Saturday, 15 March 2014

የድሬዳዋ ምእመናን በጥረታቸው የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ አስከበሩ! የቅ/ገብርኤል ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ሒሳብና የግንባታ ጥራት ምርመራ እንዲዘገይ ኹለት ጊዜ ያዘዙት ፓትርያርኩ ምርመራው እንዲቀጥል መመሪያ ሰጡ! መዝባሪዎቹ ምርመራውን ለሦስተኛ ጊዜ ለማስተጓጎል በአዲስ አበባ ይገኛሉ


  • ምርመራው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ተባርኮ ታቦቱ ከመግባቱ በፊት ይከናወናል
  • የጠ/ቤ/ክህነቱ የቁጥጥር አገልግሎት ከምእመናኑ ጥረት ጎን በመቆም ከፍተኛ ድጋፍ አድርጓል
  • በሀ/ስብከታቸው አስተዳደር ጣልቃ መገባቱን ሊቀ ጳጳሱ ለቋሚ ሲኖዶስ አባላት አስታውቀዋል
  • መዝባሪዎቹ ‹‹አንመረመርም›› በሚል በሊቀ ጳጳሱና በደብሩ አስተዳዳሪ ላይ እየዛቱ ናቸው
  • የጠ/ቤ/ክቱ ምሕንድስና ዘርፍ ሓላፊ ኢ/ር ሰሎሞን ካሳዬ ብቃት እንዲመረመር ተጠይቋል
Private Secretariat office of His Holiness on D.D.Gab Audit Row
ፓትርያርኩ በተሟጋች ምእመናን ጥያቄ ምርመራው እንዲቀጥል ያዘዙበትና የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ ያስከበረው ደብዳቤ
ለቤተ ክርስቲያናችን የታቀደውን የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ጥረት የሚቃወሙ አማሳኝና ጎጠኛ አስተዳዳሪዎችና ተባባሪዎቻቸው በእብሪትና በስሜታዊነት ሲለፍፉ እንደሰነበቱት፣ ምእመኑ የሚሰጠውን ሰጥቶ ዘወር ማለት አለበት እንጂ ስለ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የሚያገባው ነገር የለም፤ በእነርሱ እምነት ‹‹ነጠላ ለባሽ›› አቶና ወይዘሪት የሚያጠኑት ጥናትና ድጋፍ ሰጭ ጥረቶቻቸው ኹሉ ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅም አይደለም፤ እንዲያውም ‹‹የቤተ ክርስቲያን አባላት እንጂ አካላት አለመኾናቸው ታውቆ በቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ሊተላለፍበት ይገባል፡፡››
በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ግን፣ በሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንና በቃለ ዐዋዲው ድንጋጌዎች ለጾታ ምእመናን ከተሰጠው ድርሻ አንጻር ይህ ዐይነቱ የአማሳኞች የእብሪት አነጋገር ቦታ እንደሌለው የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ሥራ የተሟጋች ምእመናን ቡድን በተግባር አረጋግጠዋል!!
በሚልዮኖች የሚቆጠር የምእመናን ገንዘብና ንብረት በሕንፃ አሠሪ ኮሚቴው ለምዝበራ የተጋለጠበትና ከውለታ ጊዜው በላይ በእጅጉ የዘገየው የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ግንባታ ጥራት እንዲመረመር በቋሚ ሲኖዶሱ የተላለፈውን ውሳኔ በመጋፋት፣ ምርመራው ቤተ ክርስቲያኑ ተባርኮ ታቦተ ሕጉ እስኪገባ ድረስ እንዲዘገይ የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት በተደጋጋሚ ያስተላለፈውን ትእዛዝ በጽናት ሲቃወሙ የቆዩት ምእመናኑ፣ ጥረታቸው ሠምሮና ተቀባይነት አግኝቶ በቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔ መሠረት ምርመራው እንዲቀጥል በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መመሪያ ተሰጥቶላቸዋል፡፡
ፓትርያርኩ ምርመራው እንዲቀጥል መመሪያውን ለመስጠት የተገደዱት÷ ከድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ፣ ሰንበት ት/ቤት፣ የስብከተ ወንጌል እና ልማት ኮሚቴዎች የተውጣጡ 12 አባላት ያሉት የተሟጋች ምእመናን ቡድን በመንበረ ፓትርያርኩ በአካል ተገኝተው ጉዳዩን ለቅዱስነታቸውና ለሚመለከታቸው አካላት ኹሉ በሚገባ በማስረዳት ባደረጉት ጥረት ነው፡፡
ተጋድሎውን በ፳፻፫ ዓ.ም. የጀመረውና በመላው ምእመን የሚደገፈው ተሟጋች ቡድኑ ከየካቲት ፳፬ – መጋቢት ፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርኩ ባደረገው ቆይታ፣ በሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ግንባታ ስም በሕንፃ አሠሪ ኮሚቴው ሊቀ መንበርና የጥቅም አጋሮቻቸው የተፈጸመውንና በምርመራ የተረጋገጡ ጉድለቶችን በማስረጃ አስደግፎ ማጋለጡና ማስረዳቱ ታውቋል፡፡
pvt sec office of His Holiness 03
ፓትርያርኩ በመዝባሪዎች የተሳሳተ መረጃ የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ በመጋፋት ምርመራው እንዲዘገይ ያዘዙበት ደብዳቤ
የሕንፃ ሥራው የገቢና ወጪ ሒሳብ እንዲኹም የግንባታ ጥራቱ ቋሚ ሲኖዶስ መስከረም ፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት በብቁና ገለልተኛ ባለሞያዎች መመርመር ያለበት ቤተ ክርስቲያኑ ተባርኮ ታቦተ ሕጉ ከመግባቱ በፊት መኾን እንደሚገባው የተከራከሩት ምእመናኑ፣ ‹‹ምርመራው በማንኛውም ጊዜ ሊካሔድ ይችላል›› በሚል ለማዘግየት የሚደረግ ጥረት አንድም ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የሚጥስ በሌላም በኩል መዝባሪዎቹንና ተባባሪዎቻቸውን ከተጠያቂነት ለማዳን የሚደረግ ሙከራ ነው ብለዋል፡፡
ሒሳቡን መመርመርና የግንባታ ጥራቱን ማረጋገጥ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑን ሥራ ከማቀላጠፍ ጎን ለጎን ሊፈጸም እንደሚችል የገለጹት የተሟጋች ቡድኑ አባላት፣ የሕዝብ ገንዘብ እንዲመረመር የሚያደርጉት ጥረት ግንባታውን በማጓተት ቀውስ ለመፍጠር ከመሻት ጋራ ፈጽሞ ሊያያዝ እንደማይገባውና ይህ ፍላጎት፣ ግንባታውን በማጓተት ሕገ ወጥ ጥቅሙን ለማስጠበቅ የሚማስነው የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴው ሊቀ መንበርና የጥቅም ተጋሪው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የምሕንድስና ዘርፍ ሓላፊ እንደኾነ አስረድተዋል፡፡
ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም በቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔ መሠረት ለምርመራው ዝግጅት እንዲደረግ ለደብሩ አስተዳደር መመሪያ የሰጡበት ደብዳቤ
ተሟጋች የምእመናን ቡድኑ ባቀረቧቸው ማስረጃዎችና በሰጧቸው ማብሪራሪያዎች ላይ ከፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት፣ ከቋሚ ሲኖዶስ አባላትና ከሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም ጋራ ውይይት መደረጉ ተገልጧል፡፡ በውይይቱ ላይ ብፁዕነታቸው በቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔ መሠረት የሕዝብ ገንዘብ እንዲመረመር አማካሪ ድርጅት በግልጽ ጨረታ ተለይቶ ሥራው እንዲጀመር መመሪያ ቢሰጡም የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ለመዝባሪዎች በማድላትና ጥያቄያቸውን በመቀበል ከአንድም ኹለቴ በጻፈው ምርመራው እንዲዘገይ የሚያዝ ደብዳቤ ሳቢያ መጓተቱት አስረድተዋል፤ ድርጊቱንም በጣልቃ ገብነት ኮንነዋል፡፡
የተሟጋች ቡድኑን ድካም መና ለማስቀረት በአዲስ አበባ የሚገኘው የሕንፃው ተቋራጭ ኤፍሬም ተስፋዬና የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የምሕንድስና ዘርፍ ሓላፊ አቶ ሰሎሞን ካሳዬ በድሬዳዋ ኾኖ ከሚፎክረው የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ብርሃኔ መሐሪ ጋራ በመተባበር የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት እገዛ ቢሚፀኑም እንዳልተሳካላቸውና ‹‹አሳሳቾች›› ተብለው በልዩ ጽ/ቤቱ ሓላፊ አቡነ ገሪማ መባረራቸው ተጠቁሟል፡፡
በውጤቱም ፓትርያርኩ በልዩ ጽ/ቤታቸው በኩል በሰጡትና በቁጥር ል/ጽ/299/66/2009 በቀን 2/7/2006 ዓ.ም. በወጣ መመሪያ መሠረት÷ የሕንፃው የገቢና ወጭ ሒሳብና የግንባታው ጥራት ምርመራ ቋሚ ሲኖዶስ መስከረም ፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. በሰጠው ውሳኔ መሠረት በገለልተኛ ኦዲተርና በመንግሥት የሥራና ከተማ ልማት ባለሞያዎች እንዲጣራ፣ ቀሪው የሕንፃ ግንባታም ጎን ለጎን እንዲጠናቀቅ ትእዛዝ ሰጥተዋል፡፡
ይኸው መመሪያ የተላለፈበት የፓትርያርኩ ደብዳቤ ጥር 9 ቀን 2006 ዓ.ም. በቁጥር ል/ጽ/114/66/2006 እና የካቲት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. በቁጥር ል/ጽ/263/2006 ዓ.ም. ምርመራው ቤተ ክርስቲያኑ ተባርኮ ታቦቱ ከገባ በኋላ እንዲካሔድ የሰጡት ትእዛዝ የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ ያላገናዘበ መኾኑን በግልጽ ከማስቀመጡም በላይ ተፈጻሚነት እንደማይኖረውም ተመልክቷል፡፡
ተሟጋች ምእመናኑ ጉዳያቸውን ለሚመለከታቸው አካላት ለማስረዳት ያደረጉትን ጥረት ከመደገፍ ጀምሮ መመሪያ የተሰጠበትን የፓትርያርኩን ደብዳቤ በማርቀቅ ረገድ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የቁጥጥር አገልግሎት መምሪያ ዋና ሓላፊ መ/ር ኤርሚያስ ተድላ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጋቸው ተገልጦአል፡፡
ዋና ሓላፊው፣ የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔና በሐምሌ ወር ፳፻፫ ዓ.ም. የቁጥጥር አገልግሎት መምሪያው በኦዲት ቡድኑ ባደረገው ማጣራት ከደንብና አሠራር ውጭ ከ1.8 ሚልዮን ብር በላይ ለተቋራጭ ክፍያ እንደተፈጸመ የተረጋገጠበትን ሪፖርት መሠረት በማድረግ በጉዳዩ ተጠያቂ የኾኑት አካላት አስተያየት ውድቅ ተደርጎ የምእመናኑ አቤቱታ ተቀባይነት ማግኘት እንዳለበት ለፓትርያርኩና ለልዩ ጽ/ቤታቸ ማብራሪያ መስጠታቸው ተዘግቧል፡፡
ከዚኹ ጋራ በተያያዘም ያለበቂ ጥናት በተካሔዱና እየተካሔዱ በሚገኙ የቤተ ክህነቱ የግንባታ ፕሮጀክቶች የደረሱትንና በመድረስ ላይ ያሉትን ብክነቶችና ምዝበራዎች በመጥቀስ ፕሮጀክቶቹን በዘፈቀደ በማጽደቅ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ጉዳት እንዲደርስ ምክንያት ኾነዋል የተባሉት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የምሕንድስና ዘርፍ ሓላፊ ኢ/ር ሰሎሞን ካሳዬ ብቃትና በግለሰቡ ብቻ የሚመራው የዘርፉ የግንባታ ቁጥጥር አግባብነት እንዲገመገም በዋና ሓላፊው መጠየቁ ተገልጦአል፡፡
ምንጮች እንደሚያስረዱት፣ ፓትርያርኩ በአማካሪነት ካስጠጓቸውና ለስሕተቶቻቸውም ተጠያቂ ከሚደረጉት ግለሰቦች አንዱ የኾኑት ኢ/ር ሰሎሞን ካሳዬ፣ በመንግሥት የሥራና ከተማ ልማት መሥ/ቤት ባልደረባ የነበሩ፣ በአቅም ማነስና ሙስና ከመባረራቸውም በላይ በየትኛውም ተቋም በሞያቸው እንዳሠሩ እገዳ የተጣለባቸው ናቸው፡፡
ፓትርያርኩ ምርመራው እንዲቀጥል የሰጡት ትእዛዝ እንደተሰማ፣ በድሬዳዋ የሚገኘው የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ ሊቀ መንበር መዝባሪው ብርሃኔ መሐሪ ‹‹የተጻፈልኝን ደብዳቤ ማንም አያሻራትም›› በሚል የደብሩን አስተዳዳሪና የሀ/ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ከሓላፊነታቸው የሚያሥነሳበትን ደብዳቤ ይዞ እንደሚመጣ በተመልካቾች ፊት ከመዛቱም ባሻገር ትእዛዙን ለማስገልበጥ ከኻያ ሺሕ ብር በላይ ወጭ ከሕንፃ ኮሚቴው ገንዘብ አውጥቶና የሐሰት የአቤቱታ ፊርማ አዘጋጅቶ ወደ አዲስ አበባ መጓዙ ተሰምቷል፡፡ ይህ መረጃ በሚጠናቀርበት ሰዓትም ግለሰቡ በአዲስ አበባ እንደሚገኝ የተመለከተ ሲኾን ምርመራው እንዲቀጥል በፓትርያርኩ የተላለፈውን ትእዛዝ በለመደው መንገድ ያስገለብጠው እንደኾነ በቅርበት የምንከታተለው ይኾናል፡፡
የድሬዳዋ ሳባ ደ/ኃ/ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ግንባታ በዕሥራ ምእቱ መባቻ ከተገባለት የውለታ ጊዜ ውጭ ለስድስት ዓመት የተጓተተና በውል ስምምነት ተይዞ ከነበረው ሦስት ሚልዮን ብር በላይ በሚልዮኖች የሚገመት የምእመናን ብርና የዐይነት አስተዋፅኦ ለዝርፊያ የተጋለጠበት እንደኾን ሲዘገብ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በአዲስ አበባስ??
ከዘገባው እንደምንረዳው በቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ወገኖችን የሚያሸማቅቁት ብልሹ አሠራር የሚመቻቸውና ይኸው ብልሽት በግልጽነትና ተጠያቂነት መርሕ እንዳይታረም የሚሹ አማሳኞች ብቻ ናቸው፡፡ በአንጻሩ ለቤተ ክርስቲያናችን የታቀደው የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ጥናት በዐጸደ ሥጋም በዐጸደ ነፍስም ያሉ በርካታ ምእመናን የጸሎት ውጤትና የቤተ ክርስቲያናችን ትንሣኤ ለመቃረቡ ምልክት መኾኑን ማኅበረ ምእመናንና ሌሎችም የተቋማዊ ለውጥ ኃይሎች ከመናገራቸውም በላይ ዓይናቸው፣ ጆሯቸውና ልባቸው በለውጡ ተግባራዊነት ላይ እንደኾነ ገልጸዋል፡፡

