አባ ሰረቀ ብርሃን ‹‹በታቦት ዝርፊያ›› ክስ ብጹዕ አቡነ ማትያስ ዘንድ ቀርበው ነበር
- ‹‹ለዚህ መረጃ አቡነ ማትያስ የቀድሞ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ በአሁን ሰዓት 6ተኛው ፓትርያርክ፣ አቡነ ሣሙኤልና አቡነ ኢሳይያስ ህያው ምስክሮች ናቸውና›› መረጃውን የላኩልን የሎሳንጀለስ ምዕመን
- ‹‹አባ›› ሰረቀ ታቦት ሰርቀው ተይዘዋል፡፡ ከገዛናቸው 12 ጸናጽል ያስረከቡን ስድስቱን ሲሆን ፤ ከ 12ቱ መቁዋሚያም 6ቱን ይዘውብን ሄደዋል፡፡
- ‹‹አቡነ አረጋዊም የሚባል ቤተክርስቲያን የለም፡፡›› ‹‹አባ›› ሰረቀ ብርሃን በአንድ ወቅት የሰበኩት ስብከት
- ‹‹በወቅቱ የአሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት አቡነ ማትያስ ማኅተም ወስደው በነጭ ወረቀት ላይ እያተሙ የኔን ፊርማ እያስቀመጡ ሰዎችን ብር እየተቀበሉ ከኢትዮጵያ ወደዚህ ሲያመጡ ተደርሶባቸው..........››በወቅቱ አባ ሰረቀ ከጓደኛቸው ጋር ሲሰሩት የነበረ ሥራ የምዕመኑ ቃል
ከአንድ የሎስ አንጀለስ ምዕመን የደረሰን መልዕክት
(አንድ አድርገን የካቲት 11 2006 ዓ.ም)፡- በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት ሊካሄድ የታሰበው የአብነት መምህራን
የምክክር ጉባኤ በአባ ሰረቀ ብርሃን አማካኝነት ከቅዱስ ፓትርያርኩ በተሰጠ መመሪያ መሠረት ሳይካሄድ መቅረቱ ይታወቃል፡፡ የአባ
ሰረቀን የቀድሞ ተግባር በርካታ ምዕመን ቢያውቀውም ብጹዕ አቡነ ማትያስ የሚያውቁትን እና በሎስአንጀለስ ምዕመናን ላይ ያደረሱትን
በደል የደረሰንን መልዕክት ለእናንተው ለማድረስ ወደድን፡፡ ‹አባ› ሰረቀን ከአመታት በፊት በታቦት ሌብነት ብጹዕ አቡነ ማትያስ
ዘንድ ቀርበውም እንደነበርም መረጃው ያመለክታል፡፡ ስለዚህ ቅዱስነታቸው አሁን እየሰሩ የሚገኙት ቀድሞ ለሰሚ ጆሮ የሚከብድ ዝርፊያ በቤተ ክርስቲያን ላይ ካደረገ ሰው ጋር
መሆኑን ነው፡፡ እስኪ በወቅቱ የነበሩ ህያው ምስክሮች የላኩልንን
መረጃ ይህን ይመስላል፡፡
አባ ሰረቀ ማን ናቸው? ከዚህ በፊት ያልተሰሙ ወሬዎችን ያንብቡት
ምንም እንኳን የሰሩት ሥራ ያደረጉት አሳዛኝና አሳፋሪ ተግባር አንቱ
ለማለት ቢያስቸግርም የቤተ ክርስቲያናችን
ሥርዓት ፣ የሀገራችን ባህል አስገድዶኝ አንቱ
በማለቱ እቀጥላላልሁ ። አባ ሰረቀ ብርሃን (እዚህ ባለሁበት ሎሳንጀለስ ከተማ)
ታቦታቸውንና ንዋያት ቅዱሳታቸውን ዘርፈው ስለሄዱ አባ
