›› ሰነድ ቀርቦ ሰፋ ያለ ተከታታይ ውይይቶች የተደረገበት የዛን ሰሞኑ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ የቤተ ክህነቱ የአስተዳደር ሠራተኞችና መንፈሳዊ አባቶች የተሳተፉበት ጉባኤ በዋናነት የሚጠቀስ ነው፡፡
ይህን የለውጥ ትግበራ ጥናት ሰነድን ያዘጋጀው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶችና ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ነው፡፡ ይህ ዳጎስ ያለ ጥናትም በቁጥር ጥቂት የማይባሉ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች የኾኑ ምሁራንና ባለሙያዎች የተሳተፉበትና በገንዘብ ሲሰላም ቤተ ክርስቲያኒቱን በመቶ ሺኅዎች የሚገመት ወጪን ከማውጣት የታደጋት በብዙ ድካምና በብርቱ ጥንቃቄ የተዘጋጀ የጥናት ሰነድ እንደሆነ ነው አብዝቶ የተነገረለት፡፡
በዚህ የጥናት ሰነድ ላይም በየደረጃው ተከታታይ የኾኑና ውጤታማ ነበሩ ሊባሉ የሚችሉ ውይይቶች ተደርጎባቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ በጉባኤው ላይ ይህን የመዋቅር አደረጃጀትና የአሠራር ጥናት ሰነድ በምን መልኩ ሥራ ላይ ልናውለው እንችላለን የሚለው ላይ በተነሡ አንዳንድ ልዩነቶችና አለመግባባቶች የተነሳ የተለያዩ ቡድኖች ጎራ ለይተው የቃላት ጦር ሲማዘዙ፣ ሲጠዛጠዙ ታዝበናል፡፡ አሁንም የቃላት ጦርነቱ፣ መወራረፉና መጎነታተሉ እንደቀጠለ ነው፡፡ በአንፃሩም ችግሩንና ቀውሱን ከቤተ ክህነቱ ክልል በማውጣት በስውርም ኾነ በግልጽ እየታየ ያለ ሌላ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መሠረት ያለው ጠንካራ ግፊት እንዳለ የሚከራከሩ ድምፆች ደግሞ እዚህም እዛም እየተሰሙ ናቸው፡፡
ለቤተ ክርስቲያኒቱ የሚቆረቆሩ፣ በአገር ውስጥና በውጭ አገራት ባሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች የተማሩ ምሁራንን በሥሩ አሳባስቦ የያዘው ማህበረ ቅዱሳን ለዚህ የለውጥ ዕርምጃ የበኩሉን ዕገዛና ጥረት ለማድረግ ደፋ ቀና ቢልም፣ ማኅበሩ ያቀረበው የዳጎሰ የጥናት ሰነድ ሁሉንም የቤተ ክርስቲያኒቱን መሪዎችና አባቶች ባስማማ መልኩ ተቀባይነት አግኝቶ የለውጥ ትግበራውን ዕውን ለማድረግ ዕንቅፋት እንደገጠመው ግን በግልጽ እየተስተዋለ ነው፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ይህ የጥናት ሰነዱ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ተዛማጅ የኾኑ እንቅስቃሴዎቹም ከሰሞኑን እክል እንደገጠማቸው ሰምተናል፣ ታዝበናልም፡፡ ለአብነትም የአብነት መምህራንን በተመለከተ የጠራው አገር አቀፍ ጉባኤ መታገዱ የሰሞኑን በርካታዎችን ያሳዘነ ዜና ሆነ ማለፉን ልብ ይሏል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ቅዱስ ፓትርያርኩ ከሰሞኑን፣ ‹‹ቤተ ክርስቲያን በባይሎጂና በኬምስትሪ ምሩቃን አትመራም፡፡›› የሚለው መረርና ከረር ያለ ውስጠ ወይራ ንግግራቸው በማኅበሩ ማንነትና አቋም ላይ ያነጣጠረና ጥርጣሬያቸውንም ገሃድ ያወጣ ንግግር እንደሆነ ነው ብዙዎች ሲናገሩ የተደመጡት፡፡
የኾኖ ኾኖ ፓትርያርኩ በአደባባይ ያወጁትንና ቃል የገቡለትን ቤተ ክህነቱን ተቋም ከሙሰኞችና ከጎጠኞች እናጻዳለን ዘመቻቸውም ኾነ ለዚሁ የለውጥ ዘመቻ ያግዛል በሚል በማኅበረ ቅዱሳን ያቀረበው የጥናት ሰነድ የመጨረሻው ዕጣ ፈንታ ምን ይኾናል የሚለውን በእርግጠኝነት ለመናገር ግን አሁንም በትዕግሥት መጠበቅ የሚያስፈልግ ነው የሚሉ በርካታ ታዛቢዎች አልጠፉም፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የቤተ ክህነቱ ተቋም ትልቁና ዋንኛ ችግሩ የሚጀምረው ከላይ ከመንፈሳዊ መሪዎቹ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች አካባቢ መንፈሳዊ ሕይወትና መንፈሳዊ ቆራጥነት/ቅንዓት መጥፋቱ በቤተ ክህነቱ ተቋም ለተከሰተው የዚህ ሁሉ ምስቅልቅልና ቀውስ ዋንኛው ምክንያት እንደኾነ አድርገው ያቀርባሉ፡፡ በከፋ የሞራል ውድቀትና ዝቅጠት ውስጠ የተዘፈቁ፣ ምድራዊ ሀብትና ዝና የሚያንኾልላቸው፣ የለየላቸው ሙሰኞችና ጎሰኞች ከላይ እስከ ታች በተሰገሰጉበት የቤተ ክህነቱ ተቋም ውስጥ ለውጥን ለማምጣት መንገዱ አልጋ በአልጋ ይኾናል ተብሎ አይታሰብም፣ አይጠበቅምም፡፡
ላለፉት በርካታ ዓመታት ሲንከባለል የቆየ ይህ የተወሳሰበው የቤተ ክህነቱ ተቋም ችግሮች በአንድ ጀምበር ይፈታሉ ብሎ ማሰብም የዋኽነት ነው፡፡ እናም ለውጡን ዕውን ለማድረግ ከሚያስፈልገው ትዕግሥትና ቁርጠኝነት ባሻገር የክርስትና ሃይማኖት ዓምድና መሠረት የኾኑት ፍቅር፣ በጎ ሕሊና፣ ቅንነትና ታማኝት እንዲኖሩ የግድ ይላል፡፡ መሰሪነት፣ አድር ባይነት፣ አጎብዳጅነትና ግብዝነት በነገሡበትና መንፈሳዊነት ፈፅሞ እየተሰደደበት ባለበት ተቋም ውስጥ ለቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ መሪዎችና አባቶች ፍቅርና ኅብረት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ህልውና፣ የመንፈስ አንድነትና ሰላም ቀዳሚና ዋና አጀንዳ ሊኾን በተገባው ነበር፡፡
ከሁሉም በፊት ፍቅርንና መንፈሳዊ አንድነትን ለማምጣት ፈቃድም ኾነ አቅም ያነሰው የቤተ ክህነቱ ተቋም ጋሪውን ከፈረሱ በማስቀደም ጉልበቱንና አቅሙን በከንቱ እያባከነ ነው በማለት የሚተቹ ብዙዎች ናቸው፡፡ የቤተ ክህነቱ ተቋምም ኾነ መሪዎች በእውነትም ሊያሳስባቸውና ሊያስጨንቃቸው የሚገባው ቀዳሚው ጉዳይ የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ አንድነትና ሰላም መሆን ነበረበት፡፡ ይህ የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ መሪዎችና አባቶች ወይም የቤተ ክህነቱ ተቋም ወሳኝና ቀዳሚ አጀንዳ የአንድ ሰሞን ብቻ ወሬና ግርግር ኾኖ ማለፉና አሁን አሁን ደግሞ ከእነ መፈጠሩም የመረሳቱ ነገር ለመኾኑ መቅደም ያለበት የትኛው ነው ‹‹ሰላምና አንድነት ወይስ …›› የሚል ጥያቄን በተደጋጋሚ እያስነሳ ነው፡፡
ይህ የቤተ ክርስቲያኒቱ የአንድነትና የሰላም ጉዳይ የሚያሳስባቸው በርካታዎችም የፓትርያርኩም ኾነ የቤተ ክህነቱ ተቋም የለውጥ እንቅስቃሴ የቤቱ መሠረት ተነቃንቆ እያለ ጣርያውና ግድግዳው እንዳይፈረስ ከሚታገል የዋኽ ሰው ጋር በማመሳሰል የሚያቀርቡ ታዛቢዎች አልጠፉም፡፡
በቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ ኾኖ በማያውቅ ለሦስት ተከፍላ፣ የኢትዮጵያ ሲኖዶስ፣ ሕጋዊው ሲኖዶስ፣ ገለልተኛ በሚል የተለያዩ፣ የተከፋፈሉና ተገለባባጭና አድር ባይ የኾኑ ፖለቲከኞች እንደሻቸው የሚጠመዙዟቸው አባቶች ልዩነታቸውን በሰላም ፈተው ወደ አንድነት መምጣት እስካልፈቀዱ ድረስ፣ ለቤተ ክህነቱ የምንመኘው እውነተኛውና ተግባራዊው ለውጥ ህልም ነው ሲሉ አጥብቀው ይከራከራሉ፡፡ ዛሬ ከዳር እስከ ዳር መነጋገሪያ የኾነው ሙሰኝነትም ኾነ ጎጠኝነት የቤተ ክህነቱ ለገባበት ቀውስና የሞራል ውድቀት አንድ ወይም ጥቂቱ መገለጫ እንጂ የቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረታዊ ችግር ጥልቅ፣ የተወሳሰበና ዕድሜ ጠገብ ነው፡፡ መፍትሔውም ፍቅር፣ አንድነትና ሰላም ግድ የሚላቸው፣ ለእግዚአብሔርና ለቤቱ መንፈሳዊ ቅንአት ያላቸው መንፈሳዊ መሪዎች እንዲኖሩና እንዲበዙ መጸለይና መሥራት ነው፡፡  
የፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ ሙሰኞችንና ጎጠኞችን የማጥራት ዘመቻው ፍሬያማ እንዲኾንና ለዚሁ የለውጥ ዘመቻ ትግበራም ያግዛል ተብሎ በቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች/ምሁራን የቀረበው የጥናት ሰነድ ተግባራዊ ውጤት እንዲያመጣ ከተፈለገ መቅደም ያለበት አማራጭ ይህ ነው ሲሉም ይናገራሉ፡፡ ስለሆነም ይላሉ እነዚህ አስተያየት ሰጪዎች፣ የቤተ ክህነቱ ተቋም ማስቀደም ያለበት ዋነኛው ዕርምጃ መሆን ያለበት መንፈሳዊነትን ያስቀደሙ የእግዚአብሔርና የቤቱ ቅናት የሚያቃጥላቸው፣ መመሪያቸውና መለያቸው ፍቅር የኾነ፣ ሰላምንና ዕርቅን የሚሰብኩ፣ ለእውነትና ለፍትሕ የቆሙና የሚከራከሩ መሪዎችና አባቶች እንዲኖሩና እንዲበዙ መሥራትና መትጋት የግድ ይላል በማለት አስተያየታቸውን ይሰነዝራሉ፡፡
እነዚህ ትችቶች፣ መከራከሪያዎችና አስተያየቶች እንዳሉ ኾነው ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የጀመሩት የቤተ ክህነቱን ተቋም ከሙሰኞችና ከጎጠኞች የማፅዳት ዘመቻቸውን አጥብቀው እንዲገፉበት የሚመኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች፣ አገልጋዮችና ምእመናን ድምፅ አሁንም ጎልቶ እየተሰማ ነው፡፡ በመጨረሻ አንድ ነገር ለማለት እወዳለኹ፡፡ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በፕትርክና ዘመናቸው የተከፋፈለችውን ቤተ ክርስቲያን አንድነት በማስጠበቅ፣ የቤተ ክህነቱን ተቋም ከሙሰኞች፣ ከአስመሳዮችና ከጎጠኞች የፀዳች በማድረግ አዲስ ታሪክ ያስመዘግቡ ዘንድ ልባዊ ምኞቴ ነው፡፡

Monday, 24 March 2014

‹‹ፓትርያርኩ ይደግፉናል መንግሥት ያግዘናል›› ያሉ የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ተቃዋሚ አማሳኞች ማኅበረ ቅዱሳን ጠቅላላ ሀብትና ንብረቱ ታግዶ በፀረ ሽብር ሕጉ መሠረት እርምትና ርምጃ እንዲወሰድበት ጠየቁ



  • በሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ያልታወቀውና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት የአዳራሽ ፈቃድ የተነፈጋቸው አማሳኞቹ ትላንት መጋቢት ፲፫ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ረፋድ ላይ ተጀምሮ እስከ እኩለ ቀን በዘለቀው ስብሰባቸው፣ በሌላቸው ሕጋዊነትና ውክልና ‹‹የአዲስ አበባ አገልጋዮች ማኅበር›› መሥርተው ማኅበረ ቅዱሳንን መቃወማቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡
  • ‹ውሳኔያቸውና የአቋም መግለጫቸው› ተቀባይነት አግኝቶ ተፈጻሚ ካልኾነና የማስወጣት ርምጃ ከተወሰደባቸው የራሳቸውን ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ተቃውሟቸውን ለማጠናከር የዛቱ ተሰብሳቢዎችም አሉባቸው! - ‹‹ከዚኽ እንኳ ቢያስወጡን መንግሥታችን ቸር ነው፤ ቦታ ተቀብለን የራሳችንን ቤተ ክርስቲያን ሠርተን ለምን አንቀጥልም?››
  • የአቋም መግለጫቸውን በተለያዩ መሸኛዎች አዘጋጅተው ከሚያደርሷቸው አካላት መካከል÷ የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት፣ የቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ የመ/ፓ/ጠ/ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና ለየብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ የሚገኘበት ሲኾን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት፣ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይገኙበታል፡፡
  • ፓትርያርኩየተዘጋባቸው አዳራሽ እንዲከፈትላቸው ከማዘዝ ጀምሮ በተቃውሟቸው ሳቢያ ከሥራቸው እንደማይፈናቀሉና መፍራት እንደሌለባቸው በመግለጽ አበረታተውናል ያለው ኃይሌ ኣብርሃ፣ ‹‹ቤተ ክርስቲያን በፊዚክስና ኬሚስትሪ አትመራም›› በማለት በአንድ ስብሰባ ላይ መናገራቸው እነርሱን ለማበረታታት መኾኑን በመጥቀስ አወድሶላቸዋል፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅም በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ደብዳቤ ለመጻፍ በመድፈራቸው ‹‹ልናደንቃቸው ይገባል›› ብሏል፤ ደብዳቤዎቹም በንባብ ተሰምተዋል፡፡
*   *   *
  • ማኅበረ ቅዱሳን ‹‹በሀገር አቀፍ ደረጃ ንጹሕ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን ለአድማ በማነሣሣት በሀገርና በቤተ ክርስቲያን ላይ ሁከትና ሽብር እንዲፈጠር ሰላም እንዲደፈርስ ያደርጋል›› ያሉትና የደኅንነቱ ኃይል በእጃቸው እንደኾነ የተናገሩት አማሳኞቹ እርስ በርሱ በሚምታታውና በሚገባ ባልተደራጀው መግለጫቸው፣ ‹‹መንግሥት ለሽብር ተግባር እንደሚውል ዐውቆ በፀረ ሽብር ሕጉ ታሳቢነት ማኅበሩ በገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ስም ከምእመናን በሚሰበስበው ዓሥራት በኩራት ያፈራውን ጠቅላላ ሀብትና ንብረት ቁጥጥር በማድረግ የተለመደ እገዛው እንዳይለየን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፤›› ብለዋል፡፡