ፓትርያርኩም የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሰጠው አቅጣጫ መሠረት የአደረጃጀትና አሠራር ለውጡን ተግባራዊ በማድረግ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከብዝበዛ እንዲያድኑ ማኅበረ ምእመናኑ በእንባ ጭምር ተማፅነዋቸዋል፡፡ ንግግር፣ ገለጻና ተማኅፅኖ ግን ውጤት ሊያስገኝ የሚችለው እንደ ድሬዳዋ ምእመናን በጽናት የሚዘልቅ፣ በተግባር የታገዘ ኹለንተናዊ መተባበር ሲኖር ነው፡፡
በአኹኑ ወቅት የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ተቃዋሚዎች ለውጡን በመደገፍ የተንቀሳቀሱ አስተዳዳሪዎችን ‹‹ጥናቱ ከሽፏል፤ የት ትገባላችኹ!›› በሚል ከማስፈራራትም አልፈው የጥናት ሰነዱን ዳግመኛ እንዲገመግሙ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ስም ከተሠየሙትና በፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ዙሪያ በአማካሪነት ስም ከከተሙት የሙስና ጌቶች ጋራ ጥዋት ማታ ጥብቅ ግንኙነት ፈጥረው ይታያሉና ምእመኑ ሒደቱን በንቃት በመከታተል እንደ ድሬዳዋ ምእመናን የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ የማስከበር ድርሻውን ሊወጣ ይገባል፡፡

Friday, 14 March 2014

ጥንታዊቷ የወይብላ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተመዘበረች

አትም ኢሜይል
 መጋቢት 4 ቀን 2006 ዓ.ም.
ሹመት ገ/እግዚአብሔር
በደሴ ማእከል ከወረኢሉ ወረዳ ማእከል
በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በወረኢሉ ወረዳ የምትገኘው የወይብላ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ማንነታቸው ባልታወቁ ዘራፊዎች ተመዘበረች፡፡

የወይብላ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከወረኢሉ ከተማ 24 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ የካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም በግምት ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች ንዋየ ቅድሳቷ የመዘረፍና የመውደም አደጋ ደርሶባታል፡፡

ድርጊቱ የተፈጸመው የቤተ ክርስቲያኒቱን በርና መስኮት ሰብሮ በመግባት ሲሆን፤ ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የቅዳሴ መጽሐፍ ባለምልክቱ፣ ሰባት የቤተ ክርስቲያን መጋረጃ፣ ሰባት መቋሚያ፣ ሦስት ምንጣፍ እና አምስት መሶበ ወርቅ ተሰርቋል፡፡ ትልቅ የመፆር መስቀል እና የእጅ መስቀሎች የተፈላለጡ ሲሆን መንበሩ ተገነጣጥሏል፡፡ ቤተ ክርስቲያኗንና መንበሩን ሳርና ስዕለ አድህኖ በመሰብሰብ ለማቃጠል የተደረገው ሙከራም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

መጽሐፈ ክርስትና፣ ሥርዓተ ተክሊልና መጽሐፈ ግፃዌ ሙሉ በሙሉ ተቀዳደው፤ ሻኩራ፣ ፃህል፣ እርፈ መስቀል፤ ሻማዎች፣ የተቀጠቀጡ አንድ ሺህ ጧፎች፤ አስር ኪሎ እጣን፤ ጥላዎች ተቀዳደው፤ 15 ባለ መስታወት ፍሬም ስዕለ አድህኖዎች ተሰባብረው፤ ከፍሬም ውጭ የሆኑ 88 ስዕለ አድኅኖዎች ተቀዳደው ጫካ ውስጥ የተጣሉ ሲሆን፤ መቋሚያዎችና አምፖሎች ከነማቀፊያቸው ተሰባብረው ገደል ውስጥ ተጥለዋል፡፡ 6 ትላልቅ ሥዕለ አድኅኖዎችም ተቃጥለዋል፡፡

ይህንን ልብ የሚያደማና የሚያሳዝን ድርጊት የወረዳው ከፍተኛ የሥራ ሓላፊዎች እና የፀጥታ ኃይሎች ቦታው ድረስ በመሄድ የተመለከቱ ሲሆን፤ ድርጊቱን የፈፀሙትን ወንጀለኞች ለመያዝ የወረዳው ፖሊስ አስፈላጊውን ክትትልና ምርመራ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

የወይብላ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በግራኝ አህመድ ከመቃጠሏና ከመውደሟ በፊት “ቀርቀሬ ማርያም” በሚል ስያሜ ትጠራ የነበረ ሲሆን፤ የአካባቢው ተወላጆች ወደ ጦር ሜዳ በሔዱ ጊዜ “ያገሬ ታቦት ወይ በይኝ፣ ከዚህ ጦርነት በሰላም ከመለሺኝ ስመለስ ስዕለቴን አገባለሁ” ብለው በመሳላቸውና ሥዕለታቸውም በመድረሱ ሲመለሱ “ወይብላ ማርያም” በሚል ስያሜ እንደተጠራች ይነገራል፡፡ ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2000 ዓ.ም ድረስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኗ እንደገና ታንፆ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ መልክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነበረች፡፡