ሰራቂ በማለት ይጠሯቸዋል ። አንዲት የቤተክርስቲያናችን አዛውንት ስማቸው እንኳን ሲጠራባቸው የሚያንገሸግሻቸው አውቃለሁ።
ወደ ዋናው ቁም ነገር ልግባና አባ ሰረቀ በሎሳንጀለስ እንዴት
ነበሩ የሚለውን እስኪ እንመልከት፦
አባ ሰረቀ ብርሃን በ1993 መስከረም ላይ ከኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት
ይህንን መረጃ
የሰጡን አባት
እንዲህ ያጫውቱናል። ‹‹አባ ሰረቅ ብርሃንን ለማስመጣት ሂደቱን የጀመእኩት እኔ ነኝ። በ1993 እ.ኤ.አ. የእህቴን ባል እባክህ ጥሩ ካህን የተማረና ሰዎችን የሚያስተምር ሰው ፈልግልን ብዬ ነገርኩት። እርሱም ወዲያው አንድ በጣም የተማሩ ሰው አግኝቸልሃልሁ
ብሎ አጫወተኝና (በኢትዮጵያም ክረምት አካባቢ ነው) ደስ አለኝ። ደውዬም እንዳነጋግራቸው አመቻቸልኝና ፤ አባ ሰረቀን ድውዬ አገኘኋቸው። እርሳቸውም ለመምጣት እፈልጋለሁ ግን ለመጉዋጓዣ 2000 ዶላር ያስፈልገኛል ብለው ነገሩኝ። እኔም ቦርዱን አስፈቅጀ የመምጫቸውን ሁኔታ ጀመርን።2000 ዶላርም ተላክላቸው። ››
በኋላም ስለመምጫቸው ተነጋግረን ንዋያተ ቅዱሳት (ጽናጽልና መቋሚያ ) እንዲሁን ጽላትም ጭምር እንደሌለን ስነግራቸው፤ ሁሉንም ማግኘት እንደሚችሉ፤ ነገር ግን ተጨማሪ 1000 ዶላር እንደሚያስፈልግ
ነገሩኝ። ያንንም ቦርዱን አስፈቅጀ ላኩላቸው። መስከረም 1993 እ.ኤ.አ.
12 ጸናጽል፣ 12 መቋሚያና ጽላት ይዘውልን ሎሳንጀለስ ገቡ። እኛም አባት ናፍቆን ስለነበረ ምንም እንኳን ያወጣነው ወጭ ብዙ ቢሆንም በደስታ ተቀበልናቸው። ስላሁሰንና ዌስት (between Slauson and West) ላይ
አንድ የአድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን
ተከራይትን አገልግሎት ማግኘት ጀመርን።
ትንሽ ቆይቶም አባ
ተከስተ የሚባሉ መነኩሴ (የዛሬው ብጹእ
አቡነ ሣᎀኤል) ወደዚህ እነደሚመጡ ተነገረንና እኔው ተቀብዬ አብረው መኖር ጀመሩ። የሚገርመው ግን አባ ሰረቀ ከሰው ጋር ተስማምቶ መኖርን ስለማይፈልጉ፤
አባ ተከስተ ጋር አለመግባባት ፈጠሩና አባ ተክስተ ወደ
ሌላ ስቴት
ሄዱ።
ከዚያም እርሳቸውም ብቻቸውን እንዳይሆኑ በማለት “ሳንሆዜ የነበረ አንድ ይሥሐቅ የሚባል አገልጋይ ልናመጣልዎት ነበር” ብንላቸው ያሉንን እስከ አሁን አስታውሰዋለሁ ‹‹እኔ
ቤት አንድ
ሰው አይገባም›› ነበር በወቅቱ ያሉት። ያን ጊዜ ነበር አባ ሰረቀ ላይ የነበረው እምነታችን እየተሸራረፈ የመጣው። እንደምንም አግባብተን ልጁን ብናመጣውም አሁንም እርሱም የአባ ተክስተ እጣ ደርሶት አባረሩትና ሄደብን።