  • አማሳኞቹ በቅ/ሲኖዶስ በኩል ለሚመለከታቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እንዲተላለፍላቸው የጠየቁት የጠቅላላ ሀብትና ንብረት እገዳ ደብዳቤ ደግሞ÷ ት/ቤቶች፣ ሕንፃዎች፣ የንግድ ተቋማት፣ ግብረ ሠናይ ድርጅቶች፣ የንዋያተ ቅድሳት ማምረቻዎችና ማከፋፈያዎች፣ የአክስዮን ተቋማትና የባንክ አካውንቶች የሚመለከት ነው፡፡ አማሳኞቹ ከቀደመው ንግግራቸው ጋራ በሚጋጭ አኳኋን እንደተናገሩት፣ የማኅበረ ቅዱሳን ሀብቶችና ንብረቶች ምንጭ አይታወቅም፤ ባለቤትም የላቸውም፤ ኦዲት ተደርገውም አያውቁም፤ ዓመታዊ ሪፖርት አቅርቦ አያውቅም፤ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሞዴልም ተገልግሎ አያውቅም፡፡
  • በቅ/ሲኖዶስ ጸድቆ በተሰጠው መተዳደርያ ደንብ መሠረት ለዓላማው ተግባራዊነት በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸውና በጉልበታቸው የሚራዱ አባላት ያሉት ማኅበረ ቅዱሳን እንደየገቢያቸው መጠን በየወሩ ቢያንስ ከመቶ አንድ እጅ(1%) የአባልነት አስተዋፅኦ የሚያደርጉ አባላት አሉት፤ ለማኅበሩ አገልግሎት አስፈላጊ የኾኑ አዳዲስ የልማትና ተራድኦ ተቋማት እንዲቋቋሙ ወይም እንዲዘጉ የመወሰን ተግባርና ሓላፊነት ያለው የሥራ አመራር ጉባኤ አለው፡፡
  • ማኅበረ ቅዱሳን የአገልግሎት ዕቅድ ዝግጅቱንና የአፈጻጸም አጠቃላይ ዘገባውን በየስድስት ወሩ አንድ ጊዜ ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ያቀርባል፤ በዘመናዊ የፋይናንስ አሠራርና የንብረት አስተዳደር መመሪያ የያዘውን የአባላቱን ሀብት አጠቃቀም በተመሰከረለት የውጭ ኦዲተር ያስመረምራል፤ የኦዲት ሪፖርቱንም በየዓመቱ ያቀርባል፤ መመሪያም ይቀበላል፡፡
  • የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የነጠላ ሒሳብ ሥርዓት አዝማናት የተሻገሩትና ከማንኛውም የአካውንቲንግ ሶፍትዌሮች ጋራ የማይጣጣም ከሊትሬቸሩም የጠፋ ነው፤ ለቁጥጥር የሚያመች የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር መመሪያ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አልተተከለም፤ ሞዴላሞዴሎቹ ምስጢራዊ ኅትመት (security features) የሌላቸው፣ የሀብት፣ ንብረትና ዕዳ መጠን በተመለከተ ተፈላጊውን መረጃ የማይሰጡ በምትኩ ለአማሳኞች ማጭበርበርያ አመቺ ኾነው እንዳሉ በተለያዩ መድረኮች ሲገለጽ የቆየ ነው፡፡
  • ከዚኽ አኳያ የማኅበሩ ጥያቄ ቤተ ክህነቱ አይቆጣጠረኝ ሳይኾን ለቁጥጥር አመች(audit-able) የኾነ ነባራዊ ኹኔታ(ለምሳሌ፡- ጠቅ/ቤተ ክህነቱ ኅትመቱን የፈቀደውና ቁጥሩን የመዘገበው፣ ከሒሳብ ሥርዐቱ ጋራ የሚስማሙ ደረሰኞች ኅትመት) የመፍጠር ጥያቄ እንደኾነ በየጊዜው እንደሰጣቸው የሚታወቁ ገለጻዎች ሰሚ ጆሮ አስተዋይ አእምሮ ቢያገኙ መልካም ነው፡፡
  • በስተቀር የማኅበሩ አባላት በድካማቸው ያፈሩትን ሀብት ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡ እንጂ የማይቀበሉ (አማሳኞቹ እንዳሉት የዓለም የኑሮ ውድነት አባሯቸውና መንግሥት የሚከፍላቸው ደመወዝ አላረካ ብሏቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሰርገው የገቡ) እንዳልኾኑ፣ ማኅበረ ቅዱሳንም በማዕከላዊ የቤተ ክህነት መዋቅር ውስጥ ኾኖ የድርሻውን በመወጣት ላይ የሚገኘው፣ በአባቶች የታመነበትን ክፍተት የመሙላት አገልግሎቱን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ለመከታተል እንደኾነና ይህን የአገልግሎት ድርሻውን ለመወጣት በበጎ ፈቃድ የተሰበሰቡ አባላቱ ማኅበር በመኾኑ ለሥራው የሚመደብለት በጀት ይኹን ከእርሱም የሚጠበቅ የገቢ ፈሰስ እንደሌለ ሊያዝ ይገባል፡፡
*   *   *
  • መንግሥት ባጋመስነው የ፳፻፮ ዓ.ም. በጀት ዓመት በትኩረት እረባረብበታለኹ በሚል በያዘውና በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር አስተባባሪነት እንደሚመራ በገለጸው የፀረ አክራሪነት ዕቅድ፣ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት በማኅበራት ጥላ ሥር ይካሔዳል ያለውን ‹የአክራሪነት አመለካከትና ተግባራዊ እንቅስቃሴ› የምዝገባ፣ የክትትልና የመረጃ ሥርዐቱን አጠናክሮ የፋይናንስ ዝውውራቸውንና አጠቃቀማቸውን ግልጽነት በማረጋገጥ እንደሚፈተሽ አስፍሯል፡፡
  • የፀረ አክራሪነት ትግል አስተዳደራዊና የጸጥታ ሥራ ብቻ ሳይኾን ቁልፍ ፖሊቲካዊ ትግልም እንደኾነ የሚገልጸው መንግሥት፣ ፖሊቲካዊ ትግሉ የሴኩላር መንግሥትን ሚና ጠብቆ በንቃት ሊመራ እንደሚገባውና ከዚኽ አኳያ በገዛ መዋቅሩ ውስጥ መሽገው የትግሉን አቅጣጫ የሚያስቱ፣ የሚያደበዝዙና ሽፋን የሚሰጡ፣ የሕዝብን እይታ የሚያዛቡና ለተለያዩ ጥርጣሬዎች መንገድ የሚከፍቱ ያላቸው የመንግሥትና የድርጅት አካላትና አባላት ቁመና መፈተሽ እንደሚገባው ያሳስባል፡፡
  • እናስ? የቤተ ክርስቲያናችን ማኅበራት አፈራረጅ ይቆየንና ከእነ ንቡረ እድ ኤልያስ ጋራ ጥብቅ ቁርኝት ፈጥረው በመንቀሳቀስ የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ጥናቱ የሚሰናከልበትን አሻጥር እየሠሩ የሚገኙት አማሳኞቹ እነ ኃይሌ ኣብርሃ ‹‹በእጃችን ናቸው›› ያሏቸው ‹‹የቤተ ክህነት ደኅንነቶች›› የትግሉ አያያዝና የቁመና ጥራት መፈተሽ አይኖርበትምን?
*   *   *
  • አማሳኞቹ ተጽዕኖ ለመፍጠር አልመው እንዳስወሩት፣ ፓትርያርኩ በስብሰባው ላይ ባይገኙም ቅዱስነታቸው የቅ/ሲኖዶሱን ጽ/ቤት እና የሌሎች ብፁዓን አባቶችን ምክር ወደ ጎን በማለት ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አዳራሽ ሓላፊ ቀጥተኛ የቃል ትእዛዝ በማውረድ ለአማሳኝ ተቃዋሚዎች ቁልፍ እንዲሰጥ በማድረግ ነበር ስብሰባው በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የስብሰባ አዳራሽ የተካሔደው፡፡
the corrupt parish head haile abreha
በልማታዊነት ስምና በእልቅና ካባ በሚልዮኖች የተመዘበሩባቸው አብያተ ክርስቲያናት ሀብት (ከደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ብቻ 13.3 ሚልዮን ብር መኾኑ ተጠቁሟል) ፣ የግል ሚኒባስ፣ የግል መኖሪያ ቤቶች ይዞታና ድልብ የባንክ ተቀማጭኽ ጉዳይ ይቆየንና በ1.3 ሚልዮን ብር የተገዛውና በወር 70‚000 ብር የኪራይ ገቢ የሚገኝበት ሲኖ ትራክ ገልባጭ መኪና ባለቤትነትኽ ምንጩ ምን ይኾን?