Tuesday, 11 March 2014

ፓትርያርኩ ለአማካሪነት ባስጠጓቸው አካላት ማንነት ተተቹ


  • የአመራርና የውሳኔ ሰጭነት አቅማቸው አጠያያቂ ኾኗል
(ፋክት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፴፮ የካቲት ፳፻፮ ዓ.ም.)
his grace abune elsae
ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ
የሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ከዓመት በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፮ው ፓትርያርክ ኾነው የተመረጡበት አንደኛ ዓመት በዓለ ሢመት፣ የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. የተከበረላቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያን ከሚታወቀው አስተዳደራዊ መዋቅር ውጭ ለአማካሪነት አቅርበዋቸዋል በተባሉ አካላትና ግለሰቦች ማንነት ሳቢያ በአንድ የቅዱስ ሲኖዶሱ አባል ትችት ተሰነዘረባቸው፡፡
የፓትርያርኩ የመጀመሪያ ዓመት በዓለ ሢመት በተከበረበት ዕለት ማምሻውን፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በተዘጋጀ የራት መርሐ ግብር ላይ ትምህርት እንዲሰጡ የተጋበዙት የሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ ‹‹እርስዎ ከማን ጋር ወርደው ነው እየተማከሩ ያሉት?›› ሲሉ ፓትርያርኩን መጠየቃቸውና የምክር ቃል መለገሣቸው ታውቋል፡፡
በኤጲስ ቆጶስነት ሹመት ዘመነኛቸውና ቀራቢ ወንድማቸው መኾናቸውን ያወሱት አቡነ ኤልሳዕ፣ አቡነ ማትያስ ከረዥም ጊዜ የውጭው ዓለም ቆይታና አገልግሎት በኋላ ለፕትርክና ክብር መብቃታቸው በይበልጥ እርሳቸውን ደስ እንደሚያሰኛቸው ገልጸዋል፡፡ ‹‹አንድ ፓትርያርክ ከማን ጋር ነው ምክሩ?›› በማለት ወንድማዊ ነው ያሉትን ምክራቸውን የቀጠሉት ሊቀ ጳጳሱ፣ አቡነ ማትያስ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመምራት የተቀበሉትን ታላቅ ሓላፊነት ከቅ/ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊና ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጋራ በቅርበት እየተመካከሩ ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው፣ ከዚያም ሲያልፍ ከቋሚ ሲኖዶስና አስፈላጊ ከኾነም የቅ/ሲኖዶሱን ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት መምክር እንደሚገባቸው አስረድተዋል፡፡
‹‹ምክርዎት ከሌላ ጋር ከኾነ በጣም አስቸጋሪ ይኾናል›› ሲሉ ያሳሰቡት አቡነ ኤልሳዕ፣ ፓትርያርኩ መዋቅሩንና ደረጃቸውን ጠብቀው ሓላፊነታቸውን እንዲወጡ ከመምከራቸውም ባሻገር በአመራራቸውና ውሳኔያቸው ላይ ተጽዕኖ እያሳረፈ ነው የሚባለውን የጎሰኝነት ከበባም የሚያመለክት አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ የፓትርያርኩ በዓለ ሢመት የተከበረበት ዕለት የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት መታሰቢያ መኾኑን ያዘከሩት አቡነ ኤልሳዕ፣ ኢትዮጵያዊው ሐዋርያ ከውጭ ከመጡት ሌላው ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጋር በመላው ሀገሪቱ እየተዘዋወሩ ሲያገልግሉት ‹‹ከየት መጣኽ አልተባባሉም፤ ዘር ጎጥ አልተጠያየቁም፤ ቅዱስነትዎም ከሥራ ጓደኞችዎ ጋራ ከየት መጣኽ ሳንባባል በአንድነት እየተመካከርን ነው ማገልገል ያለብን፤ ከዚያ ወርደን መገኘት የለብንም፤›› በማለት ምክር አዘል ትምህርታቸውን አጠቃለዋል፡፡
የሊቀ ጳጳሱ ምክር አዘል ትምህርት ወቅታዊና ተገቢ መኾኑን ለፋክት የተናገሩ የበዓለ ሢመቱ ተሳታፊዎች፣ ፓትርያርኩ በአማካሪነት አቅርበዋቸዋል የሚባሉትን ግለሰቦች በስም በመጥቀስ÷ ቅዱስነታቸው በንግግር ከሚታወቁበት መልካም አስተዳደርን የማስፈን፣ ለሙስናና ብክነት የተጋለጡ ብልሹ አሠራሮችን በወሳኝ መልኩ የመቅረፍና የማድረቅ ጥረት ጋር የሚጣጣም ማንነት ጨርሶ እንደሌላቸው ያስረዳሉ፡፡ [ግለሰቦቹ በሓላፊነት በሠሩባቸው ቦታዎች የዘርና የመንደር ቡድን በማቋቋም በአቀባይና ተቀባይ (ኔትወርኪንግ) ባደራጇቸው ደላሎች የሙስና ገበያን በማጧጧፍ ቅጥር፣ ዕድገትና ፍትሕ ፈላጊውን አገልጋይና ሠራተኛ በከፍተኛ ደረጃ በማተራመስ፣ ሊቃውንቱን እየገፉ ከፍተኛ በደል በማድረስ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሀብቶችና ንብረቶች ለግል ጥቅም በማካበት የሚታወቁ ናቸው፡፡]
‹‹ሙሰኞችንና ጎሰኞችን ሰብስቦ ሙስናንና ጎሰኝነትን እታገላለኹ ማለት እንዴት ይቻላል?›› የሚሉት አስተያየት ሰጭዎቹ፣ ፓትርያርኩ በቤተ ክርስቲያኒቱ የመጨረሻ ውሳኔ ሰጭ አካል የኾነውን የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሥልጣን እስከ መጋፋት መድረሳቸውን በመጥቀስ ይህም ከግለሰቦቹ የኡለታዊ ምክር ተጽዕኖ ጋር የተያያዘ ሊኾን እንደሚችል ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል፡፡
ፓትርያርኩ ችግር መኖሩን እንጂ የችግሩ ፈጣሪዎች ተንኮል ምን እንደኾነ በትክክል ለመረዳትና ለማስረዳት ሲቸገሩ እንደሚስተዋል አስተያየት ሰጭዎቹ ይናገራሉ፡፡ ከወራት በፊት የእርምትና የማስተካከያ ርምጃ ለመውሰድ ‹‹እጅግ አስቸኳይ›› በሚል አቡነ ማትያስ ሲጠቀሙባቸው የቆዩ አነሣሽ ቃላት አኹን አኹን እየተዘነጉ የለውጥ እንቅስቃሴውን ለመምራትና ለማጠናከር የሚጣጣሩ ጳጳሳትና ባለሞያዎች በአማካሪነት ከተጠጉት ግለሰቦች ጋራ በተሳሰሩ የለውጡ ተቃዋሚዎች በፓትርያርኩ ፊት በግልጽ የሚዘለፉበት ኹኔታ መኖሩ ተጠቁሟል፡፡
የቤተ ክርስቲያኒቱ የተቋማዊ ለውጥ ጥረቶች የፓትርያርኩን የላቀ የአመራር ክህሎትና የውሳኔ ሰጭነት አቅም የሚጠይቁ እንደኾኑ የጠቁሙት ምንጮቹ፣ ከጽናትና አረዳድ አኳያ ይታይባቸዋል በሚባለው በተፈላጊው አቋም ያለመርጋትና የአቅም ውስንነት፣ ሊቃነ ጳጳሳቱና የመንግሥትም አካላት ጭምር ጥያቄ ማንሣት መጀመራቸው አያይዘው ገልጸዋል፡፡ የሊቀ ጳጳሱ አቡነ ኤልሳዕም ያልተጠበቀ ግልጽ ምክር ከዚህ ጥርጣሬ ሊመነጭ እንደሚችልና በቀጣይም የቅ/ሲኖዶሱ መነጋገርያ ሳይኾን እንደማይቀር በአስተያየት ሰጭዎቹ ተመልክቷል፡፡
About these ads

Wednesday, 5 March 2014

አሰግድ ሳህሉ ማነው ?



  • ‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ አሁንም በአብ ቀኝ ቆሞ ያማልዳል፤›› አሰግድ ሣህሉ
  • ‹‹የክርስቶስ ሥጋ እና ደም ተቀበልንም አልተቀበልንም ለውጥ የለውም›› አሰግድ ሣህሉ
  • ‹‹የእውነት ቃል አገልግሎት›› የተባለ የተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ድርጅት የመሠረተ ነው
  • ‹‹ሙሉ ወንጌል›› አማኞች የጸሎት ቤት በተካሄደው ጉባኤ ላይ ከመሰሎቹ ጋራ ተካፍሎ ሲወጣ ተደርሶበታል
የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ አራማጅ - አሰግድ ሣህሉ እንደ ማሳያ
አሰግድ ሣህሉ በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን የዉሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት የተሐድሶ ኑፋቄን ለማስፋፋት፣ አንዳንድ የሰንበት ት/ቤቱን ወጣቶች ከእናት ቤተ ክርስቲያን ወደ ‹‹ሙሉ ወንጌል›› አዳራሽ ለመውሰድ ሲያደርግ የቆየውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ በጥብቅ ሲከታተል በቆየው የሰንበት ት/ቤቱ ሥራ አመራር ኮሚቴ የተዘጋጀው ባለ 40 ገጽ ሰነድ ያስረዳል፡፡ እንደ ዘገባው ማብራሪያ አሰግድ ሣህሉ ከሚኖርበት ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 11/12 የቤት ቁጥር 417 በተለምዶ ቡልጋሪያተብሎ ከሚጠራው የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል - የከርቸሌው ሚካኤል አካባቢ ያለሰበካው ወደ ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን መጥቶ በዉሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት በ1985 ዓ.ም የተመዘገበው ሰንበት ት/ቤቱ በወቅቱ ያጋጠመውን የአገልግሎት መዳከም ተመልክቶ ስውር የተሐድሶ ኑፋቄ ተልእኮውን ለማራመድ እንዲያመቸው ነው፡፡


በሂደት የሰንበት ት/ቤቱ ‹‹የትምህርተ ሃይማኖት አስተማሪ››፣ የሥራ አመራር አባል እና የትምህርት ክፍል ሰብሳቢ እስከመሆን የደረሰው አሰግድ ወጣቶችን ከቤተ ክርስቲያን ጉያ በማውጣት የሚታወቁትን ግርማ በቀለ(ይህ ግለሰብ ከሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ት/ቤት በኑፋቄው በአባቶች ተወግዞ ከተባረረ በኋላ‹‹የእውነት ቃል አገልግሎት›› የተባለ የተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ድርጅት የመሠረተ ነው)፣ ‹‹አባ›› ዮናስ(በ1990 ዓ.ም. ሚያዝያ 28 ቀን ራሳቸውን ገልጠው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄያቸውን በአደባባይ በማስመስከራቸው ከቤተ ክህነትአዳራሽ ተወግዘው ከተለዩት አንዱ)፣ እነ ስዩም ያሚን ወደ ሰንበት ት/ቤቱ እየጋበዘ እንዲያስተምሩ አድርጓል፡፡

በ1986 ዓ.ም ነሐሴ ወር በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ አዘጋጅነት በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በተሰጠው የአንድ ወር ኮርስ ላይ ሰንበት ት/ቤቱን ወክሎ የተሳተፈው አሰግድ፣ ‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ አሁንም በአብ ቀኝ ቆሞ ያማልዳል፤›› በማለት በይፋ ይከራከር እንደነበርና በኮርሰኞቹ ምላሽ ይሰጠው እንደነበር ሰነዱ ያስታውሳል፡፡ ከዚህ በኋላ አሰግድን ጨምሮ በ1984 ዓ.ም ‹‹የተዳከመውን የቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤትን እናጠናክራለን›› በሚል ሽፋን የአጥቢያ ሰንበት ት/ቤታቸውን ትተው ከመጡ ሌሎች ሁለት ግለሰቦች(አሁን የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ሆነዋል) ጋራ እንዲታገዱ የሰንበት ት/ቤቱ ወጣቶች የደብሩን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አስተዳደር ይጠይቃሉ፡፡