መቼም የኛ ቤተክርስቲያን
ታሪካዊ ነችና
ከአሪዞና አባ
ወልደ ሰንበት የሚባሉ አንድ መነኩሴ ደግሞ አስመጣንላቸው።
ለካስ ሁለቱም መሰሪ ነበሩና የሚከተለውን ምእመናን የማይረሱትን አሳዛኝ ሥራ ሰሩ።
‹‹ቀኑ
እሁድ ነው
አስታውሳለሁ ፤
አባ ስረቀና
አባ ወልደ
ሰንበት ቅዳሴ
ቀድሰው ሲያበቁ
አባ ሰረቀ
ለእኔና ለጓደኞቸ
“አባ ወልደ
ሰንበት ወንድሙ
ስላረፈ ልናረዳው
ነው ምን
ትላላችሁ” አሉ።
እኛም አዝነን
አሁን ቅዳሴ
ቀድሰው ከምንነግራቸው
ለምን ሳምንት
ወይንም ነገ
አንነግራቸውም አልናቸው።
እርሳቸውም እሺ
ብለው እኛን
ከላኩ በኋላ
ረድተዋቸው ነበርና
ወዲያው ደውለው
አርድቻቸዋለሁና ኑ
ተባልን በጣም
ሁላችንም ተመልሰን
መጣን ።
እውነት መስሎን
በጣም አዝነን
አባ ወልደ
ሰንበትንም አጽናንተን
ተመለስን። ከዚያም
ወደ ሀገራቸ
መመልስ እንደሚፈልጉ
አባ ሰረቀ
ነገሩን እኛም
አዝነን ያለንን
አዋጥተን ላክናቸው።
ትዝ የሚለኝ
ለቤተሰቦቻቸውም አምነዋቸው
ብር አድርሱልንም
ያሉ ሰዎች
ነበሩ። ግን
አባ ወልደ
ሰንበት ሳያደርሱላቸው
ብራቸውን በዚያው
በልተው ቀርተዋል።
ከትንሽ
ጊዜ ቆይታ
በኋላ የአባ
ወለደ ሰንበትን
እህት ወይዘሮ
አብርኸትን የሚያውቅ
አንድ የቤተ
ክርስቲያናችነ አባል፤
አዲስ አበባ
ሄዶ ወይዘሮ
አብርኸትን ያገኝና
‹‹እባክሽ የወንድማችሁን
መሞት ሰምተን
እኮ አባን
አጽናናቸው ቢሏት›› የምን
ወንድም ነው
የምታወራው? ትለዋለች።
ለካስ አባ
ወልደ ሰንበት
ወድማቸው ሞተ
ትብሎ የተነገረው
የውሸት ኑሯል።
አባ ሰረቀና
እርሳቸው የፈጠሩት
ውሸት መሆኑን አወቅን። ከዚያ
በኋላ ይኸው
አባ ወልደ
ሰንበት በወቅቱ
ዜና ቤተ
ክርስቲያን ጋዜጣ
እንደዘገበው በወቅቱ
የአሜሪካ ሊቀ
ጳጳስ ከነበሩት
አቡነ ማትያስ
ማኅተም ወስደው
በነጭ ወረቀት
ላይ እያተሙ
የኔን ፊርማ
እያስቀመጡ ሰዎችን
ብር እየተቀበሉ
ከኢትዮጵያ ወደዚህ
ሲያመጡ ተደርሶባቸው
መጀመርያ ወደ
ጀርመን አሁን
ደግሞ መቼም
ጅብ በማያውቁት
ሀገር እንደሚባለው
በገለልትኞች ሲኖዶስ
ጳጳስ ሆነው
ካናዳ ይኖራሉ።
ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ፤
አባ ሰረቀ
አባ ወልደ
ሰንበትን እንዲህ አድርገው ከአጠገባቸው ካራቁ
በኋላ ከቤተ
ክርስቲያን አባልት ጋር መግባባት አልቻሉም። ከእለታት አንድ ቀን እንደውም ‹‹ቤተክርስቲያን የለችም ፤ አቡነ አረጋዊም የሚባል ቤተክርስቲያን የለም ፤›› በማለት ሲስብኩ አስታውሳለሁ።