  • እነኃይሌ ኣብርሃ ባስተባበሩትና በዘካርያስ ሐዲስ በተመራው ቅጥፈትና ያላዋቂነት እብሪት (arrogance of ignorance) በተሞላበት ስብሰባ ከተገኙት በደግ ግምት 200 ያኽል በሚኾኑ ተሰብሳቢዎች መካከል ኹለቱን ቀንደኛ አማሳኞች ጨምሮ አስተዳዳሪዎቹ ስምንት ብቻ ናቸው፡፡
  • ከ169 በላይ በኾኑ የሀገረ ስብከቱ ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት ካሉ 14 ሺሕ ያኽል ሠራተኞች መካከል አማሳኞቹ በጎጥና ጥቅም ከሳቧቸውና በሥልጣናቸው ካስፈራሯቸው በቀር የተገኙት አስተዳዳሪዎችና አጠቃላይ ተሳታፊዎች ቁጥር ማነስ አማሳኞቹን ክፉኛ አሳስቧቸዋል፡፡
  • ኹኔታውም አንዱ ተናጋሪ ‹‹ሴት ያወጣውን ሕግ አንቀበልም›› እንዳለው ሳይኾን የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በሰጠው አቅጣጫ መሠረት ትግበራው እንዲፋጠን እየተጠየቀ ያለውና 96 በመቶ የሀገረ ስብከቱን ማኅበረ ካህናት፣ ማኅበረ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች የተረጋገጠ ድጋፍ ያስገኘው የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ጥናት ሰፋኒነትና ኃያልነት የተመሰከረበት ኾኗል፡፡
  • የሕግና የሥርዓት ምንጭ የኾነችውን ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የሚመራው ቤተ ክህነታችን ባለቤት የሌለው ይመስል የግለሰቦችና ቡድኖች መፈንጫ መምሰሉ በእጅጉ ያሳዝናል፡፡ የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር ተሻሽሎ ማየት የማይሹ አማሳኞች መንበረ ፓትርያርኩን ከበው የፓትርያርኩን የለውጥ ተነሣሽነት ሲያግቱት ማየቱም ያስቆጣል፡፡ የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔዎች የማስፈጸም ሓላፊነት ያለበት ቋሚ ሲኖዶስና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአጠቃላይ እየኾነ ያለውን ነገር በዝምታ ሊያዩት አይገባም፡፡ በሃይማኖት ተቋማት ለልዩነት፣ ግጭትና ቅስቀሳ ምቹ ኹኔታዎች እንዳይፈጠሩ እሠራለኹ የሚለው መንግሥትም ነገሩን በጥንቃቄ ሊያጤነው ያስፈልጋል፡፡

ጊዜ ይፈጅ ይኾናል እንጂ ለውጡ አይቀሬ ነው



(አዲስ ጉዳይ፤ ቅጽ ፰ ቁጥር ፻፰፤ መጋቢት ፳፻፮ ዓ.ም.)
  • ሃይማኖት ከአስተዳደሩ የተለየ በጣም ጥልቅ ነገር ነው፡፡ ሃይማኖት ማለት ከአንድ ግለሰብ ኾነ ከጥቂት ሰዎች አመራር የተለየና የራሱ ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት፣ ባህልና ሥርዓት ያለው መኾኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
  • በሥነ ምግባር ደረጃ እኔን ጨምሮ ኹሉም ሰው ችግር ሊኖርብን ይችላል፡፡ ይኹንና ይኼ የሥነ ምግባር ጉዳይ ሊፈታ የሚችለው በመነጋገርና ተገቢውን ርምጃ በመውሰድ ነው፡፡ ስለ አስተዳደር ጉዳዮች ሲነሣ ነገሩ የሃይማኖት ሳይኾን የሥነ ምግባር መኾኑ መታወቅ አለበት፡፡ ስለዚኽ ለእኔ አስተዳደሩን ከሃይማኖቱ ጋራ ማቀላቀል ተገቢ አይኾንም፡፡
  • ዘመኑን ካልዋጀን ሌላው ቀርቶ የዘመኑ ትውልድ አብሮን ሊሔድ አይችልም፡፡ ትውልዱን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋራ ለማስቀጠል ከፈለግን አስተዳደራዊ ሥርዓታችንን የግድ ዘመናዊ ማድረግ አለብን፡፡ ሃይማኖት አንዴ ተሰጥቶ ያለቀ ስለኾነ የምንጨምርበት ኾነ የምንቀንስበት ነገር አይኖርም፡፡ አስተዳደራችን ግን በየጊዜው ከሚሻሻለው ዕውቀት ጋራ ተዘምዶ መሻሻል አለበት፡፡
  • የአንድ ደብር ጸሐፊ የኾነ ሰው እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ከኹለት ሺሕ ብር በማይበልጥ ደመወዝ ኹለት ሦስት መኪና፣ ኹለት የመኖሪያ ቤቶች በፍጹም ሊኖረው አይችልም፡፡ የአንድ ወር ደመወዛቸው ለመኪና ነዳጅ ወጭ የማይሸፍንላቸው አገልጋዮች መኪና እየለዋወጡ ሲይዙ በድሎት ሲኖሩ፣ የልጆችን ይኹን የራሳቸውን ወጭዎች ያለችግር ሲሸፍኑ ይኼ ነገር ከየት መጣ ያሰኛል፡፡
  • ቤተ ክርስቲያን አኹን እየተጠቀመችበት ያለው የፋይናንስ ሥርዓት ዓለም በ፲፯ኛው መ/ክ/ዘ የተወውንና የነጠላ ሒሳብ አሠራር (single entry) የሚባለውንና በሞዴል የሚሠራ የሒሳብ አሠራር ነው፡፡ በዓለም ላይ እንዲኽ ዓይነት የሒሳብ አሠራር የሚከተል ምንም ተቋም የለም፡፡
  • የነጠላ ሒሳብ አሠራር ወጪን ወጪ ይላል እንጂ ምክንያቱን አይናገርም፡፡ ስለዚኽ ወጪን ከነምክንያቱ ገቢን ከነምንጩ የሚጠቅሰው የኹለትዮሽ(ደብል) ሒሳብ አሠራር ሥርዓት የላትም፡፡ በመኾኑም ይኼን ተረድቶ የፋይናንስ ሥርዓቱን በአፋጣኝ ማዘመን ይገባል፡፡
  • ካሽ ሬጅስተር በመጠቀም እያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን ያለውን አቅም የላይኛው አስተዳደር አካል በሚገባ ለማወቅና ከፍተኛ ብክነትን ለማስወገድ ይችላል፡፡ አኹን እየጠፋ ያለውኮ ብሩ ብቻ ሳይኾን ሰነዱም ጭምር ነው፡፡ የካሽ ሬጅስተርን መረጃ ግን ማጥፋት ስለማይቻል የቁጥጥር ሥርዓትን ማጉላትና ተጠያቂነትን ማስፈን ይቻላል፡፡
  • የተጀመሩትን የለውጥ እንቅስቃሴዎች የሚቃወሙት በአስተዳደር ላይ ያሉ ጥቂት ሰዎች ናቸው፤ አስተዳደር ላይ ኾነውም ለውጡን የሚደግፉ አሉ፡፡ ምናልባት ጊዜ ይፈጅ ይኾናል እንጂ ችግሩ መፈታቱ አይቀሬ ነው፡፡
መምህር ምሐባው ዓለሙምሐባው ዓለሙ ተወልደው ያደጉት በቀድሞው አጠራር በጎጃም ክፍለ ሀገር በደጋ ዳሞት ወረዳ ሲኾን እስከ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ያለውን ትምህርታቸውን በትውልድ አካባቢያቸው ተከታትለዋል፡፡ ከዚኽ በኋላ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የከፍተኛ ትምህርታቸውን በአካውንቲንግ ዘርፍ አጠናቀዋል፡፡ በተለያዩ ተቋማት በድምሩ የ12 ዓመታት የሥራ ልምድ ያላቸው አቶ ምሐባው ዓለሙ በማስተማር፣ በኦዲተርነትና በሌሎችም ዘርፎች በተማሩበት መስክ የድርሻቸውን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡
በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ከልጅነታቸው አንሥቶ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርት በመማር ካደጉ በኋላም በሰንበት ት/ቤት እና በተለያዩ ሓላፊነቶች አገልግለዋል፡፡ በቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው ከማገልገላቸው ጋራ በተያያዘ ያላቸውን ዕውቀት መሠረት በማድረግ በተለይ በማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ላይ ልዩ ትኩረት ያደረገ ‹‹የቤተ ክርስቲያን ፈተናዎች›› በሚል ርእስ የተዘጋጀ መጽሐፍ በማሳተም በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ይስተዋላል ያሉትን በርካታ የአስተዳደር፣ የፋይናንስና የሰው ኃይል አስተዳደር ችግሮች ጠቁመዋል፡፡
ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሰፊ ትኩረት ከተቸረው የመዋቅርና የአስተዳደራዊ ለውጥ እንቅስቃሴ ጋራ በተያያዘ በቅድስት ማርያም ዩኒቨርስቲ የአካውንቲንግ መምህር ከኾኑትና በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሦስተኛ ዓመት ተማሪ ከኾኑት አቶ ምሐባው ዓለሙ ጋራ ቀጣዩን ቆይታ አድርገናል፡፡
*                                *                               *
አዲስ ጉዳይ፡- ‹‹የቤተ ክርስቲያን ፈተናዎች›› የሚለውን መጽሐፍ ለምን አዘጋጁት?
በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ ገብተኽ ስትመለከተው የምታየው እውነት አለ፡፡ እኔም የሰበካ ጉባኤ ተመራጭ ኾኜ ስሠራ ከዚያ በፊት በፍጹም በቤተ ክርስቲያን ይደረጋል ብዬ የማላስበውን ነገር ታዝቤያለኹ፡፡ እኔ አስቀድሞ በነበረኝ ግምትና እምነት የሚዋሽ አንድ የቤተ ክርስቲያን አባት አለ ብዬ በፍጹም አላምንም ነበር፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ገቢ የሚሰርቅ አገልጋይ ይኖራል ብዬ በጭራሽ አላምንም ነበር፡፡ ይኹን እንጂ በአገልግሎት ላይ ሳለኹ ከዚኽ እምነቴ ጋራ የሚቃረኑ ብዙ ነገሮች ሲፈጸሙ ተመለከትኹ፡፡ በወቅቱ ያጋጠሙኝ በጣም የሚያበሳጩ ነገሮች ስለነበሩ አንዳንዴ እንዲያውም መተኛት ኹሉ ያቅተኛል፡፡
በነገራችን ላይ ጥፋቱ ከፍተኛ ነው፡፡ ይኹንና የዚኽ ጥፋት ተካፋዮች ጥቂት ናቸው፡፡ ድርጊቱ ግን የብዙ አባቶችን ስም የሚያጠፋ፣ ለቤተ ክርስቲያናችንም ከባድ ችግርን የሚያመጣ በመኾኑ በተለይ ያሉትን ችግሮች የሚፈጽሙት ጥቂቶች እንጂ ብዙዎች ባለመኾናቸው ይኼ ነገር ለውጥ ያስፈልገዋል፤ የግድ መጽሐፍ መዘጋጀት አለበት ከሚል ውሳኔ ላይ በመድረሴ ነው መጽሐፉን ያዘጋጀኹት፡፡
አዲስ ጉዳይ፡- ከመጽሐፉ መውጣት በኋላ ያገኙት ምላሽ ምን ይመስላል?
በመጽሐፌ ዙሪያ ያገኘኹትን ምላሽ በዝርዝር መግለጹ ያስቸግራል፡፡ ይኹን እንጂ በደፈናው በአንድ በኩል ‹‹ጥሩ ነው፤ ይኼ የአንተ መጽሐፍ እንደመነሻ ኾኖ ወደፊት ለሚወሰዱት እርምቶች ማስተካከያ የሚወሰድባቸውን መንገዶች ዕድል ይፈጥራል›› በማለት ከታላላቅ አባቶች አንሥቶ የእኔን መጽሐፍ የደገፉና ያበረታቱኝ ነበሩ፡፡ ከዚኽ ተቃራኒው ደግሞ እርምቱ ሲወሰድ ጥቅማችን ይነካብናል ያሉት አካላት ግን በጣም ተቆጥተውና ተበሳጭተው ነበር፡፡
አዲስ ጉዳይ፡- መጽሐፍዎ ለምን የልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ላይ ብቻ አተኮረ?
እኔ በግሌ እንደማስበው ከኾነ እውነታው በተለይ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ተጨባጭ ጉዳይ ነው፤ ነገር ግን እንዲኽ ያለ ነገር ሲጻፍ የግድ ማስረጃ ያስፈልጋል፡፡ እኔም በእጄ ያለኝ ተጨባጭ ማስረጃ የልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን በመኾኑ ጉዳዩን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋራ ያያዝኹት ለዚኹ ነው፤ ደግሞም ጉዳዩ ሊያስከሥሥና ኾነ ተብሎ የተለያዩ ስሞች ሊያሰጥ እንደሚችል ዐውቃለኹ፡፡ በዚኽ የተነሣ ድንገት ይኼ ዓይነቱ ክሥ ቢቀርብብኝ ራሴን ነፃ ለማውጣት ይኹን ለቀረበልኝ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት የምችለው እጄ ላይ በሚገኝ ተጨባጭ ማስረጃ በመኾኑ ጉዳዩ በአንድ አጥቢያ ዙሪያ እንዲያተኩር አድርጌያለኹ፡፡
አዲስ ጉዳይ፡- በሌሎች አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትስ ችግሩ ለመኖሩ ርግጠኛ ነዎት?
በሚገባ! በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት የተለያዩ ጥናቶችን አድርጌ ነበር፡፡ ይኹን እንጂ የያዝኋቸው መረጃዎችን እንጂ ማስረጃዎቹ እጄ ስላልገቡ ነው መጽሐፉ ላይ ያልተካተቱት፡፡
አዲስ ጉዳይ፡- ማስረጃ አለኝ ባሉት አንድ አጥቢያ ላይ ማተኮርዎ ጥያቄ እንዳይነሣብዎ አድርጓል?
በርግጥ መጽሐፉ እንደወጣ ታስሬያለኹ፡፡ በይፋ ከሣሽ እኛ ነን ያሉ ሰዎች በፍጹም ራሳቸውን ግልጽ ባያደርጉም እኔ ግን ለቀናት ታስሬ ነበር፡፡ በነገራችን ላይ በእስር ቤት ረጅም ጊዜ እንዳልታሰር የኾንኩት እጄ ላይ ተጨባጭ ማስረጃ በመኖሩ የተነሣ ነው፡፡ በፖሊስ በታሰርኹ በአራተኛው ቀን ጉዳዩ የማያሳስር በመኾኑ ውጣ አሉኝ፡፡ እኔ ግን ‹‹አይ ፍ/ቤት ቀጠሮ ሰጥቶኛል፣ አልወጣም፡፡ ቀድሞስ ምን ብላችኹ አሠራችኹኝ? አኹንስ ምን ብላችኹ ትለቁኛላችኹ?›› ብዬ ጠየቅኋቸው፡፡ እነርሱ ግን የለም፣ ብትወጣ ይሻላል ብለው አንዳንድ ነገር ለማስረዳት ከሞካከሩ በኋላ የፍ/ቤት ቀጠሮ ከመድረሱ አስቀድሞ እንድወጣ አድርገዋል፡፡
አዲስ ጉዳይ፡- የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ችግር ሲነሣ ሃይማኖቱ እንደተነካ አድርገው የሚያስቡ ሰዎች አሉ፡፡ ከዚኽ ጋራ በተያይዘ የገጠምዎ ነገር አለ?
ምን አለ መሰለኽ፣ እኔ በዋናነት የጻፍኹት የአስተዳደሩን ጉዳይ የተመለከተ ነው፡፡ ይኹን እንጂ መጽሐፉን ሳያነቡ እንዲኹ በስማ በለው ተነሣስተው ደውለው ለምን እንዲኽ ታደርጋለኽ ብለው የተናገሩኝ አሉ፡፡ በርካቶች ግን እኔ የጻፍኹት ኹሉም የሚያውቀው በመኾኑ መጽሐፍኽ ለለውጥ እንደመነሻ ያገለግላል በማለት በተለያዩ መንገዶች ምስጋናቸውን ገልጸውልኛል፡፡
አዲስ ጉዳይ፡- አስተዳደሩን መውቀስ ሃይማኖቱን ከመተቸት የተለየ መኾኑን ለሰዎች በምን መንገድ ሊያስረዱ ይችላሉ?