በየጊዜው ይደረግ የነበረው የደብሩ አስተዳዳሪዎች መለዋወጥ ጥያቄው በወቅቱ ሰሚ አግኝቶ ርምጃ እንዳይወሰድ ዕንቅፋት ፈጥሮ እንደነበር የሚያመለክተው ሰነዱ፣ ጥቆማው ከቀረበላቸው የወቅቱ የደብሩ አስተዳዳሪዎች አንዱ የትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት ዋና አስኪያጅ ሊቀ ካህናት ብርሃኑ ገብረ ዐማኑኤል ሁኔታውን በመረዳት አሰግድን ጠርተው፣ ‹‹መማር ከፈለግህ እኔ ጋራ ቢሮዬ እየመጣህ አስተምርሃለሁ፤ ለጊዜው ግን ወደ ሰንበት ት/ቤት አትሂድ›› ብለው እንደመከሩት ገልጧል፡፡ በቢሯቸው ጠርተው ባነጋገሩበት ጊዜም ግለሰቡ የኑፋቄ ችግር እንዳለበት ቢረዱም ለሦስት ወራት ደብሩን አስተዳድረው በመቀየራቸው ርምጃ ሳይወሰድ መቅረቱን ዘግቧል፡፡

በዚህ ሁሉ መካከል ግን አሰግድ የተሐድሶ ኑፋቄ እንቅስቃሴ ይራመድባቸው በነበሩ የቤት ለቤት ጽዋ ማኅበራት እና በየአዳራሹ በሚካሄዱ ጉባኤያት እንደሚሳተፍ፣ ሰንበት ተማሪዎችንም እያግባባ እንደሚወስድ፣ ‹‹የክርስቶስ ሥጋ እና ደም ተቀበልንም አልተቀበልንም ለውጥ የለውም›› እያለ እንደሚቀስጥ፣ የካህናት አባቶችን ክብር እና ማዕርግ ንቆ ሲያበቃ ሌሎችም እንዲንቁት እንደሚቀሰቅስ መረጃው በመድረሱ የሰንበት ት/ቤቱ አመራር ይኸው በዐይን ምስክሮች ተገልጦ በጉባኤ እንዲመሰከርበት በማድረግ ያጋልጠዋል፡፡ ይህም በደብሩ አስተዳዳሪ አማካይነት ለሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ቀርቦ ከታየ በኋላ ጥቅምት 10 ቀን 1988 ዓ.ም ከሰበካ ጉባኤው ጽ/ቤት በተጻፈ ደብዳቤ አሰግድ ከሰንበት ት/ቤቱ ሊታገድ ችሏል፡፡

አሰግድ ግን ‹‹ያለአግባብ ከሰንበት ት/ቤቱ ታግጃለሁ፤ ዳኝነት ይታይልኝ›› ብሎ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ያመለክታል፡፡ ሀገረ ስብከቱ ጉዳዩን እንዲያጣሩ የላካቸው ሁለት ልኡካንም መጋቢት 23 ቀን 1988 ዓ.ም የደብሩ የስብከተ ወንጌል ኮሚቴ የወከላቸው አራት አባላት ባሉበት በአሰግድ ላይ ማስረጃ ባቀረቡት የሰንበት ት/ቤቱ ተወካዮች ጠያቂነት አሰግድ እየመለሰ በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ በጥያቄ እና መልስ የታገዘ ውይይት ይደረጋል፡፡ በውይይቱ ላይ የሀገረ ስብከቱ ተወካዮች አሰግድን፣ ‹‹በአንደበትህ ከተናገርከው ቃል በቂ ማስረጃ ይዘንብሃል፤ ስለምን ጥፋትህን አታምንም?›› ይሉታል፡፡ በወቅቱ የደብሩ አስተዳዳሪ የነበሩት ቆሞስ አባ ሀብተ ሚካኤል ታደሰም፣ ‹‹አሰግድ ጥፋትህን እመንና ቀኖና እንሰጥሃለን፤ እባክህ ብትመለስ ይሻልሃል፤›› በማለት ይማፀኑታል፡፡ ልቡን እንደ እብነ አድማስ ያደነደነው አሰግድም የስብሰባው ቃለ ጉባኤ እና የደብሩ አስተዳደር የውሳኔ መነሻ ወደ ሀገረ ስብከቱ ሳይላክ፣ ‹‹እኔ ተሐድሶ አይደለሁም፤ እኔ ራሴን የማውቀው የቤተ ክርስቲያን ዶግማ እና ቀኖና ጠንቅቄ መኖሬን ነው፤ ነገር ግን እናንተ የለም ተሐድሶ ነህ ካላችሁኝ ክፉ እና ደጉን ከለየሁበትና ከአደግሁበት ሰንበት ት/ቤት መለየት አልፈልግምና ቀኖና ተሰጥቶኝ እንድመለስ በልዑል እግዚአብሔር ስም አመለክታለሁ፤›› ብሎ ለደብሩ ደብዳቤ ይጽፋል፡፡

የደብሩ አስተዳደር በዕለቱ የተደረገውን ውይይት እና የደብሩን አስተያየት በማካተት ለሀገረ ስብከቱ ይልካል፡፡ ሀገረ ስብከቱም ልኡካኑ ያቀረቡትን ሪፖርት፣ የደብሩን አስተያየት እና አሰግድ ለደብሩ የጻፈውን ደብዳቤ በማገናዘብ፣ ‹‹ከቀኖና አንዱ አመክሮ ስለሆነ ወደ ሰንበት ት/ቤቱ ከመመለሱ በፊት እንደማንኛውም አማኝ ለተወሰነ ጊዜ በስብከተ ወንጌል ትምህርት እየተማረ እንዲቆይ›› የሚል ውሳኔ በቁጥር 2/58/37/88 ቀን 11/11/88 ዓ.ም በወቅቱ ሥራ አስኪያጅ በነበሩት መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ገብረ ሚካኤል በየነ(አሁን ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ) ፊርማ ያስተላልፋል፡፡ ይህን ውሳኔ የደብሩ አስተዳደር በቁጥር 63/534/88 በቀን 29/11/88 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ለአሰግድ ያሳውቀዋል፡፡ የውሳኔውን ተገቢነት አስመልክቶ በዘገባው ላይ የሚከተለው አስተያየት ሰፍሯል፡- ‹‹እዚህ ላይ በጣም የሚያሳዝነው በቤተ ክርስቲያን ላይ ኑፋቄ ለሚዘራ፣ ወጣቶችን ከእናት ቤተ ክርስቲያን ለሚያስኮበልል፣ ቅዱሳንን እና የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ለሚንቅ፣ ቅዱስ ቁርባን አያድንም ብሎ ለሚያስተምር ሰው የንስሐ አባቱ ቀኖና እንዲሰጡት እና የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት እግር ሥር ተቀምጦ እንዲማር አባቶች እንዲመደቡለት አለመደረጉ ነው፤ የተሰጠው ቀኖና እና አመክሮ ለአንድ ወር ብቻ በማታው የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር እየተገኘ እንዲማር ነው፡፡››

ሆኖም አሰግድ ይህ ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ በማታው የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር ይሁን በዕለተ ሰንበት ቅዳሴ ለአንድም ጊዜ ስንኳ ተምሮም አስቀድሶም እንደማያውቅ በሰንበት ት/ቤቱ የተመደቡት የክትትል ቡድን አባላት ማረጋገጣቸውን ዘገባው ያስረዳል፡፡ የተባለው አንድ ወር ሲደርስ ግን ከቀኗ አንዲት ሳያሳልፍ(በ29/12/88 ዓ.ም) ለደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ‹‹በሥራ ምክንያት አልፎ አልፎ በስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር ላይ ባልገኝም በአብዛኛው ጊዜ ግን ተገኝቼ ተምሬያለሁና የተሰጠኝ የጊዜ ገደብ ስለተጠናቀቀ ወደ ሰንበት ት/ቤት ለመግባት ሙሉ ፈቃዳችሁን እንድትገልጹልኝ እጠይቃለሁ›› የሚል ደብዳቤ ያስገባል፤ ይህንኑም ለሰንበት ት/ቤቱ አባላት ያስወራል፡፡

እውነቱ ግን አሰግድ ቀኖናውን ተቀብዬ እንደታዘዝሁት ፈጽሜያለሁ ባለ ማግሥት ከጳጉሜ 1 - 5 ቀን 1988 ዓ.ም ለአምስት ተከታታይ ቀናት አሁን በፈረሰው የጎተራ ማሳለጫ ፊት ለፊት በሚገኘው የጎተራ ‹‹ሙሉ ወንጌል›› አማኞች የጸሎት ቤት በተካሄደው ጉባኤ ላይ ከመሰሎቹ ጋራ ተካፍሎ ሲወጣ መረጋገጡ ነው፡፡ ይህን መነሻ በማድረግ 55 የሰንበት ት/ቤቱ አባላት አሰግድ የለየለት መናፍቅ በመሆኑ ከሰንበት ት/ቤቱ እንዲታገድ እንጂ ወደ ሰንበት ት/ቤቱ እንዳይመለስ የሚጠይቀውን አቤቱታቸውን በፊርማቸው በማረጋገጥ ለሰንበት ት/ቤቱ ሥራ አመራር ኮሚቴ ያቀርባሉ፡፡ ኮሚቴውም ይህንኑ ካጣራ በኋላ ሐሳቡን በማጽናት ለደብሩ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ያስታውቃል፡፡

በዚህ ውሳኔ ኀይል ከአንድ ዓመት በላይ ወደ ደብሩ ሳይገባ ዙሪያውን ሲያንዣብብ የቆየው አሰግድ የደብሩ አስተዳዳሪ፣ የሰበካ ጉባኤ አባላት እና የደብሩ ዋና ጸሐፊ መቀየራቸውን ሲያረጋግጥ በተለይ አዲስ የተመደበው የሰበካ ጉባኤ ጸሐፊ እንደሚረዳው ሲተማመን ለአዲሱ የደብሩ አስተዳዳሪ ‹‹ወደ ሰንበት ት/ቤቱ ልመለስ›› ሲል ጥያቄውን አቀረበ፤ የደብሩ ዋና ጸሐፊም የደብሩን አስተዳዳሪ ስላሳመነለት ‹‹አሰግድ ቀኖናውን ስለጨረሰ ወደ ሰንበት ት/ቤት ይመለስ›› የሚል ደብዳቤ ተጻፈለት፡፡ ይህን ውሳኔ የሰማው የሰንበት ት/ቤቱ አመራርም ‹‹በእውነት ከልቡ አምኖበት፣ እስከ ዛሬ የመናፍቃንን ስውር ዓላማ ማራመዱ ጸጽቶት ቀኖናውን ከፈጸመ ወደ ሰንበት ት/ቤቱ ከመመለሱ በፊት በስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር እና ከዕለተ ሰንበት ቅዳሴ በኋላ እስከ ዛሬ ሲያካሂድ የነበረውን የመናፍቃን ድብቅ ሤራ በይፋ እንዲገልጥ›› የሚጠይቅ ደብዳቤ ለደብሩ ጽ/ቤት ይልካል፡፡