ይህ በእምነታችን የሌለ ኑፋቄ ነው። ከዚያም በኋላ
ከቤተክርስቲያናችን ተለይተው ‹‹የአቡነ
ጳውሎስ እንደራሴ ነኝ
፤ እኔ ማንንም
መነኩሴ ጳጳስ እንዲሆን
አስደርጋለሁ›› ከሚለውና እዚሁ
ሎሳንጀለስ ከሚኖረው ቄስ ጋር ገጠሙና ከእኛ ጋር መጣላት ጀመሩ። ከዚያም አቡነ ማትያስ ለጥቅምት አቡነ
አረጋዊ ሲመጡ
ምእመናን ክስ
አቀረቡ። ውይይቱ የተደረገው በወዳጃችን በ አቶ
ዕቁበ ጽዮን
ቤት ነበር። ብጹእ አባታችንም ቢመክሩዋቸው አልሰማ አሉ። አባ ሰረቀንም ብጹእ
አቡነ ማትያስ ምእመናኑ ምንም አልበደሉምና ‹‹ተሳስባችሁ አብራችሁ ኑሩ›› ቢሉዋቸው አባ
ሰረቀ ‹‹ከአሁን በኋላ እዚህ አላገለግልም››
ብለው ካበቁ
በኋላ ትንሽ ቆይተው ለአቡነ ማትያስ
“ብርሌ ከነቃ…”
የሚል መልስ
ሰጧቸው።
ብጹእ አቡነ ማትያስም ‹‹እንግዲያውስ እናንተም ሌላ ካህን ፈልጉ እርሳቸውንም መጓጓዣ ከፍላችሁ ላኳቸው ፤ እርሳቸውም ንዋያተ ቅዱሳቱን ፤ ታቦቱን ጭምር ያስረክቧችሁ›› ተባለ (ይህንንም በዚያን ጊዜ አባ ኢሳይያስ- የሳንዲያጎ ገብርኤል አስተዳዳሪ የነበሩ- የአሁኑ ብጹእ አቡነ ኢሳይያስ ያረካክቡዋችሁ ተባለ)። እኛም አዝነን እሺ
ብለን 700 ዶላር
ከምዕመናን ሰበሰብንና ዶ/ር
ኃይሉ ፤
አቶ ጥላሁንና አንድ ሌላ ሰው ወክለን አባ
ኢሳይያስን ይዘው
እንዲረከቡ ላክናቸው።
ከዚያም አባ
ሰረቀ በለመዱት አንደበታቸው የተወከሉ ምእመናንን ታቦቱን ነው የያዝኩት ብለው ብሪፍ ኬዝ ይዘው መጡና ፤ ይህንን ለመነኩሴው ለአባ ኢሳይያስ ብቻ ነው የማስረክበው በማለት ወደ ውስጥ ሁለቱ ብቻ ገቡ። ብዙ ቆይተው ሲወጡ አባ ኢሳይያስን የተወከሉት ሰዎች ‹‹ታቦቱን ተረከቡ ወይ?›› ሲሉዋቸው “ታቦት ተረከብኩም አልተረከብኩም አይባልም” አሏቸው።
ተወካዮችም ግራ ግብቷቸው ሲመለሱ አባ
ኢሳይያስም ፤
ለብጹእ አቡነ
ማትያስ ደውለው ታቦቱን እንዳልተረከቡ እንደውም ወደ ውስጥ ከገቡ በኋላ አባ ሰረቀ ብሪፍ ኬዙን ሳይከፍቱ ይረከቡ ይሏቸዋል። አባ ኢሳይያስም ‹‹ይክፈቱት እንጂ እንዴት ዝም
ብዬ እረከባለሁ›› ይሉና ተቀብለው ቢከፍቱት የተገኘው ታቦት ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ
እንደሆነ፤ ከዚያም አባ ሰረቀ እግራቸው ላይ ወድቀው ‹‹እባክዎን አልተቀበልኩም ብለው ለተወካዮች አይንገሩብኝ ፤ ታቦቱን ዲሲ ልኬዋለሁ እዚያ ሄጄ ለአቡነ ማትያስ እሰጣለሁ ወይንም እልከዋለሁ›› ብለዋል ይሏቸዋል።
ይህንን ነገር አቡነ ማትያስ ሲሰሙ