ሃይማኖት ማለት ከኹሉ አስቀድሞ በኾነ ወቅት ወይም በአንድ አስተዳደር ብቻ የሚገለጽ አለመኾኑ መታወቅ አለበት፡፡ ሃይማኖት ከአስተዳደሩ የተለየ በጣም ጥልቅ ነገር ነው፡፡ ሃይማኖት ማለት ከአንድ ግለሰብ ኾነ ከጥቂት ሰዎች አመራር የተለየና የራሱ የኾነ ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት፣ ባህልና ሥርዓት ያለው መኾኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡ በሥነ ምግባር ደረጃ እኔን ጨምሮ ኹሉም ሰው ችግር ሊኖርብን ይችላል፡፡ ይኹንና ይኼ የሥነ ምግባር ጉዳይ ሊፈታ የሚችለው በመነጋገርና ተገቢውን ርምጃ በመውሰድ ነው፡፡ በመኾኑም ስለ አስተዳደር ጉዳዮች ሲነሣ ነገሩ የሃይማኖት ሳይኾን የሥነ ምግባር መኾኑ መታወቅ አለበት፡፡ ከዚኽ ውጭ ግን አኹን እኔ ባየኋቸው የተለያዩ ነገሮች ተካፋይ በነበሩ አባቶች ላይ ምንም ዓይነት የሃይማኖት ችግር በፍጹም አላየኹም፡፡
በርግጥ በተወሰነ ደረጃ አንዳንዶቹ ሃይማኖት አላቸው ወይም ሌሎቹን ደግሞ በርግጥ ክህነት የተቀበሉ ናቸው ወይ? በሚል ጥያቄ ያነሣኹበት ኹኔታ አለ፡፡ የኾነው ኾኖ ግን አብዛኞቹ በሃይማኖታቸው ችግር የሌለባቸው ካህናት ናቸው፤ እውነተኛ አገልጋዮችም አሉ፡፡ ይኹን እንጂ በአስተዳደሩ ላይ ተሳትፎ ያላቸው ሰዎች የሥነ ምግባር ችግር ገጥሟቸዋል፡፡ ይህን ችግር መፍታት አለብን፡፡ ይህን የሥነ ምግባር ችግር ደግሞ አንዳንዶቹ ወደውት ሳይኾን ተገደው የገቡበት ሊኾን ይችላል፡፡ የነበረው ሥርዐት እነርሱ በፈለጉት መንገድ አላስኬድ ብሏቸው ወደዚኽ መንገድ ተገደው የገቡበት ሰዎችም አሉ፡፡
ስለዚኽ ለእኔ አስተዳደሩን ከሃይማኖቱ ጋራ ማቀላቀል ተገቢ አይኾንም፡፡ በተለይ ደግሞ አንድ አባት አስተዳደር ላይ ስለተቀመጡ ብቻ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴያቸውንና የሚያስተላልፏቸውን ውሳኔዎች በሙሉ የሃይማኖቱ አካል ተደርጎ መታሰብ አይኖርበትም፡፡
አዲስ ጉዳይ፡- ‹‹ለቤተ ክርስቲያን ዘመናዊ ሥርዐት አያሻትም፡፡ የነበረው ጥንታዊ የአስተዳደር ሥርዓት መቀጠል አለበት፤›› በማለት የሚከራከሩ ሰዎች ለቤተ ክርስቲያን የሚበጃት ይኼ ብቻ ነው የሚል መከራከርያ ያቀርባሉ…
እንዲያውም ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ዘመኑን ዋጁ›› ብሎ እንደ መመሪያም እንደ ማስጠንቀቂያም የነገረው ለቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ በመኾኑም በየጊዜው የሚኾነውን ነገር በሚገባ እያጤኑ ዘመኑን መቅደም ያስፈልጋል፡፡ ከጥንት ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር፣ የሥርዓት ኾነ የብዙ ነገር ምንጭ ናት፡፡ ይኼ ነገር በርግጥ አኹን እየተዳከመ ነው፡፡ ከዚኽ ቀደም የዕውቀት ምንጭ የኾኑ ብዙ የሃይማኖት ተቋማት ነበሩ፡፡ አሁን የሉም፡፡ ፊደል ቀርፃ፣ ቀለም በጥብጣ፣ ብራና ፍቃ ብዙ ታሪክና ቅርስ ለትውልድ ያበረከተች ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ይኼ ቀድሞ በነበረበት እየኼደ አይደለም፡፡ በአስተዳደሩ ዘርፍ የነበረው ቀደምት ሥልጠና አኹን የለም፡፡ በሕጉ በኩል ይሰጡ የነበሩ ሥልጠናዎች ቀርተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የነበራት አቅም እየጠፋ ነው፡፡
በመኾኑም እስከ አኹን የነበረውን የላቀ ውጤታማ ለማድረግ ያለንን አስተዳደራዊ ሥርዐት ዘመናዊ ማድረግ፣ ከዘመኑ ጋራ እያሻሻልን እየበለጸግን መሔድ እንጂ አስተዳደራዊ ሥርዓቱ መለወጥ የለበትም የሚለው አያስኬድም፡፡ እንዲያውም ይኼን የማናደርግ ከኾነ እኛ ልንኖር አንችልም፡፡ ዘመኑን ካልዋጀን ሌላው ቀርቶ የዘመኑ ትውልድ አብሮን ሊሔድ አይችልም፡፡ ትውልዱን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋራ ለማስቀጠል ከፈለግን አስተዳደራዊ ሥርዓታችንን የግድ ዘመናዊ ማድረግ አለብን፡፡ ሃይማኖት አንዴ ተሰጥቶ ያለቀ ስለኾነ የምንጨምርበት ኾነ የምንቀንስበት ነገር አይኖርም፡፡ አስተዳደራችን ግን በየጊዜው ከሚሻሻለው ዕውቀት ጋራ ተዘምዶ መሻሻል አለበት፡፡
አዲስ ጉዳይ፡- ‹‹ቤተ ክርስቲያን የካሽ ሬጅስተር ማሽን ያለቫት ትጠቀም›› የሚለው ሐሳብ እያወዛገበ ነው…
የእኔ መጽሐፍ ለንባብ ከበቃ በኋላ አባቶች በምን መልኩ ማሻሻያ ይደረግ ብለው ጠይቁኝ፡፡ እኔም በጉዳዩ ላይ የራሴን ጥናት በማድረግ ፕሮፖዛሉን አቅርቤያለኹ፡፡ ከተጠቃሚውና ከሰርቨሩ አንጻር ያለውን ዝርዝር የመረጃ ልውውጥ ኢትዮ ቴሌኮም በአካል ተገኝቼ በማጥናት በቤተ ክርስቲያናችን ካሽ ሬጅስተር ቢገባ በምን መልኩ ማስተዳደር ይቻላል የሚለውን ገምግሜያለኹ፡፡ ከዚያ በኋላ ሐሳቡ ጎልቶ የብዙዎች መነጋገርያ ኾነ፡፡
አዲስ ጉዳይ፡- ይኽን ፕሮፖዛል ወይም ምክረ ሐሳብ ለምን ማቅረብ መረጡ?
አንደኛው ትልቁ ነጥብ፣ እያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን ያለውን አቅም የላይኛው አስተዳደር አካል በሚገባ ለማወቅ ይችላል፡፡ አኹን በጣም ከፍተኛ ብክነት በመኖሩ የላይኛው ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ከታች ያለውን ትክክለኛ አቅም አላወቀውም፡፡ በመኾኑም በየአር ትራንስፖርት እንበለው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ካሽ ሬጅስተር በመጠቀም የገቢውን ትክክለኛ አኃዝ የላይኛው አስተዳደር ማወቅ የሚችልበት ዕድል ያመቻቻል፡፡
ኹለተኛው ትልቁ ጉዳይ ደግሞ ካሽ ሬጅስተር ለመጠቀም አኹን እየጠፋ ያለውን ከፍተኛ ገንዘብ በመዝገብ በመያዝ ዘመናዊ አሠራርን ማስፈን ይቻላል፡፡ አኹን እየጠፋ ያለውኮ ብሩ ብቻ ሳይኾን ሰነዱም ጭምር ነው፡፡ የካሽ ሬጅስተርን መረጃ ግን ማጥፋት ስለማይቻል የቁጥጥር ሥርዓትን ማጉላትና ተጠያቂነትን ማስፈን ይቻላል፡፡ በዚኽም ያለውን የፋይናንስ ሥርዓት ችግሮች በማስወገድ ቤተ ክርስቲያን ባላት አቅም የተለያዩ ልማቶችንና ሌሎች ሥራዎችን ማከናወን ይቻላታል ከሚል ሐሳብ በመነሣት ነው ፕሮፖዛሉን ያዘጋጀኹት፡፡
አዲስ ጉዳይ፡- ካሽ ሬጅስተር መጠቀሙ ሃይማኖታዊ ትእዛዝን ያዛንፋል የሚሉ አሉ?