በወቅቱ የደብሩ አስተዳዳሪ የነበሩት መልአከ ይባቤ ተስፋ ሚካኤል መርሻ በአንድ የሰንበት ቅዳሴ ቀን አሰግድን አጠገባቸው አቁመው፣ ‹‹ምእመናን፣ ይህ የምትመለከቱት ልጅ አስቀድሞ የተሐድሶ አራማጅ ነበር፤ አሁን ግን ጥፋቱን አምኖ ቀኖናውን ተቀብሏል፤ ምእመናን እልል በሉ፤›› ሲሉ ተናገሩ፡፡ አሰግድም ጥፋቱን አምኖ ቀኖናውን ፈጽሞ መመለሱን እንዲናገር ዕድል ሲሰጠው፣‹‹ምእመናን፡- እኔ ተሐድሶ አይደለሁም፤ እኔ የቤተ ክርስቲያን ዶግማ እና ቀኖና ጠንቅቄ የምኖር ነኝ፤ ነገር ግን አንዳንዶች ስሜን ሲያጠፉ ነው፤›› ብሎ የአዞ እምባውን ለቀቀው፤ ምእመናንም የደብሩ አስተዳዳሪ በተናገሩት እና አሰግድ በሰጠው የአባይ ምስክርነት ግራ ቢጋቡም በማልቀሱ ግን አዘኑለት፡፡ የሰንበት ት/ቤቱ ሥራ አመራር አባላት ግን ‹‹የፈለገው ነገር ቢመጣ እኛን ያስወጡን እንጂ እርሱ ወደ ሰንበት ት/ቤት አይገባም›› ብለው በአቋማቸው ጸኑ፡፡

ሁኔታውን አስመልክቶ የዘገባው አጠናቃሪ፣ ‹‹የአሰግድ ዋና ዓላማ ለምእመናን የተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ አለመሆኑን ተናግሮ ስሙን ለማደስ እንዲሁም ለእርሱ እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነውን በደብሩ አስተዳዳሪ የተጻፈለትን ቀኖናውን ስለጨረሰ ወደ ሰንበት ት/ቤት ይመለስ የሚለውን ደብዳቤ መያዝ እንጂ ወደ ሰንበት ት/ቤቱ መመለስ አልነበረም፤›› ብለዋል፡፡ ዘጋቢው እንዳሉትም ውስጠ ተኩላው አሰግድ የልቡን ከፈጸመ በኋላ እስከ 1996 ዓ.ም ድረስ ለአምስት ዓመታት ወደ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ደርሶ እንደማያውቅ ተገልጧል፡፡ ይሁንና ከዚያ በኋላ በተመሳሳይ የኑፋቄ ተግባሩ ከጃቴ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያንም እንደተባረረ የደብሩ አስተዳዳሪ የነበሩት ቆሞስ አባ ክፍለ ዮሐንስ ለመልአከ ይባቤ ተስፋ ሚካኤል መርሻ የነገሯቸውን ምስክርነት ዘገባው አስፍሯል፡፡ በዚህም መልአከ ይባቤ ተስፋ ሚካኤል ቀደም ሲል አሰግድ ቀኖናውን ፈጽሞ ወደ ሰንበት ት/ቤቱ እንደተመለሰ በቀናነት ለሰንበት ት/ቤቱ የጻፉትን ደብዳቤ ለመሻር ወስነው የሰንበት ት/ቤቱን ጥያቄ ሲጠባበቁ ከአስተዳዳሪነታቸው መነሣታቸውን ዘገባው በቁጭት ያስታውሳል፡፡

ከዚህ በኋላ ወደ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በማታው ክፍለ ጊዜ ገብቶ በዲፕሎማ መርሐ ግብር መማር የጀመረው አሰግድ በክፍል ውስጥ በጥራዝ ነጠቅ የኑፋቄ ሐሳቦች መምህራኑን እና ደቀ መዛሙርቱን መነትረክ በመጀመሩ የግለሰቡን ዓላማ እና ተልእኮ የሚያጠና ሦስት ደቀ መዛሙርት የሚገኙበት ኮሚቴ ይቋቋማል፡፡ ይህን ተከትሎ አሰግድ ትምህርቱን ‹‹ሲያጠናቅቅ›› በኮሌጁ ዲፕሎማው ሳይሰጠው ተይዞበት ይቆያል፡፡ ዘገባው እንደሚለው፣ እንዴት እንደተፈጸመ በማይታወቅ አኳኋን አሰግድ የተያዘበትን ዲፕሎማ ከኮሌጁ ቆይቶ ተቀብሏል፡፡

በ2003 ዓ.ም በዲግሪው መርሐ ግብር ትምህርቱን በማታው ክፍለ ጊዜ ለመቀጠል ለኮሌጁ ያመለከተው አሰግድ፣ ከነበረበት ደብር የአስተዳዳሪው ወይም የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ፊርማ እና ማኅተም ያረፈበት፣ በአገልግሎት ላይ ስለመሆኑና ተመርቆ ሲወጣ ቤተ ክርስቲያኒቱን ተመልሶ እንደሚያገልግል ዋስትና የሚሰጥ ደብዳቤ እንዲያቀርብ ይጠየቃል፡፡ ይሁንና የደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ማንነቱን በውል የሚያውቅ በመሆኑ የትብብር ደብዳቤውን ስለማይጽፍለት፣ ቀሲስ አስቻለው መሐሪ የተባሉ ግብር አበሩን በመላክ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ አባል መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ለቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲጻፍለት ኅዳር አንድ ቀን 2003 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ይጠይቃል፡፡

ደብዳቤውን የተመለከተው የወቅቱ የደብሩ ዋና ጸሐፊ ዲያቆን ክብረ በዓል ዐሥራትም ከደብሩ አስተዳዳሪ እና ከሰንበት ት/ቤቱ አመራር ጋራ አሰግድን በተመለከተ በቂ መረጃ ጠይቆ ለማግኘት ቢችልም ይህን ጥረት ሳያደርግ ራሱን ከተጠያቂነት ነጻ ለማድረግ ብቻ፣ አሰግድ የአራት ዓመት(ከ2000 - 2003 ዓ.ም) የሰበካ ጉባኤ ውዝፍ(ብር 96) እንዲከፍል በማድረግ በ01/03/2003 ዓ.ም ያስገባውን የትብብር መጠየቂያ ደብዳቤ ዕለቱኑ ‹‹የንስሐ አባቱ ነኝ›› ላሉት ቀሲስ ተጠምቀ አስፍሓ አስተያየት እንዲሰጡበት ይመራላቸዋል፡፡ የንስሐ አባቱም ‹‹በእኔ ንስሐ አባትነት የተመዘገበ እና የሰበካ ጉባኤ ክፍያውንም ወቅቱን ጠብቆ እየከፈለ መሆኑን አረጋግጣለሁ›› በማለት በውክልና በተላከላቸው ደብዳቤ ላይ ይፈርማሉ፡፡ ዘገባው አሰግድ በርቀት(በውክልና በመላላክ) የንስሐ አባቱን እና የደብሩን ዋና ጸሐፊ በማግባባት ዓላማውን ለማሳካት የሞከረበትን መንገድ ሲያስረዳ፣ ‹‹ከአፅራረ ቤተ ክርስቲያን በሚጎርፍለት የገንዘብ ድጋፍ በመደለል›› ሊሆን እንደሚችል የደጀ ሰላምንዜና በመጥቀስ ያስረዳል፡፡

በመጨረሻም በደብሩ ዋና ጸሐፊ በዲያቆን ክብረ በዓል ዐሥራት ፊርማ አሰግድ በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ‹‹የንስሐ አባት ይዞ፣ ተገቢውን የአባልነት ክፍያ አሟልቶ የሚገኝ መሆኑን›› በመግለጽ ለቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በቁጥር 200/88/03 በቀን 06/03/03 የትብብር ደብዳቤ ተጽፎ በቀሲስ አስቻለው መሐሪ በኩል ተላከለት፡፡ ይህ በቅሰጣ የተገኘ የተልእኮ ደብዳቤ ግን በኮሌጁ የበላይ ሐላፊ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም፡፡

ስለሆነም አሰግድ ዐይኑን በጨው አጥቦ ራሱ ደብሩ ድረስ በመሄድ አስተዳዳሪውን መልአከ ገነት በቀለ ዘውዴን የትብብር ደብዳቤ እንዲጽፉለት ይጠይቃቸዋል፡፡ እርሳቸውም ዋና ጸሐፊው ያለእርሳቸው ዕውቅና በራሱ ፊርማ የጻፈለትን ደብዳቤ ሲመልስ የጠየቀውን ደብዳቤ እንደሚጽፉለት በብልኀት ይነግሩታል፡፡ ብልጡ አሰግድም የደብዳቤውን ኦሪጅናሌ ሳይሆን ቅጅውን ያቀርባል፡፡ ብልጥ አላንድ ቀን አይበልጥምና አስተዳዳሪው መልአከ ገነት በቀለ ዘውዴም ‹‹ዋናውን የማታመጣ ከሆነ ከዛሬ ጀምሮ እንዳትመጣ›› ብለው አሳፍረው ሸኝተውታል፡፡ በቁጥር 417/666/03 በቀን 17/05/03 ዓ.ም ለቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በጻፉት ደብዳቤም ‹‹የአሰግድ ንስሐ አባት ነኝ›› ያሉት ካህን አስተያየታቸውን በመግለጽ በአድራሻ ቁጥር 200/88/03 በቀን 06/03/2003 ዓ.ም ለኮሌጁ ያስተላለፉት መልእክት መሻሩን አሳውቀዋል፡፡
አሰግድ ቀደም ሲል ወደ ምሥራቀ ፀሐይ ቀበና መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሄዶ የነበረ ቢሆንም የአጥቢያው አባልም አገልጋይም ባለመሆኑ የትብብር ደብዳቤ ሊጻፍለት እንደማይችል በአስተዳዳሪው ተነግሮት መመለሱን ይታወሳል -የኦርቶዶክሳውያኑ አባቶች እና ወጣቶች ቀናዒነት እና መተባበር ምሳሌነት ያለው ሲሆን የተሐድሶ ኑፋቄ አቀንቃኙ አሰግድ ሣህሉ ጥውየት(ክፋት እና ጥመት) እንዲሁም ኀፍረተ ቢስነት ደግሞ እግዚኦ የሚያሰኝ ነው!!