በጣም አዝነውና ተናድደው ነገሩን ምእመናን እንዲሰሙ ያደርጋሉ። ሁለቱም አባቶች (አቡነ ማትያስና አቡነ ኢሳይያስ በሕይዎት ስላሉ
ህያው ምሥክር ናቸውና ስለ እውነትነቱ እነሱው ሊጠየቁ ይችላሉ።) ከገዛናቸው 12 ጸናጽል ያስረከቡን ስድስቱን ሲሆን
፤ ከ
12ቱ መቁዋሚያም 6ቱን ይዘውብን ሄደዋል። ምእመናንም በዚህ ተናድደን ያዋጣነውን ገንዝብ ሳንሰጣቸው ቀርተናል። ከሁሉ
የሚገርመኝ ሲሄዱ
አንዲት ምዕመን ለቤተ ክርስቲያን የሰጠችውን ሰንና ብርን ይስጡን ብለን ስንጠይቃቸው ፤
‹‹መልሳ
ወስዳዋለች›› አሉን። ይህ ሁሉ እንግዲህ በሎሳንጀለስ የነበራቸው ታሪክ ነው።
አንድ መነኩሴ ከሰረቀ ፤ ከዋሸ ፤ ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ
ስልጣን ፤ ገንዝብና ፤ ክብርን ከፈለገ እንዴት መነኩሴ ይሆናል። በአሁኑ ሰዓት
የሚያደርጉት ብጥብጣ እኔ ከአባ ሰረቀ የማልጠብቀው አይደለም። እርሳቸው፤ ከሰው ጋር ተስማምተው የማይሰሩ ፣ የሚዋሹና ፤ በሃሰት ማንኛውንም ኃጢያት ሁሉ ሊሰሩ የሚችሉ ሰው ናቸው። ለዚህ ደግሞ አቡነ ማትያስ ቀድሞ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ አሁን 6ተኛው ፓትርያርክ ፣ አቡነ
ሣሙኤል፤ አቡነ
ኢሳይያስ ህያው
ምስክሮች ናቸውና ፡፡ እነሱን በመጠየቅ ወይንም ለእኔም በመደወል የበለጠ መረጃ ማግኝት ይቻላል ብለውናል።
በአጠቃላይ አባ
ሰረቀ ማለት ለእምነታቸው
ሳይሆን ለሆዳቸውና ለገንዘብ
የሚኖሩ ፤ ካለ ፍርኃት
የሚዋሹ ፤ ካለ ሃፍረት
የሚሰርቁ ፤ ከሰው ጋር
ተባብረውና ተግባብተው መኖርን
የማያውቁ ሰው ናቸው።
እርሳቸው ከሄዱ በኋላ ስድስት ወራት
ሙሉ ካለ
ካህን እሁድ
እሁድ ምእመናን ብቻችንን ተሰብስበን አቶ
እቁባይ መጽሐፍ ቅዱስ እያነበቡልን እንበተን ነበር። በኋላ ይኼው እስከ አሁን የሚያገለግሉንን ታላቅ
አባቶች አግኝተን እንገለገላለን፡፡
እንደውም ባለፈው ዓመት ቤተ ክርስቲያን ገዝተን ገብተናል። በአሁኑ ሰዓትም ከልብ
የሚያገለግሉ ካህናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት
አባላትና ታላላቅ ም ምእመናን ያላት ቤት ክርስቲያን በማግኘታችን ደስትኞች ነን። በማለት አባ ሰረቀ ቤተክርስቲያን
ላይ ያደረሱትን በደል ከብዙ በጥቂቱ እንዲህ አቅርበውልናል፡፡
እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን
No comments:
Post a Comment