እዚኽ ላይ ግልጽ መኾን ያለበት ነገር ካሽ ሬጅስተሩ የአንድን ሰው ስጦታ ሳይኾን የቤተ ክርስቲያኒቱን ገቢ የሚያሳውቅ ብቻ መኾኑ ነው፡፡ ምእመኑ ልክ እንደ ቀድሞ ኹሉ አቅሙ የፈቀደውን ነው ማንም ሳያይበት ሙዳየ ምጽዋት ውስጥ የሚጨምረው፤ ነገር ግን ከሙዳየ ምጽዋት ውስጥ ገንዘቡ ወጥቶ ይቆጠራል፡፡ ይኼን የተቆጠረ ገንዘብ ነው ካሽ ሬጅስተሩ የሚመዘግበው፡፡ ከዚኽ ውጭ ግን ከተለያየ ቋሚ ይኹን የአገልግሎት ገቢ ሲገኝ ለወትሮም በደረሰኝ የሚሰበሰቡ በመኾናቸው ወዲያውኑ በካሽ ሬጅስተሩ እንደሚዘገብ ይደረጋሉ፡፡
አዲስ ጉዳይ፡- በቤተ ክርስቲያን ያለውን የአስተዳደር ችግር ፈጽሞ ለማመን የሚከብዳቸው አሉ…
በነገርኽ ላይ እኔም ሰው ሲነግረኝ በፍጹም አላምንም ነበር፡፡ የሚሰርቅ ቀርቶ የሚዋሽ የአስተዳደር ሠራተኛ ይኖራል የሚል እምነት ፈጽሞ አልነበረኝም፡፡ ይኼ ግምቴ ግን ድሮ ሳይኾን አኹንም የዩኒቨርስቲ አስተማሪ እንኳ ኾኜ ነው፡፡ እኔ ራሴ የአስተዳደር ዝርክርክነቱ መኖሩን ያወቅኹት በሰበካ ጉባኤ መሳተፍ ከቻልኹ በኋላ ነው፡፡
ይኼ የአስተዳደር ችግር ባይኖር ኖሮ የአንድ ደብር ጸሐፊ የኾነ ሰው እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ከኹለት ሺሕ ብር በማይበልጥ ደመወዝ ኹለት ሦስት መኪና፣ ኹለት የመኖሪያ ቤቶች በፍጹም ሊኖረው አይችልም፡፡ የአንድ ወር ደመወዛቸው ለመኪና ነዳጅ ወጭ የማይሸፍንላቸው አገልጋዮች መኪና እየለዋወጡ ሲይዙ በድሎት ሲኖሩ፣ በርካታ የልጆች ኾነ የራሳቸው ወጭዎች ያለችግር ሲሸፍኑ ይኼ ነገር ከየት መጣ ያሰኛል፡፡ እንደውም አንዳንዶቹ ከተወለዱበት ዕለት አንሥቶ አኹን የሚያገኙበት ደመወዝ ተደምሮ ቢሰጣቸው ሊኖራቸው የማይችለውን ሰፊ ሀብት ለማካበት ኹሉ የቻሉ ናቸው፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ቅርብ ለኾኑ ሰዎች ኹሉ ይኼ ግልጽ ነው፡፡
አዲስ ጉዳይ፡- በአኃዛዊ ስሌት የገንዘብ ዘረፋው ምን ያኽል ይደርሳል?
እኔ በየዓመቱ ቤተ ክርስቲያን በመቶ ሚልዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ትመዘበራለች ብዬ በመጽሐፌ ላይ ገልጩ ነበር፡፡ ይኹን እንጂ አኹን ከቀድሞ በተሻለ ጉዳዩን ስመለከተው ቤተ ክርስቲያን በምዝበራ የምታጣው ሀብት ከመቶ ሚልዮኖች የሚልቅ መኾኑን ለመረዳት ችያለኹ፡፡
አዲስ ጉዳይ፡- የቤተ ክርስቲያኗ የፋይናንስ ሥርዓት ኋላቀር መኾኑ ይነገራል፡፡ እውነት ነው?
ስለ ፋይናንስ ሥርዓቱ ሲነሣ ብዙ ሰዎች ቤተ ክርስቲያኒቱ የምትጠቀምበት ዘመናዊ አሠራር (double entry) ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን አኹን እየተጠቀመችበት ያለው የፋይናንስ ሥርዓት ዓለም በ፲፯ው መ/ክ/ዘ የተወውንና የነጠላ ሒሳብ አሠራር (single entry) የሚባለውንና በሞዴል የሚሠራ የሒሳብ አሠራር ነው፡፡ በዓለም ላይ እንዲኽ ዓይነት የሒሳብ አሠራር የሚከተል ምንም ተቋም የለም፡፡ በመኾኑም ይኼን ተረድቶ የፋይናንስ ሥርዓቱን ማዘመን ይገባል፡፡
ይኼ የሒሳብ አሠራር በፍጹም ምቹ አይደለም፡፡ የሒሳብ አሠራሩ በራሱ ነጠላ ነው፡፡ ወጪን ወጪ ይላል እንጂ ምክንያቱን አይናገርም፡፡ ስለዚኽ ወጪን ከነምክንያቱ ገቢን ከነምንጩ የሚጠቅሰው የኹለትዮሽ(ደብል) አሠራር ሥርዓት የላትም፡፡ ይኼ አሠራር ደግሞ በአፋጣኝ መለወጥ አለበት፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ቀደም ሲል ከጠቀስኹት ወጭ ዘርዝረን የማንጨርሳቸው በርካታ ሌሎችም ችግሮች ስላሉ ነው፡፡
አዲስ ጉዳይ፡- እርስዎ ያቀረቡት ሐሳብ ይኹን የተጀመረው የለውጥ ዝግጅት እንቅስቃሴ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ እንደዚኽም ኾኖ ያሉት የአስተዳደር ችግሮች ይፈታሉ ብለው ያስባሉ?
ትውልዱና ዘመኑ የሚፈልጉት በመኾኑ ያቀረብኹት ሐሳብ ይተገበራል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ዛሬ ላይ ባይኾን ነገ ይኼ ነገር ይተገበራል፡፡ በዚኽ ላይ የተጀመሩትን የለውጥ እንቅስቃሴዎች የሚቃወሙት በአስተዳደር ላይ ያሉ ጥቂት ሰዎች ናቸው፤ አስተዳደር ላይ ኾነውም ለውጡን የሚደግፉ አሉ፡፡ ምናልባት ጊዜ ይፈጅ ይኾናል እንጂ ችግሩ መፈታቱ አይቀሬ ነው፡፡ በዚያ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስና ሌሎችም አባቶች ግልጽነቱ እንዲመጣ ጠንካራ አቋም ይዘው እየሠሩ በመኾኑ ለውጡ አይቀሬ ነው፡፡ ይኼም ኾኖ የአስተዳደር ችግር እንዲፈታ ኹሉም የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል፡፡

Saturday, 22 March 2014

ሰበር ዜና – የማኅበረ ቅዱሳንን አመራርና አባላት በአክራሪነት የሚከስ ዶክመንተሪ ሊዘጋጅ ነው ተባለ



  • ዶክመንተሪው የ2007 ሀገራዊ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት አካል እንደኾነ ተጠቁሟል
  • ‹‹ማስረጃ አቅርቡና እንነጋገርበት›› ለሚለው የማኅበሩ ጥያቄ ምላሽ አልተሰጠም
(ፋክት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፴፰፤ መጋቢት ፳፻፮ ዓ.ም.)