Tuesday, 4 March 2014

ፓትርያርኩ ከአማሳኞችና ጎሰኞች ጋራ ተዋርደው ከመምከር እንዲታቀቡና በዐደባባይ ቃል የገቡበትን ተቋማዊ ለውጥ በተግባር እንዲያስፈጽሙ ሊቃነ ጳጳሳቱ አሳሰቧቸው

His Grace Abune Elsa on 32 SGGA
ብፁዕ አቡነ አልሳዕ
  • ‹‹ቅዱስነትዎ÷ ይህን ታላቅ ሓላፊነት ሲቀበሉ ቅ/ሲኖዶስ አዲስ ዋና ጸሐፊ፣ አዲስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርጎ ሰጥዎታል፤ መምከር ያለብዎ ከእነርሱ ጋራ ነው፤ ከዚያም ካለፈ ከቋሚ ሲኖዶሱ ነው፤ አስፈላጊ ከኾነም ጠቅላላው ጉባኤው ይሰበሰባል፡፡ እርስዎ ግን ወርደው ከማን ጋራ ነው እየተማከሩ ያሉት?››
  • ‹‹በአገራችን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በመላው ኢትዮጵያ ሲያገለግሉ ከየት መጣኽ አልተባባሉም፤ ከሥራ ወንድምችዎ ጋራ ከየት መጣኽ ሳንባባል በአንድነት እየተመካከርን ነው ማገልገል ያለብን፤ ከዚያ ወርደን መገኘት የለብንም፡፡››
  • ‹‹የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት በመጀመሪያ ቅዱስ ወንጌል ከዚያ የሐዋርያት፣ የሊቃውንት እያሉ ነው የሚቀጥሉት፤ እርስዎም ከብፁዕ ዋና ጸሐፊ፣ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ከቋሚ ሲኖዶስ፣ ከምልዓተ ጉባኤ ጋራ ነው፡፡ ከዚያ ሲወርድ ግን ከሊቃውንት መጽሐፍም ወርዶ ልቦለድ መጽሐፍ እንደ ማንበብ ነው!!›› /ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ የሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ/
His Grace gen sec of the patriarchate Abune Mathewos speaking on the enthronment anniv.
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ማቴዎስ
  • ‹‹እግዚአብሔር ለሚወደው ሕዝብ ነቢይ ኾኖ ትንቢት የሚነግራቸውን፣ አስተዳዳሪ ኾኖ የሚመራቸውን፣ ኖላዊ ኾኖ የሚጠብቃቸውን አባት ያዘጋጅላቸዋል፤ የዛሬው ቀን ይህን እግዚአብሔር የሚወደውን ሕዝብ ለቅዱስነትዎ ያስረከበበት ቀን ነው፡፡››
  • ‹‹የዛሬው ቀን ለቤተ ክርስቲያን ችግሯን ፈቺ፣ ለዕድገቷ ፕላን አውጪ፣ ለአስተዳደሯ መመሪያ ሰጪ ለመኾን በዐደባባይ ቃል የገቡበት ቀን ስለኾነ በታላቅ አክብሮትና ደስታ እናስታውሰዋለን፡፡ ራስን ለሌላው አሳልፎ መስጠት በቀላል አይመጣም፤ የልብ መሻትና መሠበርን ይፈልጋል፤ ማዕርግ ከነክብሩ፣ ሥልጣን ከነእውነቱ፣ መስቀል ከነትዕግሥቱ ካልተሰጠ አይቻልም፡፡ /ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ/
His Holiness giving benediction on the day of His enthronment
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ
  • ‹‹የዛሬ ዓመት የተናርኋቸው ቃላት ኹሉ እንደጸኑ ናቸው፤ አልተበረዙም፤ አልተከለሱም፤ እንዲያውም ከቅ/ሲኖዶስ አባላት፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ከምእመናን ጋራ በመኾን አጠናክራቸዋለኹ፡፡››
  • ‹‹የቤተ ክርስቲያን ጥሪ በምድር ላይ ለመከራ መስቀል እንጂ ለተድላ ሥጋ አይደለም፤ ተድላውና ደስታው የተዘጋጀው በላይኛው ዓለም ነው፤ የቤተ ክርስቲያን መሪ፣ አገልጋይና ተከታይ የኾነ ኹሉ በውል መገንዘብ ያለበት ይህን ነው፤ የተጠራነው ለሰማያዊ ሀብትና ሹመት እንጂ እንደ ሣር ቅጠል ለጊዜው ታይቶ ለሚጠፋ ምድራዊ ሀብትና ሥልጣን አይደለም፡፡››
  • ‹‹የቤተ ክርስቲያናችን አሠራር እንዳይቃና እየተጠላለፉና እየተመሰቃቀሉ ብዙ እንዳንራመድ የሚያደርጉን ምክንያቶች ከማንም ይኹን ከየት ምንጫቸው ከፍቅረ ንዋይና ከፍቅረ ሢመት ውጭ ናቸው የሚል ግንዛቤ የለም፤ ለእነዚኽ ደግሞ ቁልፍ መፍትሔያቸው ራስን ክዶ መስቀልን ለመሸከም በቁርጥ ከመነሣት በቀር ሌላ ሊኾን አይችልም፡፡ እኛ የቤተ ክርስቲያናችን ተጠሪዎች ሥራችን ሊቃና፣ ተደማጭነታችን ሊሰፋ፣ ተልእኳችን ሊሠምር፣ ሕዝባችን ሊያምነንና ሊከተለን የሚችለው የጌታችንን ቃል አክብረንና ራሳችንን ክደን ለእውነት የቆምን እንደኾን ብቻ ነው፡፡››
  • ‹‹ባሳለፍነው የአንድ ዓመት ጉዞ ቅ/ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያናችን በዕቅድ እንድትመራ፣ የቤተ ክርስቲያን ሀብትና ንብረት እንዳይባክን በዘመናዊ አያያዝ እንዲያዝ፣ መልካም አስተዳደር፣ ፍትሕና ርትዕ፣ እኩልነት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ከመወሰን ባሻገር ይህን በሕግ ማህቀፍ፣ በደንብና በመመሪያ አጠናክራ ለመሥራት በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና በዕውቅ ምሁራን አማካይነት ልዩ ልዩ ጥናቶችን እያካሔደች ትገኛለች፡፡ ይህ የተጀመረው የአሠራር ለውጥ ተፈጽሞ ሲታይ ኹሉን እንደሚያስደስት ጥርጥር የለውም፤ ቤተ ክርስቲያናችን በሕግና በሥርዐት ስትመራ፣ የቤተ ክርስቲያናችን ኢኮኖሚ ጠንካራ ይኾናል፤ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎታችንም ለሕዝበ ክርስቲያን በአግባቡ ተደራሽ ይኾናል፡፡ እነዚኽን ዐበይት ጉዳዮች ከሥራ ላይ ለማዋል የኹሉም ቀና መንፈስና ትብብር ያስፈልጋል፤ ራስን መካድ ያስፈልጋል፡፡›› /ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ/
*                                  *                                  *
  • ለአንደኛ ዓመት በዓለ ሢመት አከባበር በእንግሊዝኛ የወጣው የመርሐ ግብሩ ዝርዝር የታየበት የአጻጻፍ ውስንነትና የእውነታ ስሕተት በታዳሚዎች ተተቸ – ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን “the 1st patriarch of the Ethiopia Orthodox Tewahido Church” ያደርጋቸዋል፤  ‹‹Message from the Acting patriarch of EOTC” የሚል መርሐ ግብርም አለው! የሰዓት አገላለጹማ….
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የኾኑት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ባለቤ ለቤተ ክርስቲያን በማይገባ አለባበስ (በአጭር ቀሚስ) የበዓለ ሢመቱ እንግዳ መኾናቸው ቅሬታ ፈጥሯል፡፡

ፓትርያርኩ ከአማሳኞችና ጎሰኞች ጋራ ተዋርደው ከመምከር እንዲታቀቡና በዐደባባይ ቃል የገቡበትን ተቋማዊ ለውጥ በተግባር እንዲያስፈጽሙ ሊቃነ ጳጳሳቱ አሳሰቧቸው

