(አንድ አድርገን የካቲት 18 2006 ዓ.ም)፡- በወላይታ
ሶዶ ኦቶና ደ/ጽ/ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከጥር 23-25 በተካሄደዉ ጉባኤ ላይ አቶ በጋሻዉ ደሳለኝ
የተናገራቸው ነገሮች ብዙዎችን ያስገረመ ከመሆኑ በላይም አሁንም በሌላ የምንፍቅና ክንፍና በልዩ አስተምህሮ መመለሱን
ማመስከር ችሏል፡፡ ፍጹም ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ ከስርዓተ ቤተክርስቲያን የወጣ በዜማ የታጀበና የረዘመ ‹‹አሜን››
አባባልም ለምዕመኑ አለማምደውት ታይቷል ፤ ሊቃውንቱ ሲሰብኩ ሰው ወደ ውስጡ እንዲመለከትና በጥሞና እና
በአስተውሎ የእግዚአብሔር ቃል እንዲያደምጥ ሲያደርጉ ነበር እኛ የምናውቀው ፤ አሁን አሁን በአስር ደቂቃ ጊዜ ውስጥ
ከ20 ጊዜ በላይ ‹‹አሜን›› የሚያስብለውን ሆነ ‹‹አሜን›› በማያስብለው ምዕመኑን ጮኻሂ የማድረግ አዝማሚያ
እየታየ ነው ፤ ያ መናፍቃን ቤት የሚገኝው ጩኽት እኛ ቤትም ለመግባት ደጃፍ ላይ እያኮበኮበ ይገኛል፡፡ ለዚህ
እማኝ ይሆን ዘንድ ከዚህ ቀጥሎ ያለውን በቦታው ላይ የተከናወነውን ነገር ይመልከቱ፡፡Click here
አቶ በጋሻው ደሳለኝ በድምጽ ከተቀዳ እማኝ ማስረጃ ላይ በሶስቱ ቀናት ጉባኤ የሚቀጥሉትን መልዕክቶች አስተላልፏል (ወደፊት እንደ አስፈላጊነቱ የድምጽ ቅጅው ፖስት እናደርጋለን)፡፡ አሁንም ቢሆን የድፍረት ቃላቶች የእግዚአብሔር ስም በሚጠራበት ቦታ ላይ ላለመስማት አውደ ምህረት ፈቃጆች ለማን እንደምትፈቅዱ አስተውሉ፡፡
አቶ በጋሻው ደሳለኝ በድምጽ ከተቀዳ እማኝ ማስረጃ ላይ በሶስቱ ቀናት ጉባኤ የሚቀጥሉትን መልዕክቶች አስተላልፏል (ወደፊት እንደ አስፈላጊነቱ የድምጽ ቅጅው ፖስት እናደርጋለን)፡፡ አሁንም ቢሆን የድፍረት ቃላቶች የእግዚአብሔር ስም በሚጠራበት ቦታ ላይ ላለመስማት አውደ ምህረት ፈቃጆች ለማን እንደምትፈቅዱ አስተውሉ፡፡
23/05/06 ዓ.ም
- ‹‹ቄስ መነኩሴ አትፈልጉ እራሳችሁ ፀልዩ፡፡››
- ‹‹እኛ ፀልየን ሁለት ህፃናት ከHIV/AIDS ነፃ ሆኑ፡፡››
- ‹‹ያለ ክርስቶስ ስም ፀሎት አያርግም፡፡››
- ‹‹ክርስቶስ ብቻ ሙሉ ስም ነው፡፡››
- ‹‹ክርስቶስን ብዙ መውደድ ነው እንጅ ብዙ መስገድ አያድንም፡፡››
24/05/06 ዓ.ም
- በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ይሁዳ ብር ሲያዩ የሚጎመጁ አገልጋዮች አሉ፡፡
- ‹‹አገልግዬ ወጣቶችን ከብዙ ነገር አስመልጫቸዋለሁ›፡፡››
- ‹‹ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ ነው ለሌላ ለማንም አትስጡ፡፡››
- ‹‹በነፃነት ለማምለክ መውጣት በክርስቶስ ስም ነው፡፡››
- ‹‹በትናንትናው የስብከት አገልግሎታችን አንዲት በሽፍቶች ተደብድባ ዓይኗ ጠፍቶ የነበረ እህታችንእኔ እያሰብኩዋት ስለነበር ጉባኤውም እያሰባት ስለነበር ጉባኤው ሲያልቅ ዓይኗ በራ፡፡››
25/05/06 ዓ.ም
- ‹‹በመዳን ህይወት ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው ኢየሱስ ነው፡፡››
- ‹‹የመጣችሁ እንግዶች ካላችሁ እኛ የምንሰብከው ኢየሱስን እንደሆነ እወቁ፡፡››
No comments:
Post a Comment