FACT Magazine Megabit Cover00በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሲኖዶሱን ይኹንታ አግኝቶ በመላው አገሪቱ የሚንቀሳቀሰውን የማኅበረ ቅዱሳንን አመራርና አባላት በአክራሪነት የሚከስ ነው የተባለ ዶክመንተሪ ፊልም ለማዘጋጀት መታቀዱ ተጠቆመ፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አንዳንድ ሓላፊዎች አቀብለውታል በተባለ መረጃ እንደሚታገዝና በመንግሥት አካል እንደሚሰናዳ የተገለጸው የዶክመንተሪ ዝግጅቱ በማኅበሩ ኻያ አመራሮች እና አባላት ላይ እንዳነጣጠረ ተገልጧል፡፡
መንግሥት በምርጫ – 97 ውጤትና በተከታይ ኹኔታዎቹ ላይ ባካሔደው ግምገማ፣ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ናቸው የሚባሉ ግለሰቦች በተለይ በገጠር ቀበሌዎች ለተቃዋሚዎች ተሰሚነት ማግኘት በምክንያትነት መጥቀሱ በዜና ጥቆማው የተመለከተ ሲኾን ‹‹የአክራሪነትና የጽንፈኛ ፖሊቲከኞች ምሽግ ነው›› በሚል የሚያቀርበው ክሥም ከዚኹ የሚነሣና ለመጪው የ2007 ሀገራዊ ምርጫ የሚደረግ ቅድመ ዝግጅትም አካል እንደኾነ ተነግሯል፡፡
በቅድመ ዝግጅቱ የሚወሰዱ ርምጃዎች የማኅበሩን አቅሞችና እንቅስቃሴዎች በመቆጣጠር በተለይም የማኅበሩ መሠረቶች ናቸው የሚባሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያትን ‹‹በሴኩላሪዝም መርሖዎች የመግባቢያ ሰነድ›› ጠርንፎ ‹የአገልግሎት ቅኝቱን የማስተካከል› ዓላማ እንዳላቸው የገለጸው የዜና ምንጩ፣ ይህም ካልተሳካ በተከታታይ አስተዳደራዊ ርምጃዎችና የተቃውሞ ቅስቀሳዎች ማኅበሩን በማወከብ ተቋሙን ለዘለቄታው የማፍረስ ውጤት ሊኖረውም እንደሚችል አመልክቷል፡፡
ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት አብያተ ክርስቲያናት የተጠሩ ናቸው የተባሉ አስተዳዳሪዎችና ሠራተኞች የሚሳተፉበት እንደኾነ የተገለጸና ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በማኅበሩ አገልግሎት ላይ ቁጥጥሩን እንዲያጠብቅ የሚጠይቅ ስብሰባ በዛሬው ዕለት በቤተ ክህነቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚካሔድ የተዘገበ ሲኾን ዓላማውም ‹‹በአክራሪዎችና ጽንፈኛ ፖሊቲከኞች ምሽግነት፣ የቤተ ክህነቱን አሠራር ባለማክበርና ከቤተ ክህነቱ በላይ ገዝፎ በመውጣት›› ማኅበሩ የሚከሰስባቸውን ኹኔታዎች በማጠናከር ለታቀዱት ርምጃዎች የሚያመቻች ነው ተብሏል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን÷ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ላይ በማተኮር የተማረው ትውልድ ሃይማኖቱን የሚወድ፣ ግብረ ገብነት ያለው፣ ሀገሩንና ቤተ ክርስቲያኑን በዕውቀቱ፣ በሞያውና በገንዘቡ የሚያገለግል ብቁ ዜጋ ይኾን ዘንድ በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በተሰጠው መተዳደርያ ደንብ መሠረት በመሥራት ላይ እንዳለ የሚገልጹ የማኅበሩ አባላትና ደጋፊዎቹ፣ ማኅበሩ ለቀረቡበት ክሦች የሚመች አደረጃጀት ይኹን ባሕርይ እንደሌለው በመግለጽ ተጠሪ ከኾነለት ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጋራ በአሠራር ሒደት የሚፈጠር ክፍተትን በማጦዝ የሚሰነዘሩ ውንጀላዎች ተቀባይነት እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡
የተጠቀሱትን ክሦች ለሚያቀርቡት አካላት ‹‹የሚነገረውና የሚጻፈው እኛን የሚገልጸን ስላልኾነ ማስረጃ አቅርቡና እንነጋገርበት›› የሚል ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ለሠለጠነ ውይይት ፍላጎት እንደሌላቸው አባላቱ አስረድተዋል፤ በምትኩ ‹‹ርምጃ እንወስዳለን›› በማለት በተለያዩ መድረኮች ማኅበሩን ማሳጣትና መክሠሥ እንደሚመርጡም ለፋክት መጽሔት አስታውቀዋል፡፡ ታቅዷል የተባለው የዶኩመንተሪ ዝግጅት እውነት ከኾነም ማኅበሩን ብቻ ሳይኾን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የማዳከም አጠቃላይ ዘመቻ አንድ አካል አድርገው እንደሚቆጥሩትና በቀላሉ እንደማይመለከቱት አሳስበዋል፡፡

የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ተቃዋሚ አማሳኞች ማኅበረ ቅዱሳን በአክራሪነትአ እና ሕገ ወጥነት የሚወነጀልበትን መሠረተ ቢስ ክሥ የሚያዳብር የአቋም መግለጫ የሚያወጡበትን ስብሰባ ቅዳሜ ለማካሔድ እየቀሰቀሱ ነው



ማኅበረ ቅዱሳን
ማኅበረ ቅዱሳን
  • አማሳኞቹ ‹‹በግንቦቱ ሲኖዶስ ለውሳኔ ይቀርባል›› ያሉት የአቋም መግለጫ ከፖሊቲከኞችና ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኞች ጋራ ግንባር የፈጠሩበትና የማኅበሩን መዋቅር እና አገልግሎት አዳክሞ ለመቆጣጠር አልያም አካቶ ለማፍረስ ለተያዘው የአስተዳደራዊ ርምጃ ውጥን ግብዓት የሚኾን ነው፡፡
  • የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር እና ሥራ አስፈጻሚ አባላት በደጅ ጥናትም ቢኾን ከፓትርያርኩ ጋራ በግንባር የመነጋገር ዕድል ካገኙና ፓትርያርኩም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ይዘው ሌላ ዙር ሰፊ ምክክር እንደሚያካሒዱ በገለጹሳምንት ጊዜ ውስጥ÷ ‹‹በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ለግንቦት ሲኖዶስ ውሳኔ ግብዓት የሚኾን የአቋም መግለጫ እናውጣ›› ለሚሉ አማሳኞች የስብሰባ ፈቃድ መሰጠቱና ፓትርያርኩም በስብሰባው ላይ ለመገኘት መስማማታቸው፣ ሰሞኑን የሚታየው የማኅበሩን እንቅሰቃሴ በአስተዳደራዊ ርምጃዎች የማሰናከልና አገልግሎቱን የማዳከም ርብርብ ውጫዊ ፖሊቲካዊ ግፊትም እንዳለበት አመላካች ኾኗል፡፡
  • ፓትርያርኩን በግንባር ያነጋገረው የማኅበሩ አመራር በአጠፌታው፣ የሚሰነዘርበትን ማንኛውንም ውንጀላ በፍትሕ አካል በሕግ አግባብ ከመፋረድ ጀምሮ በጥቅመኝነት፣ በፖሊቲከኝነትና በኑፋቄ ዓላማዎች የሚገፋውን የቀንደኛ አማሳኞች ክሥ በዐደባባይ ለመፈተንና ለማጋለጥ እንደሚሠራ ይጠበቃል፡፡
*                               *                              *
NebureEd Elias Abreha
ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ
  • የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከሰጠው አቅጣጫ በተፃራሪ ‹‹የአደረጃጀትና አሠራር ጥናቱን ዳግመኛ መገምገም›› በሚል በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ስም ተሠይመው የጥናት ሰነዱን በተጽዕኗቸው ሥር ካስገቡት ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ እና አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ጋራ ጥብቅ ቁርኝት ፈጥረው የሚንቀሳቀሱት አማሳኞቹ እነ ኃይሌ ኣብርሃ እና ዘካርያስ ሐዲስ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ሀብትና ንብረቱን ያስረክብ›› በሚል በጠሩት ስብሰባ ላይ የማይሳተፉ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችን በመፈረጅና የሓላፊነት ቦታቸውን በማስነጠቅ ጭምር ለማስመታት እየዛቱ ናቸው፡፡
  • ‹‹ድምፃችን አልተሰማም›› የሚሉ የተቋማዊ ለውጥ ደጋፊዎች በበኩላቸው፣ በአማሳኞቹ የተጠራውን ስብሰባ÷ የአደረጃጀትና አሠራር ጥናቱ የደረሰበትን ለማወቅ እና በማኅበሩ ላይ አላግባብ የሚደረገው ተጽዕኖ እንዲቆም ወደሚጠይቅ ትዕይንት ለመለወጥ እየተዘጋጁ ናቸው፡፡
  • ፓትርያርኩ የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ተቃዋሚ አማሳኞችን ለአማካሪነትና ለረድእነት ባቀረቧቸው ግለሰቦች አሳላፊነት በየዕለቱ ለማለት በሚቻል ኹኔታ እየተቀበሉ ከመማከር ባሻገር በስብሰባቸው ላይ ለመገኘት ፈቅደዋል መባሉ ለመልካም አስተዳደር፣ ፍትሕና ርትዕ ከሚናገሩበት ሞራላዊ ሥልጣን እንደሚያሰናብታቸው እየተነገረ ነውውጤቱም ቤተ ክርስቲያናችንን የርስ በርስ ትርምስ ውስጥ በመጨመር ተቋማዊ ህልውናዋን ለከፋ አደጋ እንዳያጋልጠው አስግቷል፡፡