His Grace Abune Elsa on 32 SGGA
ብፁዕ አቡነ አልሳዕ
  • ‹‹ቅዱስነትዎ÷ ይህን ታላቅ ሓላፊነት ሲቀበሉ ቅ/ሲኖዶስ አዲስ ዋና ጸሐፊ፣ አዲስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርጎ ሰጥዎታል፤ መምከር ያለብዎ ከእነርሱ ጋራ ነው፤ ከዚያም ካለፈ ከቋሚ ሲኖዶሱ ነው፤ አስፈላጊ ከኾነም ጠቅላላው ጉባኤው ይሰበሰባል፡፡ እርስዎ ግን ወርደው ከማን ጋራ ነው እየተማከሩ ያሉት?››
  • ‹‹በአገራችን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በመላው ኢትዮጵያ ሲያገለግሉ ከየት መጣኽ አልተባባሉም፤ ከሥራ ወንድምችዎ ጋራ ከየት መጣኽ ሳንባባል በአንድነት እየተመካከርን ነው ማገልገል ያለብን፤ ከዚያ ወርደን መገኘት የለብንም፡፡››
  • ‹‹የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት በመጀመሪያ ቅዱስ ወንጌል ከዚያ የሐዋርያት፣ የሊቃውንት እያሉ ነው የሚቀጥሉት፤ እርስዎም ከብፁዕ ዋና ጸሐፊ፣ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ከቋሚ ሲኖዶስ፣ ከምልዓተ ጉባኤ ጋራ ነው፡፡ ከዚያ ሲወርድ ግን ከሊቃውንት መጽሐፍም ወርዶ ልቦለድ መጽሐፍ እንደ ማንበብ ነው!!›› /ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ የሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ/
His Grace gen sec of the patriarchate Abune Mathewos speaking on the enthronment anniv.
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ማቴዎስ
  • ‹‹እግዚአብሔር ለሚወደው ሕዝብ ነቢይ ኾኖ ትንቢት የሚነግራቸውን፣ አስተዳዳሪ ኾኖ የሚመራቸውን፣ ኖላዊ ኾኖ የሚጠብቃቸውን አባት ያዘጋጅላቸዋል፤ የዛሬው ቀን ይህን እግዚአብሔር የሚወደውን ሕዝብ ለቅዱስነትዎ ያስረከበበት ቀን ነው፡፡››
  • ‹‹የዛሬው ቀን ለቤተ ክርስቲያን ችግሯን ፈቺ፣ ለዕድገቷ ፕላን አውጪ፣ ለአስተዳደሯ መመሪያ ሰጪ ለመኾን በዐደባባይ ቃል የገቡበት ቀን ስለኾነ በታላቅ አክብሮትና ደስታ እናስታውሰዋለን፡፡ ራስን ለሌላው አሳልፎ መስጠት በቀላል አይመጣም፤ የልብ መሻትና መሠበርን ይፈልጋል፤ ማዕርግ ከነክብሩ፣ ሥልጣን ከነእውነቱ፣ መስቀል ከነትዕግሥቱ ካልተሰጠ አይቻልም፡፡ /ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ/
His Holiness giving benediction on the day of His enthronment
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ
  • ‹‹የዛሬ ዓመት የተናርኋቸው ቃላት ኹሉ እንደጸኑ ናቸው፤ አልተበረዙም፤ አልተከለሱም፤ እንዲያውም ከቅ/ሲኖዶስ አባላት፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ከምእመናን ጋራ በመኾን አጠናክራቸዋለኹ፡፡››
  • ‹‹የቤተ ክርስቲያን ጥሪ በምድር ላይ ለመከራ መስቀል እንጂ ለተድላ ሥጋ አይደለም፤ ተድላውና ደስታው የተዘጋጀው በላይኛው ዓለም ነው፤ የቤተ ክርስቲያን መሪ፣ አገልጋይና ተከታይ የኾነ ኹሉ በውል መገንዘብ ያለበት ይህን ነው፤ የተጠራነው ለሰማያዊ ሀብትና ሹመት እንጂ እንደ ሣር ቅጠል ለጊዜው ታይቶ ለሚጠፋ ምድራዊ ሀብትና ሥልጣን አይደለም፡፡››
  • ‹‹የቤተ ክርስቲያናችን አሠራር እንዳይቃና እየተጠላለፉና እየተመሰቃቀሉ ብዙ እንዳንራመድ የሚያደርጉን ምክንያቶች ከማንም ይኹን ከየት ምንጫቸው ከፍቅረ ንዋይና ከፍቅረ ሢመት ውጭ ናቸው የሚል ግንዛቤ የለም፤ ለእነዚኽ ደግሞ ቁልፍ መፍትሔያቸው ራስን ክዶ መስቀልን ለመሸከም በቁርጥ ከመነሣት በቀር ሌላ ሊኾን አይችልም፡፡ እኛ የቤተ ክርስቲያናችን ተጠሪዎች ሥራችን ሊቃና፣ ተደማጭነታችን ሊሰፋ፣ ተልእኳችን ሊሠምር፣ ሕዝባችን ሊያምነንና ሊከተለን የሚችለው የጌታችንን ቃል አክብረንና ራሳችንን ክደን ለእውነት የቆምን እንደኾን ብቻ ነው፡፡››
  • ‹‹ባሳለፍነው የአንድ ዓመት ጉዞ ቅ/ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያናችን በዕቅድ እንድትመራ፣ የቤተ ክርስቲያን ሀብትና ንብረት እንዳይባክን በዘመናዊ አያያዝ እንዲያዝ፣ መልካም አስተዳደር፣ ፍትሕና ርትዕ፣ እኩልነት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ከመወሰን ባሻገር ይህን በሕግ ማህቀፍ፣ በደንብና በመመሪያ አጠናክራ ለመሥራት በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና በዕውቅ ምሁራን አማካይነት ልዩ ልዩ ጥናቶችን እያካሔደች ትገኛለች፡፡ ይህ የተጀመረው የአሠራር ለውጥ ተፈጽሞ ሲታይ ኹሉን እንደሚያስደስት ጥርጥር የለውም፤ ቤተ ክርስቲያናችን በሕግና በሥርዐት ስትመራ፣ የቤተ ክርስቲያናችን ኢኮኖሚ ጠንካራ ይኾናል፤ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎታችንም ለሕዝበ ክርስቲያን በአግባቡ ተደራሽ ይኾናል፡፡ እነዚኽን ዐበይት ጉዳዮች ከሥራ ላይ ለማዋል የኹሉም ቀና መንፈስና ትብብር ያስፈልጋል፤ ራስን መካድ ያስፈልጋል፡፡›› /ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ/
*                                  *                                  *
  • ለአንደኛ ዓመት በዓለ ሢመት አከባበር በእንግሊዝኛ የወጣው የመርሐ ግብሩ ዝርዝር የታየበት የአጻጻፍ ውስንነትና የእውነታ ስሕተት በታዳሚዎች ተተቸ – ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን “the 1st patriarch of the Ethiopia Orthodox Tewahido Church” ያደርጋቸዋል፤  ‹‹Message from the Acting patriarch of EOTC” የሚል መርሐ ግብርም አለው! የሰዓት አገላለጹማ….
  • የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የኾኑት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ባለቤ ለቤተ ክርስቲያን በማይገባ አለባበስ (በአጭር ቀሚስ) የበዓለ ሢመቱ እንግዳ መኾናቸው ቅሬታ ፈጥሯል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ይከታተሉ፡

