Sunday, 9 February 2014

የሃይማኖት ተቋማት ምዝገባን መቃወም የአክራሪነትና ጽንፈኝነት ዝንባሌ ነው ተባለ



  • በሐዋሳው ስብሰባ የተጠበቀው የምዝገባ ዐዋጁ ረቂቅ ለውይይት ሳይቀርብ ቀረ
  • የዐዋጁ ጉዳይ በቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ደረጃ ሊመከርበትና አቋም ሊያዝበት ይገባል
  • የሰላም ዕሴት ግንባታ ሰነዱ በአወዛጋቢ ይዘቱ ለተጨማሪ ግምገማ እንዲዘገይ ተደረገ
Dr. Shiferaw Hawassa
ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም
የሃይማኖት ወይም እምነት ተቋማትን ለመመዝገብና የዕድሳት አገልግሎት ለመስጠት በሚል መዘጋጀቱ የተገለጸውን የዐዋጅ ረቂቅና አሠራሩን በመቃወም የሚካሔድ እንቅስቃሴ የአክራሪነትና ጽንፈኝነት ዝንባሌ መገለጫ መኾኑን የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም ተናገሩ፡፡
ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት፣ በሐዋሳ ለሁለት ቀናት በተካሔደውና የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ‹‹ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ›› ጋራ በመተባበር ባዘጋጀው ዐውደ ትምህርት ላይ ‹‹አክራሪነትና ጽንፈኝነት ከሕገ መንግሥታችን ጋራ ያለው የማይታረቅ መሠረታዊ ቅራኔና መፍትሔው›› በሚል ርእስ ባቀረቡት ጽሑፍ ነው፡፡
ይኸው የሚኒስትሩ ጽሑፍ ‹‹አክራሪነትና ጽንፈኝነት ማብራሪያና መፍትሔዎቻቸው›› ተብሎ በስላይድ ታግዞ የቀረበ ሲኾን መንግሥትና የሃይማኖት ተቋማት በሰላምና ልማት ጉዳይ ጭምር መደራረስ የለባቸውም በሚል የሚካሔድ እንቅስቃሴ መኖሩን ይገልጻል፡፡
እንቅስቃሴው የአክራሪነትና ጽንፈኝነት ዝንባሌ እንደኾነ የሚኒስትሩ ጽሑፍ ያመለክታል፡፡ ‹‹የአክራሪነትና ጽንፈኝነት ዝንባሌዎች የጋራ ጉዳዮች›› በሚል ንኡስ ርእስ ሥር የተካተተው ይኸው የሚኒስትሩ ምልከታ፣ በስም ለይቶ ያነሣው አካል ባይኖርም ‹‹የሃይማኖት ተቋማት ምዝገባ ጉዳይ እና የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ›› የሚሉ ነጥቦችን በመጥቀስ በእነርሱ ዙሪያ የሚቀርቡ ትችቶችን በማሳያነት ማቅረቡ ተዘግ

No comments:

Post a Comment