Monday, 3 March 2014

የፓትርያርኩ የለውጥ ተግዳሮትና ተስፋ – በአንደኛ ዓመት በዓለ ሢመት ዋዜማ


Abune Mathias 1st anniv. enthronment
  • የብልሹ አሠራርና ሙስናን ችግር በዐደባባይ የተናገሩ የመጀመሪያው ፓትርያርክ ናቸው
  • ጽኑ አቋም ስለሚጎድላቸው ለጣልቃ ገብነት የተመቹ ኾነዋል
  • ጣልቃ ገብነቶችን መቋቋምና የቅ/ሲኖዶሱን ልዕልና ማስከበር ይጠበቅባቸዋል
  • የተጠጓቸውን ‹አማካሪዎች› ማንነት መለየትና ዙሪያቸውን መፈተሽ አለባቸው
  • የተሟላና ብቃት ያለው የአማካሪ መዋቅር ያስፈልጋቸዋል
(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፫ ቁጥር ፯፻፴፯፤ የካቲት ፳፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)
Admas logoየካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም.፤ ለስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ምርጫ ከቀረቡት አምስት ዕጩዎች መካከል በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማትያስ በከፍተኛ ድምፅ መመረጣቸው ተነገረ፡፡ ሊቀ ጳጳሱ በቤተ ክርስቲያኒቱ የፓትርያርኮች ምርጫ ታሪክ ከፍተኛውን የመራጮች ድምፅ በማግኘት አሸናፊ መኾናቸው በተገለጸበት ወቅት የብዙዎችን ትኩረት በሳበ ኹኔታ በመስቀላቸው ሲያማትቡ ታዩ፡፡
የወቅቱን ስሜታቸውን አስመልክቶ ‹‹ዜና ቤተ ክርስቲያን›› በተሰኘው መጽሔት ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ÷ ‹‹ፓትርያርክ እኾናለሁ የሚል መንፈስ በውስጤ ስላልነበረ ውጤቱ ሲገለጽ፣ እንዴት ነው ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ምንድን ነው ከሚል ደነገጥኹኝ፤ በዚያው ቅጽበት የተሰማኝ፣ እግዚአብሔር ይህን ታላቅ ሓላፊነት እንዴት እችለዋለሁ? በል አንተ ታውቃለህ፤›› የሚል እንደነበር አስረድተዋል፡፡
ከምርጫው ሦስት ቀናት በኋላ የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም. በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተከናወነው ሥርዐተ ሢመት÷ ለፓትርያርክነት መመረጣቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ጥሪ እንደኾነና ጥሪውን የተቀበሉት መኾኑን፣ መቀበላቸውም ለክብርና ለልዕልና ሳይኾን ለመሥዋዕት በመታዘዝ በመኾኑ የቅዱስ ሲኖዶሱን አባላት በመያዝ በጋራ እንደሚወጡት ያላቸውን እምነት ተናግረው ነበር፡፡
ፓትርያርኩ በዚያ ንግግራቸው ‹‹ቅዱስ ሲኖዶሱ በራሱ መተማመን አለበት›› ሲሉ በአጽንዖት የተናገሩ ሲኾን እንደ አንድ ልብ አሳቢ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾኖ በሥምረት ከሠራ፣ ችግር ይኖራል ብለው እንደማያምኑ ገልጸዋል፡፡ በቅ/ሲኖዶሱ ሊሠሩ ይገባል በሚል ካሳወቋቸው ተግባራት መካከልም ቤተ ክርስቲያኒቱ ፍትሕ ርትዕ እኩልነት የሞላባት፣ መልካም አስተዳደር የሰፈነባት የእውነትና የሐቅ መገኛ እንድትኾን በመንፈሳዊነት፣ ታማኝነትና ተጠያቂነት የተደገፈ መጠነ ሰፊ የሥራ እንቅስቃሴ ማድረግን ይጨምራል፡፡ ‹‹እምነትና ሐቅ በቤተ ክርስቲያን ካልተገኙ ከየት ይገኛሉ?›› ሲሉ የጠየቁት ፓትርያርኩ፣ ካህናትና ቤተ ክርስቲያኒቱን በሞያቸውና በልግሥናቸው አቅፈው ደግፈው የያዙ ምእመናን የድርሻቸውን ለመወጣት ብርቱ ጥረት ማድረግ አለባቸው ማለታቸውም ይታወሳል፡፡
ከፕትርክና ሢመቱም በኋላ ለብዙኃን መገናኛዎች በሰጧቸው ቃለ ምልልሶች÷ ሰው ሊመሰገንም ሊሾምም፣ ሊሻርም፣ ሊወቀስም የሚገባው በጠባዩ፣ በግብረ ገብነቱ፣ በትምህርቱ ብቻ እየተመዘነ እንጂ በዘሩ አንወደውም አንጠላውም በማለት በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ውስጥ ሥር የሰደደ የመጠቃቀሚያ መንገድ ነው የሚባለውን በጎሰኝነት መሳሳብን ተቃውመዋል፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቷ ታላቅ መኾኗንና ለታላቅነቷ የሚመጥኑ ሰዎች መገኘት እንዳለባቸው በአጽንዖት የተናገሩት ፓትርያርኩ፣ ‹‹የተሟላና የተቃና ሥራ ለመሥራት ከኹሉ አስቀድሞ ብቃትና ጥራት ያለው ሥራ መሥራት ያስፈልጋል፡፡ ለዚኽ ደግሞ ሰው በሰው ላይ መደራረብ ሳይኾን ትምህርትና ችሎታ ያለው፣ ለተመደበበት የሥራ ደረጃ የሚመጥን ሰው መቀመጥ አለበት፤›› ብለዋል፡፡
የቤተ ክህነቱ አስተዳደር ከላይ እስከ ታች ተስተካክሎ የመልካም ሥራ አብነት ይኾን ዘንድ ‹‹ሙስና ይጥፋ፤ ተጠያቂነትና ሐቀኝነት ይስፋፋ›› የሚለውን ዐዋጅ ደጋግመው በማሰማት እየታወቁ የመጡት ፓትርያርኩ፣ ቅ/ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያኒቱን ስም ለመጠበቅና ክብርዋን ለመመለስ ሊወስዳቸው ይገባል ያሏቸውን የለውጥ ርምጃዎች በመዘርዝር በምልዓተ ጉባኤው በአጀንዳነት አስይዘው ዐቢይ ውሳኔ ለማስወሰን አስችለዋል፡፡
ፓትርያርኩ ሥር ነቀል ለውጥን የሚያመጡና ቆራጥ አቋምን የሚሹ ናቸው ያሏቸው እኒህ ዐበይት ርምጃዎች÷ ብልሹ አሠራር በፀረ ሙስና እንቅስቃሴ የሚታረምበትና የሚወገድበት፣ የአስተዳደር መዋቅሩና የሚሠራባቸው ደንቦችና ሕጎች ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲኖራቸው ተደርገው የሚሻሻሉበት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ራእይና ተልእኮ በግልጽ የሚታይበት ስትራተጅያዊ የአመራር ሥርዐት የሚነደፍበት፣ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ ላለው የገንዘብ ፍሰትና አያያዝ አንድ ወጥ የኾነ ሥርዐት የሚዘረጋበት እንደኾነ አመልክተዋል፡፡
His Holiness Abune Mathias with thier Graces the Archbishops
ቅዱስነታቸው ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ
አቡነ ማትያስ፣ አሳፋሪና አሳዛኝ ነው ያሉት የአሠራር ብልሽት ሳይታረም ቢቀጥል ቤተ ክርስቲያኒቱ ለሚገጥማት አስከፊ ችግር ፓትርያርኩ ራሳቸውን ከተወቃሾች ተርታ በመቁጠር ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚታደግና ችግሮቿን የሚቀርፍ አጀንዳ በመያዝ በእግዚአብሔር፣ በታሪክና በመጪው ትውልድ ፊት የሚመዘን ችግር ፈቺ ውሳኔ እንዲወሰን የቅ/ሲኖዶሱን አባላት አነሣስተዋል፡፡
ፓትርያርኩ ከሹመታቸው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በርእሰ መንበርነት የመሩትና በግንቦት ወር 2005 ዓ.ም. በተካሔደው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በይፋ ባስታወቁት በዚኽ መግለጫቸው ላይ በመወያየት ቤተ ክርስቲያኒቱ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ሥራዎቿን በመሪ ዕቅድ በመምራት ሙስናንና የመልካም አስተዳደር ዕጦትን ከሥሩ ለመቅረፍ የሚያስችል ጥናት የሚያቀርብ ከሊቃነ ጳጳሳት፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከቤተ ክህነቱ የሥራ ሓላፊዎችና ከምሁራን ምእመናን የተውጣጣ ዐቢይ ኮሚቴ ተሠይሟል፡፡
ይኸው የቅ/ሲኖዶሱ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ የአደረጃጀትና አሠራር ጥናት የሁሉም አህጉረ ስብከት ማእከልና የመንበረ ፓትርያርኩ መቀመጫ በኾነው በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት እንዲደረግ መመሪያ ሰጥቷል፤ ሀ/ስብከቱም በመዋቅርና አደረጃጀት፣ በሰው ሀብት አስተዳደር፣ በሒሳብ አሠራርና ቁጥጥር የሚታይበትን የገዘፈና የተመሰቃቀለ ችግሩን ለመፍታት የባለሞያ ቡድን አቋቁሞ በፍጥነት ወደ ተግባር መግባቱ ተዘግቧል፡፡
በመንበረ ፓትርያርክም በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ደረጃም የተቋቋሙት ሁለቱም አካላት የጥናት ውጤታቸውን በጥቅምት ወር 2006 ዓ.ም. ለተካሔደው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቅርበው በማስገምገም የወሳኝ አካሉን ይኹንታ ከማግኘታቸውም በላይ ቀጣይ የአፈጻጸም አቅጣጫ ተሰጥቷቸዋል፤ የመሪ ዕቅድ ማህቀፉን ያስገመገመው ዐቢይ ኮሚቴ በቀጣይ ዕቅዱን በሥራ ለመተርጎም በሚያስችል አኳኋን በዝርዝር አዘጋጅቶ እንዲያቀርብ መመሪያ ተሰጥቶታል፡፡
የአዲስ አበባ ሀ/ስብከትን የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ጥናት የሠራው የባለሞያ ቡድንም ጥናቱን ወደ ታች አውርዶ በካህናት፣ በምእመናንና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በውይይት ካዳበረ በኋላ ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርብና በቋሚ ሲኖዶሱ እንዲጸድቅ በምልዓተ ጉባኤው በተሰጠው የአፈጻጸም አቅጣጫ መሠረት ተግባሩን አከናውኖ በውይይቱ የብዙኃኑን ካህናትና ምእመናን ተቀባይነት ያረጋገጠውን የጥናት ሰነድ በሀ/ስብከቱ አማካይነት ለቅ/ሲኖዶሱ አስረክቧል፡፡
ከነገ በስቲያ ሰኞ፣ የካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. በሚከበረው አንደኛ ዓመት የበዓለ ሢመት ዋዜማቸው ላይ የሚገኙት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ በቀጣዩ የሥራ ዘመናቸው የተናገሯቸውንና ተጠንቶ የቀረቡላቸውን በተግባር ለመተርጎም የሚንቀሳቀሱበት እንደሚኾን አዲስ አድማስ ያነጋገራቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሓላፊዎች፣ አገልጋይ ካህናትና ምእመናን ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡
ቤተ ክህነቱ ያለበትን መሠረታዊ ተልእኮውን የማያገለግል የተንዛዛ ቢሮክራሲ፣ ወገንተኝነትና ሙስና በፓትርያርክ ደረጃ አምነውና ተቀብለው በዐደባባይ ገልጠው ለመናገር አቡነ ማትያስ የመጀመሪያው እንደኾኑ የተናገሩ አንድ አገልጋይ÷ የፓትርያርኩ ተደጋጋሚ መግለጫዎች በየአጥቢያቸው ችግሩን የሚጋፈጡ ወገኖችን በልዩ ልዩ መንገድ ለተቋማዊ ለውጥና ለፀረ ሙስና ትግል እንዳነሣሣ፣ ይህም ቢያንስ ብልሹ አሠራሩን ለሕገ ወጥ ጥቅም ያዋሉ አማሳኞችን እንዳሸማቀቀ ይገልጻሉ፡፡
ለዓመታት የተከማቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ዘርፈ ብዙ ችግር በአንድ ዓመት ተጠንቶ ሊታወቅ ይችል እንደኾነ እንጂ መፍትሔ ያገኛል ተብሎ እንደማይጠበቅ የጠቀሱት አገልጋዩ፣ አንድ ዓመት የፓትርያርኩን ስኬት ለመገምገም በቂ አይደለም ይላሉ፡፡ ፓትርያርኩ በጵጵስና ከተሾሙበት ጊዜ ጀምሮ ለሠላሳ ዓመታት በውጭ የነበሩ እንደመኾናቸው ቤተ ክህነቱን በበላይነት የመምራት ልምድ ሊያንሳቸው እንደሚችል ጠቁመው፣ ይህን ክፍተት የሚጠቀሙ ከቀድሞም የነበሩና ዛሬም ያልታጠፉ የጥፋት እጆችን ተጽዕኖ በፓትርያርኩ ዙሪያ እንደሚያስተውሉ ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ፓትርያርኩ የሚያስጠጓቸውን አማካሪዎች ማንነት በጥንቃቄ መለየት እንደሚኖርባቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ስለ ፓትርያርኩ የአንድ ዓመት ጉዞ የተጠየቁትና ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ከፍተኛ የሥራ ሓላፊ፣ ፓትርያርኩ ከተሾሙበት ዕለት አንሥቶ ያስተጋቧቸውን የተቋማዊ ለውጥ ዕሴቶችና መርሖዎች ተግባራዊ ለማድረግ ዙሪያቸውን መፈተሽ አለባቸው የሚለውን አስተያየት የሚጋሩት ሓላፊው፣ ‹‹ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያለው ኹኔታ ብቃት ያላቸውን እውነተኛ ባለሞያዎች ከፓትርያርኩ የሚያሸሽ እንጂ የሚያቀርብ አይደለም፤›› ይላሉ፡፡
የአስተዳደራዊ መዋቅር ማሻሻያ ሒደት የራሱ ተግዳሮቶች እንዳሉት የሚናገሩት የሥራ ሓላፊው፣ የአመራር ብቃትና ብስለት ተግዳሮቶቹን ለበጎ ለውጦ በመጠቀም እንደሚረጋገጥ ያስረዳሉ፡፡ ፓትርያርኩ ሥር ነቀልና ቆራጥ ተግባራዊ ርምጃ እወስዳለኹ ብለው በጀመሩት እንቅስቃሴ ተቃውሞ ሲገጥማቸው፣ ተቃውሞውን የማዳመጥ አባታዊ ሓላፊነት ቢኖርባቸውም ዋናውን የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ ሳይቀር እስከማመቻመች መድረሳቸው የፀረ ሙስና አቋማቸው ራሳቸውን ከሚያስተዋውቅ የሚዲያ ፍጆታና ከንግግር ያላለፈ፣ የሚናገሩትንም ያህል ጠንካራና ጽኑ አቋም የሚይዙ ውሳኔ ሰጭ ናቸው ብለው እንዳያምኑ እንዳደረጋቸው አስረድተዋል፡፡ ይህም በውጤቱ የተቋማዊ ለውጥ ተቃዋሚዎቹን በማፈርጠምና የለውጥ ተስፋውን በማመንመን ሒደቱ ዳግመኛ እንዳይነሣ አድርጎ አደጋ ውስጥ ሊከተውና የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር የበለጠ ሊያወሳስበው እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡
‹‹ለፓትርያርኩ የአቋም ጽናት የሊቃነ ጳጳሳቱ የአቋም አንድነት አስፈላጊ ነው፤›› የሚሉት ሌላው አስተያየት ሰጪ፣ አቡነ ማትያስ ከምንጊዜውም በላይ በቤተ ክህነቱ ላይ ተባብሶ የሚታየውን የተቋማዊ ለውጡን ሒደት የሚያደናቅፉ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነቶችን መቋቋምና የቅዱስ ሲኖዶሱን የውሳኔ ልዕልና ማስከበር እንደሚጠበቅባቸው ያሳስባሉ፡፡
ፓትርያርኩ በተመረጡበት ቀን ‹‹እግዚአብሔር ይህን ታላቅ ሓላፊነት እንዴት እችለዋለሁ? በል አንተ ታውቃለህ፤›› ማለታቸው በርግጥም የሚገባ ነው ያሉት እኚኹ አስተያየት ሰጪ፣ ታላቋንና ጥንታዊቷን ቤተ ክርስቲያን ርእሰ አበው ኾኖ ለመምራት የውስጥ ችግሩና የውጭ ተግዳሮቱ የበዛ ቢኾንም ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ ዕድገትና ስሉጥነት የሚያደርሰው ጎዳና በአቡነ ማትያስ ዘመነ ፕትርክና መጠረግና መደልደል ይገባዋል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡
About these ads